አንተ ወንድ ከኾንክ ….. !

አንተ በትከክል ተፈጥሮኣዊ ወንድነትህን ስትረዳው፣ ስትጠብቀውና ስታጎለብተው ብቻ አባት፣ ባል የቤትህም ራስ ትኾናለህ።

አንተን (አእምሮህን፣ መንፈስህንና አካልህን) የሚያጠነክሩ፣ የሚያሳድጉ በዚህም ወንድነትህን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ንባቦችንና ድርጊቶችን ላይ አዘውትር።

ጊዜህን በእንቶ ፈንቶ አታጥፋ። ለንግግርህም ኾነ ለድርጊትህ ኃላፊነትን መውሰድ ተማር ተለማመደውም። ደርሶ ሰበበኛም አትኹን።

በራስህ ሕይወት ለሚደርሰው ስኬትም ኾነ ውድቀት ማንም ላይ ጣትህን ሳትቀስር ስኬትህን ጨምረህበት ከውድቀትህም ተምረህበት እለፍ።

አንተ ወንድ ከኾንክ የሚስትህ፣ የልጆችህ፣ የትዳርህ፣ የቤተሰብህ ኃላፊ አንተና አንተ ብቻ መኾንህን እወቅ።

በሴታቆርቋዡ(Feminism) የተመረዘው ከባቢህ እንዳይበክልህም ከሚነዛው ውሸት ተጠበቅ።
ነጭ ውሸት ቁጥር ፩
ትዳር 50/50 ነው። ለትዳር መቶ እጅ ሰጥቶ 50 በመቶውን አንተ 50 በመቶውን ሚስትህ አዋጡ የምትባሉበት ስሌት የቁም ቅዠት ነው።

ወንድሜ በሴታቆርቋዡ እሳቤ የተወሰደው ዘመንኛው ተምሬያለሁ የሚለው ትውልድ ሊሟሉ በፍቅር የተጣመሩትን ወንድና ሴት በሒሳብ ስሌት ተራቅቄያለሁ ብሎ 50/50 አዋጡ ይላቸዋል።

ይኽ አመለካከት ለትዳራችሁ የምታደርጉትን የትኛውንም አስተዋጽዖ “በመስፈሪያ” እየሰፈረ የሚያወዳድር የሚያፎካክር እንጂ ተፈጥሮኣዊ ብቃትንና ስጦታን የተመለከተ ዐላማዊ ሚናንም ያገናዘበ አይደለም። ራስወዳድነትን፣ መጠባበቅን ከዚያም መተዛዘብንና መጨቃጨቅን ያመጣል።

እኔ ግን እልኃለሁ በትዳርህ ስኬታማ መኾን ትፈልጋለህ? ሚስትህን(መቼም ያባቷ ልጅ፣ ትኁት የእናቷ ቢጤ ነች) አሰልቺ እና እንጨት እንጨት ከሚል ትዳር መታደግ ትሻለህ? እንግዲያውስ አንተ ወንድ ከኾንክ ንሳ ምክሬን
ተፈጥርኣዊ እውነት ፩ አንተም ኾንክ እርሷ ለተፈጠራችኹበት ዐላማ በተፈጠራችኹበት ሚና እንጂ ስልጣኔ ብሎ ሥራንም ኾነ መዋጮን መስፈር አይመከርም።
አንተ በሚናህ የትዳርህ መሪ፣ አሰትተዳዳሪ፣ አዛዥ፣ ናዛዥ ነህ።
እርሷ በሚናዋ አንተን መከተል፣ ላንተ ቃል በማደር አንተን መታዘዝ፣ በመታዘዟም ለልጆችህ አርኣያ መኾን የሚስትህ ነው።

ከአንተ ለሚወጣው ተፈጥሮኣዊው፣ ወንዳወንዳዊና በልዕልና ላለ ኃይል ተመጣጣኝ፣ ተፈጥሮኣዊና ሴታሴታዊ በኾነ ትኅትና ግብረ መልስ (እርሷ)ስትሰጥ ምሉዕ ትኾናላችሁ። ከኹለት ወደ አንድም ትመጣላችሁ።
በቤታችሁ የኹለታችሁ ሚና ለየቅል ነው። በምንም ዐይነት መስፈሪያ አይሰፈርም፣ እርስ በርሱም አይለካካም።

ውሸት ቁጥር ፪ “በቤት ውስጥ የወንድና የሴት የሚባል ሥራ የለም”
በሴታቆርቋዦቹ (Feminists) አመለካከት ማንኛውም በቤት ውስጥ ያለ ሥራ ወንድ ሴት ሳይባል እኩል ተከፍሎ ይሠራል።

ይኽም ማለት ሥራው የሚፈልገው አካላዊ ጥንካሬና ጉልበት አልያም አእምሮኣዊም ኾነ መንፈሳዊ ብቃት ግምት ውስጥ ሳይገባ ማለት ነው። በተጨማሪም ከሥራው ፍጻሜ በኋላ ኹለቱ ጾታዎች ላይ የሚያሳድረው አካላዊ፣ አእምሮኣዊና መንፈሳዊ (ስሜታዊ) ተጽዕኖም አልታሰበበትም።

ተፈጥርኣዊ እውነት ቁጥር ፪ የቤት ውስጥ ሥራ የወንድና የሴት አለው። “ምዕራባውያን የሰለጠኑት እኮ….. ..” አትበለኝ ። የቤት ውስጥ ሥራን ሲካፈሉ የትዳራቸውን ለኹለት መከፈል የማጣፊያውንም ማጠር ጨምረህ መውረስ ካልፈለክ በቀር።
አስረጅ
በቤት ውስጥ የጉልበት ሥራ ቢኖር ባል ይጠራል ሚስት አትሠራውም አይደለም ልትሠራው ትችላለች ነገር ግን
1. ሲጀመር ከአካል ብቃት አንጻር ከእርሷ እርሱ የተሻለ ነው (ምንም እንኳ የዛሬ ባሎች በአካል ብቃት የሚያሳፍሩ ቢኾኑም)
2. የጉልበቱን ሥራ ከሠራ በኋላ በሠውነቱ ላይ የሚፈጠረው ወይም የሚያድገው ጡንቻ ወንድነቱ ላይ ጤናማ እይታን ቢፈጥር እንጂ… እና ሌሎችም

ሥራው አስቀድሞ ከእኛ የሚጠብቀው ዝግጁነት ከተፈጥሮ ስጦታችን ጋር ይስማማል ወይ? ሥራውን ከሠራን በኋላስ በእኛ ተፈጥሮኣዊ ባሕርይ ላይ ጥሎት የሚሄደው አሻራ ተፈላጊ ነው ወይ? ሥራን እየሰፈሩ ከመከፋፈል በፊት ሊታሰብባቸው የሚገቡ ጥያቄዎች ናቸው።

ለቀዳሚት ሰንበት….. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *