አባወራ ክብሩን ያስጠብቃል።

ይሄ እውቀት ምንም እንኳን ለሰው ሁሉ ቢሆንም ለአባወራው ግን በተለይ ወሳኝ ነው። አባወራውን ከሌሎች የሚለየው ሆዴ ከሞላ፣ገንዘብ ካገኘሁ፣የወሲብ ፍላጎቴም ከተሳካ ሌላ ምን እፈልጋለሁ ስለማይል ነው።

ክብርን ከማን?
አባወራ ሰብዓዊ(ከእንሰሳ ሲለይ) ሆነ ጾታዊ(ከሴቷ ሲለይ) ክብሩን ከፈጣሪው ያገኘው ነውና በዚህ ላይ “ይጨመራልም” ሆነ “ይቀነሳል” ቢባል ይህን መሠረታዊ ክብር የማያፋልስበት ነው። ስለዚህም እርሱም ይህን ክብር ይጠብቃል ሌሎችም እንዲጠብቁት ግድ ይላል። ልብ አድርጉ አባወራ ከምንም በላይ ከፈጣሪ የተሰጠውን ክብር ይጠብቃል።እርሱ ያልጠበቀውን ክብር ማንም እንደማይጠብቅለት ያውቃልና፤ቅድሚያ የተሰጠውን ክብር ይጠብቃል ከዛም ሌሎችም እንዲጠብቁት ግድ ይላል።
አስተውሉ በእነዚህ አናቅጽ ውስጥ መደጋገሞችን ብታገኙ በስህተት ሳይሆን ሆን ብዬ ትኩረትን እንዲያገኙ እና የደም ሥራችሁ ውስጥ እንዲገቡ ብዬ ነው።

**አባወራ ክብርን ከሰው አይጠብቅም**
ሰዎች ካላከበሩኝ ብሎ አይሟገትም። ክብሩን ፈጣሪው ሰጥቶታል ፤ሰዎች የሚጨምሩለት ክብር በጥቅም የሚጫን እና በኢፍትሃዊነት የሚነሳ ነውና ሲሰጡትም ሳይደንቀው ሲነሱትም ሳይቆጨው ያለንውጽውጽታ ተረጋግቶ ወደ ዓላማው ይጓዛል።
አዎን!!! አባወራን በተረጋጋ ማንነት ውስጥ እንዲኖር የሚያደርገው ይህ ነው። ሰዎች አላከበሩኝም ብሎ አያዝንም እንዲያከብሩትም አይሽቆጠቆጥም፣አያሽቃብጥምም። ክብር አልሰጡኝም ብሎም አያላዝንም ክብሩ ተሰፍሮ ተለክቶ ተሰጥቶታልና። ድብርት ውስጥ የሚከት የበታችነት ስሜትም ሆነ ሌሎችን የሚያስንቅ የበላይነት ስሜት አይሰማውም።

**አባወራ በፈጣሪው ለተሰጠው ክብር ትልቅ ቦታ እና ጥበቃ ያደርጋል**
ይህ ሰብዓዊም ሆነ ጾታዊ ክብሩ የተሰጠው እርሱ ታላቅ ሆኖ ሰዎችን ትልቅ ከሚያደርገው ፈጣሪው ነውና ስለራሱ፣ ስለሰውነቱ፣ ስለወንድነቱ ሰዎች ከሚሉትም ሆነ ራሱ ከሚለው በላይ ትልቅ አክብሮት አለው።ይህንንም የክብር አድማስ ፣በዚህም ውስጥ ያለውን የፈጣሪውን ዓላማ ለማወቅ ይጥራል። ለዚህም ለተረዳው ክብሩ ትልቅ ጥበቃ ያደርጋል። ይህም ማለት ራሱ እንኳ ቢሆን ይህን ሰብዓዊ ክብሩን የሚቃረን ሥራ አይሰራም፤ሌሎችም ይህን እዲያደርጉበት አይፈቅድም።
አስተውሉ የአባወራው ሙግት፦ ክብርን ስጡኝ አይደለም ክብሩን ጠብቆ ክብሬን ጠብቁ እንጂ።
በዚህ ግንዛቤ የአባወራውን የፍቅር ሕይወት ብንታዘብ፥ አባወራው ሚስቱ ክብሩን እንድትጠብቅለት ሲሻ ከፈጣሪው የተቸረውን የሰውነት ከምንም በላይ ደግሞ የወንድነት ክብሩን ጠብቆ እንድትጠብቅ ያደርጋል። እርሱ ክብሩን ንቆ እና አዋርዶ፣ ራስነት ሲሾም ሎሌነትን ከመረጠ፣ አዛዥነት ሲሾም ተላላኪነትን ከመረጠ፣ መሪነትን ሲሾም መመራት ከፈለገ፣ አስተዳዳሪነትን ሲሾም ተዳዳሪነትን ከወደደ፣ አፍቃሪነትን ሲሾም አልተፈቀርኩም ብሎ ካላዘነ፣……ግን በጭራሽ ክብሩ ካላይ እንዳየነው አሁኑም በእጁ ቢሆንም ራሱ ያላከበረውን ክብር ማን ያከብርለት ዘንድ ይሻል። ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ድንጋይ ነው ብለው ይጥሉታልና።

እጩ አባወራ
የወደፊቱ እጬ አባወራም ክብሩን ጠብቆ ያስጠብቃል። የክብር ድንበሩን ደጋግማ የምትጥስ ሴት ሲጀመር ድንበሩን ጥሳ ምን ይወዳታል ሲቀጥል ቢወዳት እንኳ ይህ ጠባይዋ ሳይስተካከል በምንም መልኩ የሕይወቱ አጋር(ሚስቱ) አያደርጋትም። ምክንያቱም ካላይ የጠቀስናቸው የክብሩ ድንበሮች ተጥሰው ለጊዜው ሚስቴን ላስደስት ቢል የአሞሌው ተረት ይደርስበትና ትርፉ ንቀት እና መጣል ይሆናል። ድንበር የለሽ አፍቃሪነት መናቅን(አለመከበርን) እንዲያተርፍ። የዓለምን 50-50 የኪሳራ ትርጉም ተወው። አንተ ምንጊዜም ያለእንከን ልትወዳት እርሷም ልታከብርህ የተገባህ መሆንክን ይኽም ተፈጥሮአዊ መሆኑን አስተውል።

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *