ወሲብ(ያልተረዳነው>> ያልተጠቀምንበት>> የተጎዳንበትም ጸጋ

ወሲብ

ያልተረዳነው —>> ያልተጠቀምንበት –>> የተጎዳንበትም ጸጋ(ስጦታ)

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ወሲብ እያልኩ የምጠቅሰው በሰው ልጅ ወንድ እና ሴት መካከል በትዳር ውስጥ የሚፈጸመውን ነው።

አስቀድመን የእኛን ወሲባዊ ጸጋ ከእንሰሶች ጋር በማመሳሰላችን በተለይ ለሰው ዘር ያለውን በረከት እንዳናይ አድርጎናል። የእኛን የወሲብ ፍላጎት፣ ተግባር፣ አፈጻጸምና ከእርሱ የሚገኘውንም ጥቅም ለእንሰሳት ካለው ጋር ማመሣሠሉ መሠረታዊ ስህተት ነው።

ብታመሳስሉት ግን ወሲብ መፈጸማችሁ ባይቀርም የሚሰጣችሁ ጥቅም ለበግ እና ለፍየል ከሚሰጠው የተለየ አይኾንም። ወሲባዊ ስጦታችንን ከእንሰሳት ጋር ማመሳሰል ስጦታችንን አለማወቅ፣ ሰጪውን መናቅ፣ በእርሱም ውስጥ ያለውን ዓላማ አለመረዳት እና ከስጦታውም አለማትረፍም ነው።

ምንም እንኳ ከእንሰሳውያኑ ጋር በስጋዊው ፍትጊያ ቢመሳሰልም በዓላማው ግን ፍጹም ልዩ ነው። እኛ ወሲብ ስጦታ ነው ብለን እናምናለን። ይኽ ስጦታም ፍጹም ከእንሰሳት የተለይ ዓላማ እና አፈጻጸምም አለው።አልያ ግን እንሰሳዊ ጠባይ ስንለው ኹለት ጥጎች ላይ ይወስደናል ወግ አጥባቂ ስንኾን ተጠይፈን ስንርቀው፤ደስታ ልንሸምትበት አንድነት ልናተርፍበት ሲገባ ፉክክርና ጭቅጭቅ ይተርፈናል።እንሰሳዊ ጠባይ ነው ብለን በአጉል ነጻነትም ተወሰደን ልቅም ስንኾን የማያስቡት እንሰሶች እንኳ የማይፈጽሙትን ለተፈጥሮኣችን የማይስማማውን እንፈጽማለን።

ለደስታ እንደ ሰጪው ፈቃድ እና እንደኃሳቡም መጠን ልናተርፍበት ስንሻ በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ኹሉ ለእኛ ልዩ ቦታ ላለው ፍቅረኛችን እና ከእርሱም ጋር ለምንተባበርባት እለት እናቆየዋለን።

ወሲብን፦
፩ ትዳርን ለማጽናት እየተጠቀምንበት አይደለም
ወሲብ በትዳር መመሥረት ውስጥ ከፍተኛ ሚና ቢጫወትም ትዳሩን ማቆየቱ ግን የሕይወት ዘመን ሚናው ነው። ይኹንና በቀደሙት ዘመናት ከነበረው ይልቅ ዘመነኛው ትዳር ውስጥ ይኼ የወሲብ ሚና እጅጉን አሽቆልቁሏል።

ሲጀመር በአኹኑ ወቅት ወሲብ ትዳርን ለማጽናት የሚጫወተውን ሚና ብዙዎቻችን አናውቅም ብናውቅም አንቀበልም ስልጣኔ እና አጉል መንፈሳዊነት ጋርደውብናልና። ሲቀጥል ደግሞ በትዳር ውስጥ ያለው ወሲብ በራሱ ከዘመን አመጣሹ የ”እኩልነት” አባዜ ተጣብቆ ለተፈጠረለት ዓላማ ከመዋል ይልቅ የእኛ ፉክክር ተጠቂ ኾኗል።

ወሲብ ባልና ሚስትየማጣመር ኃይሉ እና ድርሻው መዘንጋቱንና የዛሬውን ጊዜ የባለትዳሮች የትሰጪኛለሽ አልሰጥህም ፉክክር ሳስብ ወዳጄ እ.ማ. የነገረኝ የቀድሞው ዘመን አንድ ታሪክ ትዝ አለኝ። ወይዛዝርቱ ከቀን ውሎዋቸው ሲለያዩ ከመካከላቸው አንዷ “ነገ ቤተክሲያን እንገናኛለን?” ብላ ስትጠይቅ “ባሎቻችን እንዳሳደሩን ነዋ” ብለው መመለሳቸው ጥቅሙን በኅቡዕ የተረዱት መኾኖኑን ያሳያል።

ከላይ ባነሳናቸው ነጥቦች ምክንያት ከቀድሞዎቹ ዘመናት ይልቅ ፍቺ ተበራክቶ ብታዩ አትደነቁ። ትዳራችንን ልናጸናበት የተሰጠንን ወሲብ ከእንሰሳት ፈርጀነው ለእነርሱ የተሰጣቸውን ወሲብ ከእኛ ጋር አንድ አደረግነው እነርሱ በወሲብ ከመራባት ሌላ እንደማያተርፉ ለእኛም እንዲሁ ቢኾን አይያደንቅም ።

ሌሎች እኛ ሰዎች ወሲብን ያልተጠቀምንበት እንሰሶች ደግሞ የማይጠቀሙበት፦
➽ ከእንሰሶች የተራክቦ ክንውን በተቃራኒ የደስታችን፣ የአንድነታችን የፈቃዳችን ስምም መኾን ምክንያት ይኾናል።
➽ ትዳርና ቤተሰብም በዚህ የፈቃድ ስምምነትና ደስታ ላይ ይመሠረታሉ
➽ ሲቀጥል ትዳር ይጸናል ፍቺ ይቀንሳል
➽ በዚህ በጸናው ትዳር ውስጥ ልጆች አስፈላጊውን የአእምሮ፣ የመንፈስ(የነፍስ) እና የአካል ክብካቤ ያገኛሉ

ልብ አድርጉ! ወንዱን እና ሴቷን ያከጃጀለ፣ ተቀራርበው ተወያይተውም ከስምምነት ላይ ሲደርሱ አንድነታቸውን ያተመ፣ በቀጣይም ላለው የፍቅር ሕይወታቸው መጥበቅ ከፍተኛ ሚና የሚጫወተው ስጦታችን ወሲብ ነው። ግን ስላልተረዳነው እናም እውቅና ነፍገነው በመኖራችን ከእርሱ ብዙም አልተጠቀምንም ።
ሳምንት ብንኖር ወሲብ የተጎዳንበት ስጦታ…… ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *