እናቷን አይተህ ልጅቷን አግባ

ሳተናው!

ይኼ የምሰጥህ ምክር ተረት ሰምቼ፣ ወድጄውም የምትርክልህ እንዳይመስልህ። የመጀመሪያ ደረጃ የዐይን ምስክር ኾኜ ያየሁት፣ በሁለተኛ ደረጃም የታዘብኩት አልፌ ተርፌም በሕይወት ካለፉበት ሰዎች ላይ ከሰበሰብኩት መረጃ ነው።

አብዛኛውን ጊዜ ደጋግሜ የ”አባቷ ልጅ” ስል ትሰማለህ እንዲሁ ሁሉ ይህች የአባቷ ልጅ የእናቷ ልጅ መኾኗን ልብ ልትል ይገባል። ነገር ግን የእናቷ ልጅ ማለት በማሕበረሰባችን ውስጥ የ”ሴት ልጅ” የሚለውን ገላጭ አይተካም የኋለኛው ለሌላ ጊዜ ይቆየንና የፊተኛውን እንነጋገር።

ወንድም ዓለም!
ለትዳር የምትመርጣትን ሴት “አባቷ በሥነ-ስርዓት አሳድጓታል ወይ?” ብለህ ስትጠይቅ “እናቷስ አርኣያ ኾናታለች?” የሚለው ጥያቄ ተከትሎ ይመጣል። በምርጫህም ወቅት መልኳ፣ የትምህርት ደረጃዋ፣ የኑሮ መደቧ(ከሐብታም፣ ከደሃ፣….)፣ የምታገኘው ገቢ፣ የስልጣን እርከኗ ሁሉ ቀድሜ ያነሳኋቸውን ሁለቱን ቢከተሉ እንጂ አይቀድሙም።

የእናቷ ልጅ የኾነች ኮረዳ፦
? እናቷ የባሏን(የልጆቿን አባት) የቤቱን አባወራነት፣ የትዳሩን መሪነት በመርህ ደረጃ፣ ለወሬ ማድመቂያነት ሳይኾን በልቧ አምና በተግባር የምትከተል በዚህም አርኣያ የኾነችላት ናት።

“እናንተ አባታችሁ የሚላችሁን አትሰሙም!” እያለች ሳይኾን ሲጠራት አቤት ሲያናግራት ሰምታው ነው።

? እናቷ መታዘዝን ታዛ፣ እሺ ማለትን እሺ ብላ፣ ባልን ማክበርን አክብራ ያሳየቻት ናት። ባሏን ስለቃሉ አክብራ፣ ጠብቃ፣ እንደቃሉም አድርጋ ነው

? አመስግኖ መቀበልን በተሰጣት መጠን ሳይኾን ባሏን ስላስከለው ዋጋ አመስግና ተቀብላ አብዝታ፣ አትርፋና አጣፍጣም በመመለስ ያስተማረቻት ናት። የሰጣት ነገር ከሌሎች ቤት አነጻጽራ “ትልቅ ነው ትንሽ ነው” ብላ የእርሱን አቅልላ የሌሎችን አወድሳ ሳይኾን ያንን ለማምጣት ስለከፈለው ዋጋ አመስግና እንጂ።

? እናቷ ትኅትናን ትኁት ኾና፣ ከእንካ ሰላምታ ርቃ፣ የምንዴት መልስም ባፏ ሳይዞር ባሏን አክብራ ማስከበር ያወቀችበት በዚህም አርኣያ የኾነችላት ናት። “ኧረ! እንዴት ወዴት ምን ማለት ነው” ሳትል ለንግግሯም ኾነ ለምታሳየው የሰውነት እንቅስቃሴ ቁጥብና ትኁት በመኾን ማለት ነው።

? እናቷ የባሏን፣ የቤቷን ገበና ሸፍና ልጆቿን ለቁምነገር የምታበቃ ባሏን በማማት፣ የማታሳማ በዚህም የማትታማ ምሳሌም የኾነቻት ናት።

? ለእናቷ ባሏ የቤቷ ንጉስ፣ በሁሉ የምታስቀድመው እርሷም የምትሰማው፣ የምትከተለው በዚህም መሪነቱን የጸናለት ልጅቷም ይኽንንም በግልጥ ያየች ናት።

አንዲትን ሴት ለትዳር ስትመርጥ የእናቷ ልጅነቷን ማጣራትህ በልጅነቷ ያየችውን፣ እውቀት ባልቀሰመው አእምሮዋ፣ ክፉና ደግ ባልለየው ልቧ የተዘራውን መልካም ምግባር ማጣራትህ ነው።

ለጋብቻ አንዲት ሴትን ስትመርጥ፣ ስትፈልግ እና ስታማክር ማማከርም ኾነ ማስመረጥ ከሌሉብህ ሰዎች መካከል ዋነኞቹ ሴታውል እና ምስኪን ወንድን ናቸው።

የፊተኛው ራስወዳድ፣ እንደ እባብ ለስላሳ እንደ ድመትም ዓመሉን የማይረሳ ሲኾን የኋለኛው ደግሞ ሲጀመር አቋም የለሽ፣ ቢኖረውም የማይጸናበት ከሁሉ፣ በሁሉ ለሁሉም ነገር መስማማትን፣ ምቾትን የሚሻ “ሰላምና ፍቅርን” የሚያስቀድም ነው።

እንዴት….. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *