አንተ አባወራ ነህ?(የቀጠለ)

አባወራ አዋቂ ፣ አማኝ(ማለት በፈጣሪው፣በራሱም ተፈጥሮ፣በድርጊቱም)፣ለንግግሩም ሆነ ለድርጊቱ ሙሉ ኃላፊነት የሚወስድ ነው ብለናል። አባወራውን እንዲህ ስንገልጸው ከፈጣሪ በተከፍሎ(በጸጋ) ይቀዳጀዋል እንጂ የማይሳሳት ፍጹም ሆኖ አይደለም።

አባወራ ውሳኔው ጽኑ ነው
ራሱን በትምህርት በሥራ በኑሮው ውጣ ውረድም ከሚገጥመው ፈተና እያስተማረ ደፋርና ጠንካራ (በአካል ብቃትም ሆነ በስነ-አእምሮ)ይሆናል። ይህም ስለወደፊት ህይወቱ ምን መሆን እንዳለበት ዓላማ ይሰቅላል፤ ወደ እዛ ዓላማ ስኬትም ይጓዛል። ከዓላማውም ምንም እንዲያሰናክለው እድል አይሰጥም። ፈተናዎችንም እንደ አመጣጣቸው የተጎዳውን ተጎድቶ ይመልሳል እንጂ ዓላማውን ለፈተና መስዋዕት አድርጎ አይሰዋም። በፈተናዎች ውስጥ ስለሚያገኘው ስጋዊ ትምህርት እና መንፈሳዊ ጸጋ ተጽናንቶ ወደ ዓላማው ይዘረጋል።

ሳያስብ አያደርግም ምክንያቱም ኃላፊነት ይወስዳልና፤አስቦ አውርቶም አይቀርም ፈጻሚ አድራጊ የተግባር ሰው ነውና፤ ድርጊቱ ስህተት ቢሆን በሃዘን በብስጭት ተቆራምዶ አይገኝም ተምሮበት ያልፋልና። አባወራ አዋቂ ነው ብለናል፤ ይህ እውቀቱም በተከፍሎ(በጸጋ) ከፈጣሪው ያገኘው እንጂ የባህሪው ባለመሆኑ ከቃሉ ግድፈት፣ ከሥራው ስህተት፣ከኑሮው ድክመት፣ከሕይወቱም ህጸጽ እንደማይጠፋ ያውቃልና በጸጸትና በሀዘን የሚያጠፋው ጊዜ የለውም። በወቅቱ በነበረው ግንዛቤ የተረዳውን ትክክል ነው ብሎ ያመነበትን ቢያደርገውና ባይሳካለት ከትካዜ፣ ከጸጸት፣ ከሃዘን ይልቅ ከስህተቱ ተምሮበት ለሚቀጥለው ዓላማ ግብዓት ያደርገዋል።

ወንዶችን ወደ አባወራነት ከፍታ እንዳይወጡ የሚያግዷቸው ነገሮች መጥፎ ፈተና የሚባሉ ብቻ ሳይሆኑ መልካም አጋጣሚ መስለው የሚመጡ ክስተቶችም ናቸው። ከነዚህም ውስጥ ትልቁን ቦታ(ድርሻ) የሚይዘው የሴት ፍቅር ነው። አንድ ወንድ ልጅ ፍቅር ይዞኛል በሚል ምክንያት ከትምህርቱ፣ከሥራው፣ ወይም ሊያሳካው ከሚፈልገው እንደ ዓላማ ከያዘው ጉዳይ ቢለይ ለዓላማው ያልቆመ በውሳኔው የማይጸና ይህንንም የሚለማመድ(የሚለምድበት)ይሆናል።

ሴቷም ለጊዜው ለእኔ ሲል ትምህርቱን፣ሥራውን(ንግዱን፣እርሻዉን፣ቢሮዉን፣…….) ትቶ ስትል የወደደችለት ይምሰል እንጂ ውስጧ ግን ወንዱ በዓላማው መጽናቱን ይጠራጠራል፣ነገስ እምነት ይጣልበት ይሆን እንዴ ብሎ ይጠይቃል። ይህ የጥርጣሬ ጥያቄ መልስ እስካላገኘኘ ድረስ ምንም እንኳ ብትወደው ለእርሱ ያላት አክብሮት እና በዕቅዱ ላይ ያላት እምነት እጅጉን ያሽቆለቁላል። ምስኪኑ-ወንድም አለመከበሩም ሆነ አለመታመኑ ወደ ብስጭትና ጭቅጭቅ ሲወስደው እንጂ መንስኤው የእርሱ በዓላማው አለመጽናት እንደሆነ አያስተውለውም።

ለአባወራው ግን እንዲህ አይደለም በቃላት የተገለጸ በወቅት የተገደበ ዓላማ ያስቀምጣል። ይህን ዓላማ ለማሳካት ይጥራል። በዚህ መሐል ጥንካሬውን አድንቃ ለመጣች ሴት እድል ይሰጣል። በምንም አይነት መልኩ ግን ዓላማውን ለእርሷ ”ፍቅር” አይሰዋም ምክንያቱም በኋላ ለእርሱ እምነትም ሆነ አክብሮት እንደማይኖራት ያውቃልና። ስለዚህ አባወራ ቢያገባም ባያገባም ዓላማውን አይስትም። ይህም ባያገባ ሴቶች የእርሱ በመሆን ትዳራቸውን በውሳኔው በሚጸና ከተረጋጋ ባል ጋር ለመኖር ይመርጡታል፤ ቢያገባም ሚስቱ ለእርሱ፣ለቃሉ፣ ለድርጊቱ ትልቅ አክብሮትና እምነት ይኖራታል።….

እናንተስ ምን ትላላችሁ?

..ይቆየን።

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

2 Responses

  1. elshaday says:

    congrats heni for z launching of ur website

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *