አንተ አባወራ ነህ?

 

አባወራ ሲያገባ ብቻ ሳይሆን ከማግባቱም በፊት ታላቅ የሆነ ኃላፊነት የወገን አደራ የዜግነት ግዴታ አለበትና ራሱን እንደሚከተለው ያንፃል።
ኃይለቃል
አባወራ አዋቂ ነው ሲያውቅም ያወቀውን፤አማኝ ነው ሲያምንም ያመነበትን ያደርጋል። ለዚህም ድርጊቱ ኃላፊነቱን ሙሉ ለሙሉ ይወስዳል።
ኃተታ
አባወራ አዋቂ ነው። ከፈጣሪው በተሰጠው ፀጋ ተጠቅሞ የራሱን፣የሚስቱን(የሴቶችን)፣ የአካባቢውን እና በጠቅላላው የተፈጠረባትን ምድር ጠባይ ለማወቅ ከቀደሙት አያቶቹን እና አባቶቹ ይጠይቃል ራሱም ይመረምራል። እንዲሁ በደመነፍስ ሆዱ እስካልጎደለ ፍላጎቱም እስከሞላ ድረስ ከብዙኃኑ ጋር አይፈስም።

አባወራ አማኝ ነው። ከላይ ያጠራው እና ያጣራው በፈጣሪው እውነት ላይ መሥርቶ ገንዘብ ያደረገው የጨበጠው እውቀቱ ብዙኃኑ ከሚከተለው ስህተት ነፃ(አርነት) እንዲያወጣው ኑሮውንም እንዲያቀልለት በሙላት ያለጥርጥር እና ያለፍርኃት ያምናል። መተማመኑም በራሱ ችሎታ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን ሁሉን በሚያውቅ ማድረግም በሚችል የሚሳነውም በሌለ ፈጣሪው ላይ ያረፈ ከእርሱም የሚቀዳ (የሚነሳ) ነው።

አባወራ ሲናገርም ሆነ ሲያደርግ ከዚህ ካወቀው እና ካመነበት እውቀት ተነስቶ ነው። ሲሉ ሰምቼ ፣እንዲህ ሳይባል አይቀርም፣ እንዲህ ተብሎ ፣ መስሎኝ…..የመሳሰሉ አሉባልታዎች እርሱ ጋር ቦታ የላቸውም። ወሬ ለመስማትም ሆነ ለማውራት ሆዱን አይቆርጠውም፤ ለመወደድ ብሎም የሚያስረዝመው የይምሰል ወሬ የለውም። ያቺን የሚያውቃትን ያረጋገጣትን የሚያደርጋትን ይናገራል ያደርግማል።

ታላቁ የአባወራ ብቃትና መገለጫ
ለንግግሩም ሆነ ለድርጊቱ ሙሉ ኃላፊነት ይወስዳል። በየትኛውም አጋጣሚ አባወራ ከአፉ ለወጣው ቃል ከመዳፉ ለተገኘው ድርጊት ሙሉ ኃላፈነቱን እኔ ነኝ ብሎ ይወስዳል። በዚህም በሕይወቱ ውስጥ ወጥነት ያለው ከማስመሰልም ሆነ ከመሸፋፈን የራቀ ግልጽ ስብዕና ይይዛል። የሚመጣውንም ለመቀበል ራሱን ያዘጋጃል እንጂ ምክንያትና ሰበብ አያበዛም፣አይደበቅም፣ አይሹለከለክም።
……ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *