እውን ዛሬ ወንድ አለ?

ለአባቶቹ ውለታ የደረሰ፣አገር የሚወርስ፣በወንድነቱ…..
ከረጅም ዘመናት በኋላ ወንዶች ወንድነታቸው አጠያያቂ የሆነበት ጠባያቸው ብቻ ሳይሆን መልካቸው(አለባበሳቸውን እና የሰውነት እንቅስቃሴያቸው) ጭምር የወንድነትን ቅጥ ያጣበት ጊዜ አሁን ነው። ይህ የወንድነት ወኔ፣ አለባበስ፣አነጋገር፣አካሄድ፣አዛዥነት፣የበላይነት፣ቆፍጣናነት ደፋርነት፣ቆራጥነት፣ወሳኝነት፣የአካል ብቃት፣በጠፋበት ዘመን ታዲያ ልጆቻችንን ከውጭ ሆኖ ለግብረ-ሶዶማዊነት የሚጋብዛቸው እና የሚፈትናቸው መኖሩ ችግሩን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ያደርገዋል።

ለዛሬ በዙሪያችን ያሉ በሥራ ፣ በመኖሪያ ፣ በትምህርት፣በመንፈሳዊ ተቋማት፣በመዝናኛ እና በሌሎችም ማህበራዊ ሕይወቶቻችን የምናገኛቸውን ወንዶች ከማንም በላይም ራሳችንን እስቲ እንታዘብ።
* ጠዋት ሲመጡ ታጥቦ የተተኮሰ ልብስ ከመልበስ አልፈው ሰውነታቸው ሽቶ ውስጥ ተነክሮ ያደረ የሚመስሉ፤
* ከንፈራቸውን የሚያወዛ ቅባት ለመቀባት የቆመ መኪና የጎን መስታወት ላይ ወይንም መታጠቢያ ቤት አስር ጊዜ የሚመላለሱ
*ፊታቸውን መልሰው መላልሰው በመስታወት ካላዩት የማያምኑ
*የመዳፋቸውን ልስላሴ የሚጠብቁ
*ወገባቸውን በቀበቶ ከፍ እና ጠበቅ አድርገው የማይታጠቁ
*ድሮ ድሮ ወንዱ ስፖርት ሠርቶ፣ቀበቶውን ታጥቆ፣ጨማውን አስሮ፣እጁን ሰብስቦ፣፧የደረት ሸሚዙን ከፍቶ፣ደረቱን ገልብጦ፣ከአንገቱ ቀና ብሎ ገርመም ገርመም እያለ እንደባለ ሥልጣን ይሄድ ነበር። ዛሬ ግን የተጣበቀ ቲሸርት፣በተጣበቀ ሱሪ ለብሶ ደረቱን ሳይሆን የቂጡን ፍንክት፣ሸሚዙን ሰብስቦ የእጁን ጡንቻ ሳይሆን ሱሪውን ሰብስቦ የእግሩን ተረከዝ፣ጫማውን ከማሰር ይልቅ ገመድ አልባ ጫማ (lazy man shoe) ተጫምቶ፣ቀና ብሎ በኩራት፣አስተውሎም በትኩረትም ሳይሆን ግራ በተጋባ ማንነት አይኑ ተቁለጭልጮ፣ሴቶች ባጠገቡ ባለፉ ቁጥር እየቀላወጠ፣ መንገዱን በሙሉ ሥልጣን እየረገጠ ሳይሆን ተረከዙ ላይ ቁስል እንዳለበት ይራመዳል።…….የታዘባችሁትን ጨምሩበት

ለንግግሩም ቢሆን ለከት የሌለው፣ ከሚያውቀው ይልቅ የገመተውን፣ አስቦ ሳይሆን በመሰለኝ የሚያወራ ሁሉን አውቃለሁ ባይ ነው። ጠዋት የተናገረውን ማታ፣ሠራተኛው ፊት የተናገረውን አለቃው ፊት የማይደግመው ነው።
ለአባወራ ወንድ ግን እንዲህ አይደለም ምን ጊዜም ሲናገር አስቦ ይናገራል ሰውን ያስደስትልኛልብሎ ሳይሆን ያመነበትን በተለይም እውነትን ያስተላልፋል።
ይህንን እንድትይዙልኝ እፈልጋለሁ ዛሬ ዛሬ ከመጣው ጋር ለመመሳሰል፣ ለሥልጣን፣ለሆድ፣ ለመወደድ፣ ለሌላም ለብዙ ምክንያት ተብሎ የቃላችን ውሉ ላልቷል።ድሮ ግን ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ በሚል የጀግና አባወራ ብሂል ስለምናወራው ነገር እንድንጠነቀቅ አጽንኦት ይሰጣል። እንዴት?
አባወራ
***አስቦ፣አውቆ፣አስረግጦ፣በሙላት፣በኩራት፣ይናገራል***
***የተናገረውን፣አደርጋለሁ ያለውን በሙሉ ሥልጣን ያደርጋል***
***ለተናገረው ቃል፣ላደረገው ድርጊት ማላከኪያ፣ማምለጫ ሳይፈልግ ከፋም ለማም ሙሉ ኃላፊነቱን ይወስዳል***
***ቃሉ እና ድርጊቱ እርሱን ይገልጹታል የሚናገረው፣የሚያደርገው እና እርሱ የተዋሃደ አንድነት አላቸው***
አንተ አባወራ መሆን ትፈልጋለህ?
*ራስህን እወቅ(ራስህን ለማወቅ የቀደሙትን መምህራንን ጠይቅ መጻሕፍትን መርምር) ዛሬ ላይ ዓለም ተፈጥሮን በጠበቀ መልኩ ሳይሆን ለራሷ እንዲመቻት ደበላልቃዋለች፣
*ራስህን ለቃልህ አስገዛው(ለራስህ ታማኝ ሁን)
*የተሰጠህን የመምራት፣ የመግዛት፣የማስተዳደር መክሊት ተጠቅመህ ጥቀምበት። ዓለም በሥልጣኔዬ ደርስኩበት ብላ መክሊቱን አሽቀንጥራ በኪሳራ የሚመላለስ ወንድነቱ የሸሸው ወንድ አድርሳ ባል ይሁን ሚስት (ወንድ ይሁን ሴት) ግራ ገብቶት እርሱም ተቸግሮ ፈጣሪውም አዝኖ በስጋ ፍትወት(በገንዘብ፣በሥልጣን፣በወሲብ)ልቡ የጠፋ ወይንም ፍዝ(ሆዱ ከሞላ ስለወገኑ፣ ስለሀገሩ፣ስለዓለም፣ስለሚስቱ) የማየገደው ሆኗል።
የወንድ ለነበሩ መገለጫዎች እና ጠባዮች ጨቋኝ፣ አቆርቋዥ፣ ፍቅር የለሽ፣ ራስወዳድነት እና የመሳሰሉትን ምክንያት እየተሰጠ ወንድ ሆኖ መገኘት በራሱ አንገት አስደፊ የሆነበት ዘመን ነው።….ይቆየ

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *