ወሲብ(የመጨረሻው ክፍል)

ወሲብ

ያልተረዳነው–>> ያልተጠቀምንበት–>>የተጎዳንበት ጸጋ(ስጦታ)

የመጨረሻው ክፍል

የተጎዳንበት ስል፦
ቀድሞውኑ ወሲብን አጣመን ከተረዳነው የጸጋው ዓላማ አይገባንም። እርሱ ካልገባን ደግሞ ወሲብን ሳንጠቀምበትና ሳናተርፍበት ዘመናችን ማለቁ አይቀርም። ይባስም ብሎ ለጥቅማችን ተብሎ የተሰጠንና ያደረግነው ነገር መጎጃችን ይኾናል።

ወንድሜ ወሲብን አንተ አልፈጠርከውም፣ አንተ አላገኘኸውም፣ አንተ አልሠራኸውም፣ ወይም በዝግመተ ለውጥም(evolution) አለተከሰተም። ሰውን ወንድ እና ሴት አድርጎ በጾታ ለይቶ ሲፈጥር ቀድሞውኑ በፈጣሪ ልቦና የተሳለ፣ የተወጠነም ዓላማ ያለው ነበር እንጂ።

ሰጪው ደግሞ ፈጣሪህ ከኾነና አንተ ደግሞ በእርሱ አርኣያ(ምሳሌ) የተፈጠርክ ከኾንክ ላንተ የተሰጠህ ወሲብ በምንም ዓይነት መልኩ ዓላማው ለእንሰሳት ከተሰጠው ጋር አንድ አይኾንም።

ይኽ ሳይኾን ቀርቶ ግን አንተ ወሲብን አፈጻጸሙንም ኾነ ላንተ ያለውን የላቀ ዓላማ አውርደህ ከእንሰሳት ብታመሳስለው የምታገኘው ጥቅም ከእነሱ ያልተሻለ እና ያልተለየ ይኾናል።

በዚህን ጊዜ ነው እንግዲህ ወሲብ ለሰውልጅ በሚሰጠው ረብ አለመጠቀም ብቻ ሳይኾን የኃጢያቱ ምክንያት፣ የጉዳቱ መጀመሪያ የጥፋቱም መንኩራኩር የሚኾነው።

ወሲብ ትዳርን በመመሥረቱ ኂደትም ኾነ አጽንቶ በማቆየቱ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። በትዳር መመሥረቱ ላይ ከፍተኛ ሚና የሚጫወተው ወሲብ አጽንቶ በማቆየቱ ላይም ከቀድሞው ቢበልጥ እንጂ ያነሰ ሚና የለውም።
እኛ ግን በአብዛኛውን ጊዜ በምሥረታ ላይ ብቻ ያለውን ሚና አጉልተን በቀጣይ ዘመናት የሚሰጠውን የማጽናቱን ጸጋ አንጠቀምበትም።

ይኼንንም አስተዋጽዖውን ካለማወቅ የተነሳ በጥቃቅን ምክንያቶች ከወሲብ የምንታቀብበት (የምንከላከልበት)፣ ወሲብን እንደምክንያት ሳናነሳ በሌሎች የዳቦ ስም በሰጠናቸው ሰበቦች የምንነጫነጭበት፣ የምንጨቃጨቅበት፣ የምንጋጭበት ብሎም ትዳራችን የሚፈርስበት አንዱ ምክንያት ኾኗል።

ለዚህ ጉዳት የዳረገንን ሥረ ነገር ስንነቅስ፡ ወሲብንና ፈጣሪያችን በወሲብ ውስጥ ለእኛ ያለውን ዓላማ አለመረዳት፣ አጣሞ መረዳት አልያም በቁንጽል መረዳት ኾኖ እናገኘዋለን።

አለመረዳት አልኩኝ፦
ወሲብን ከኃጢአትና ከመቆሸሽ ጋር አቆራኝቶ ለሰው ያለውን ስጦታ አለመገንዘብ።

አጣሞ መረዳት አልኩኝ፦
ተራ እንሰሳዊ ፍላጎት ማርኪያ(መፈጸሚያ) ነው፤ ስለዚህም “ፈቃዳችን ሲያስቸግረን በትዳር ከተወሰንነው ሰው ጋር ተራክቦውን ፈጽሞ መገላገል ነው” ብለን አስቀድመን አጣመን ስንረዳው።

በቁንጽል መረዳት አልኩኝ፦
ከዚህ ቀደም እንዳልነው ወሲብን ለእንሰሳት እንደተሰጠው ዘር ለመተካት ከመፈጸም ያለፈ ጥቅም የለውም ብለን ፈጣሪ ለእኛ የሰጠበትን ዓላማ አጥብበንና አውርደን ከእንሰሳቱ ጋር ስናስተካክለው ነው።

የመጎዳታችን ነገር፦
1. እውቀትና እውቅና አልቦ የኾነው የወሲብ ክልከላ ለትዳር መፍረስ ከፍተኛ ምክንያት ኾነ
2. ለዝሙት ምክንያት ኾነ
3. ለባሕርያችን ያልተስማሙ እንግዳ እና ጎጂ ልማዶች መገኛ ኾነ(ግብረ-ሰዶማዊነትና…..)
ወዘተርፈ

ሳምንት ብንኖር ሴቶችን አቆርቋዡ Feminism በአባወራ እይታ…. … .. .. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *