አንዳንዴ በውስጥ መስመር ከምናወራው

ሳተናው!

ግልጽነትህን አደንቃለሁ፤ ብዙውን ጊዜ ስንፍናችንን(ድክመታችንን) ሸፋፍነን የእድሜ ልክ በሽታ እናደርገዋለን።

ካለህበት ጠባይ ለመውጣት የገባህበትን መንገድ ማወቅ፣ ከእነርሱም ተነስተህ መፍትሔውን ማበጀት ይቻልሃል።

ከጠቀመህ እኔ የሄድኩበትን መንገድ እነሆ፦

1) ዘፈን በተለይም “የፍቅር” ዘፈን አትስማ ብትፈልግ ስለሀገር የተዘፈኑትን ስማ።

2) “የፍቅር” ፊልም(የሀገር ውስጥም ኾነ የውጭ)፣ ድራማ ቴያትር አትይ(ከተፈጥሮ እውነት የራቀ ምናባዊና ስሜታዊ ተረት ስለሚበዛባቸው)፤ ከፈለግህ Action film እይ

3) ማንበብን አዘውትር፤ ንባብህ እውነተኛ የኾኑ የሀገር ታሪኮች(የራሳችንንም ኾነ የሌላ) ፣ የግለሰቦች ግለ ታሪክ(Biography) አንብብ በጭራሽ የፍቅር ልብ ወለድ አታንብብ

4) በጠዋት ተነሳ ስፖርት ሥራ በተለይም ክብደት አንሳ፣ push up, pull up ሥራ Aerobics አላልኩህም

5) ከትምሕርትህ ጎን ለጎን የምትወደውን(ዝንባሌ ያለህን) ሙያ ተማር ሥራበትም(ብዙ ዓይነት ልምምዶችhobbies ቢኖሩህ ጥሩ ነው)፤ ሁልጊዜ ዐዲስ ነገር ተማር፣ ቦዝነህ አትቀመጥ

6) የመገናኛ ብዙኃንን፣ ማሕበራዊ የትስስር ገጾችን ቀንስ (እኔ ቁጭ ብዬ ቲቪ ካየሁ ዓመታት ተቆጥረዋል) ከሚገነቡት የሚያፈርሱት ይበዛሉና

7) ራስህን ጠብቅ (በአመጋገብ ጣፋጭ ነገሮችን አስወግድ፣ ባለህ ባቅምህ ጥሩ ነገር ፋብሪካ ያልገባ ተፈጥሮኣዊ ነገር ብላ፣ ንጽሕናህን ጠብቅ፣ ጾምንም ተለማመደው)

8) ስትራመድ ካንገትህ ቀና፣ ከደረትህ ነፋ ቀልጠፍም በል

9) ሰዎችን ስታናግር አይናቸውን እያየህ አውራቸው

10) የምታጎነብሰው፣ የምትንበረከከው እና የምታለቅሰው አምላክህ ፊት እርሱም ለንስሃ ቢኾን እንጂ በጭራሽ ስለምንም ማንንም አትፍራ አትለማመጥም..

11) በጸሎትህ ልመናን ሳይኾን ምስጋናን አስቀድም፣ አዘውትርም(ዛሬን ስላየሃት፣ ነገንም በርዕይህ ስለምታይ፣ ጤነኛም ስለኾንክ)

12)የሰማከውን፣ የተረዳኸውንም ማንኛውንም ነገር በወረቀት ላይ ለመከተብ ሞክር(ሁለት መስመርም ቢኾን)

13) ርዕይ ይኑርህ ወንድምዓለም ሴት፣ ትዳር፣ ልጆች፣ ገንዘብ ርዕይ አይደሉም! ኾድ አደር፣ ሴሰኛ፣ ሱሰኛ እና ሙሰኛ ከመኾን ራቅ። ሀገርህ ባለራዕይ ቆራጥና ጀግና ወንዶችን ትፈልጋለችና አንዱ ኹንላት።

14) ስሜቶችህን (ወሲብ፣ ርሃብ፣ ጥማት፣ ንዴት፣ ሐዘን፣ ደስታ…) ግዛቸው ተቆጣጠራቸው በመዳፍህ ስር አውላቸው። ሰዓት ስለሞላ በቀን ሦስቴ መብላት አለብኝ ብለህ ሳይኾን መብላት ስትፈልግና ስትወስንም ብላ(ለወሲብም፣ ለመጠጥም…እንዲሁ)

15) ራስህን ችለህ ቁም፦ በገሃድ በአካልም ኾነ በሐሳብ
ሰውን አትደገፍ፤ አጨብጫቢም አትፈልግ።

16) ስለርዕይህ አንብብ፣ ተመራመር፣ ተመሰጥ ጸልይ ሰውን ግን ብዙም አታማክር ብዙ ሰው ፈሪ ነው አንተንም እንዲሁ ያደርግሃል። ይልቁንስ እንዴት እውን እንደምታደርገው የሚያግዙህ ካሉ እነርሱን አድምጥ ልብ አድርግ ሕልም ለአንድ ሰው ብቻ የሚታይ የሚገለጥም እንጂ..።

17) ማንም አይደለምና ፍጹምነትን፣ ንጽሓ ባሕርይን ካንተ አትጠብቅ። ይልቁንስ ሞክር ተሳሳት ሰውን ካስቀየምክ ይቅርታ ፈጣሪህንም ከኾነ ንስሓን አትርሳ

18) ላመንክበት ነገር በተለይም የታወቀ፣ የተረዳ ገሃድም ለኾነ ተፈጥሮኣዊ ሐቅ ሰው “ምን ይለኛል” አትበል፤ አትሳቀቅ፣ ይቅርታም አጠይቅ

19) ስለሴትና ስለወንድ ተፈጥሮኣዊ ባሕርይ መርምር እወቅ፤ ተፈጥሮህን ሳታውቅ ልታተርፍበት አትችልምና፦ “ማነህ፣ ምን ዓይነት ጠባይ አለህ፣ አንተ ከሴቷ በምንትለያለህ?”

20) ትዳርህን የምትመራው አንተ ነህና ለዚያ የሚኾን የእውቀት፣ የሥነልቦና፣ የአካል ብቃት፣ የገንዘብ እና የቁስ ዝግጅት አድርግ (ከእኩልነት ተረት ራቅ)፤ በተለይም በዘፈቀደ ያልኾነ በዓላማ መጓዝን ተለማመድ።

ትዝ ሲለኝ ደግሞ እጨምርልሃለሁ..

በርታልኝ የእኔ ሳተና!
ልብ አድርግ! ጀግና ነህ!

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *