ወሲብ

ያልተረዳነው —>> ያልተጠቀምንበት –>> የተጎዳንበትም ጸጋ(ስጦታ)

በዚህ ጽሑፍ ላይ ወሲብ እያልኩ የምጠቀመው ቃል በአንድ ወንድ እና በአንዲት ሴት (ሰዎች) መካከል የሚፈጸመውን የግብረ ስጋ ግንኙነትን ነው።

ያልተረዳነው ስልም፦

አንድም፦ ወሲብን ከፈጣሪ በዓላማ የተሰጠን ጸጋ ስጦታ መኾኑን ዘንግተን ለምንም እንደተሰጠን ሳንረዳ ዛሬም ስጋዊ ፈቃድ መፈጸሚያ፣ እንሰሳዊ ጠባይንም ማርኪያ ብቻ አድርገን ማሰባችን፤ ከዚህም ጋር ተያይዞ “መኝታውም ንጹህ ነው” ተብሎ በቅዱስ ቃሉ የጸናውን በትዳር ውስጥ እንኳ ኾነን ከመቆሸሽ፣ ከመተዳደፍ እና ከንጽሕናም ከመራቅ ጋር ስለምናያይዘው ነው።

አንድም፦ እኛ ከእንሰሶች እጅግ በበዛ መልኩ የተለየን ኾነን ሳለን ወሲብን ጨምሮ ሌሎች ፍላጎቶቻችንን ለእንሰሶች ካላቸው ጋር መደመራችን በእኛ ዘንድ ያለውን ተፈጥሮኣዊውንና እውነተኛውን የወሲብንም ኾነ ሌሎች ተፈጥሮአዊ ስጦታዎቻችንን እንዳንረዳ በመጋረዱ ነው።

ከላይ በጠቀስኳቸው ኹለት መሠረታዊ ምክንያቶች የተነሳ ፍቅራችንን የምንገልጽበት፣ አንድነትም የምንመሠረትበት፣ ደስታችንንም የምንጋራበት ኾኖ ሳለ ግን፤ ዋና ዓላማው ለመራባት የኾነ፣ እንሰሳዊ ጠባይ፣ አስነዋሪም ድርጊት፣ የኃጢአትም ምክንያት ተደርጎ በአእምሮአችን ተስሏል።

ከልጅነታችን ጀምሮ ሲነገረን እንዳደግነው ታዲያ ከመቆሸሽ፣ ከማደፍ፣ ከኃጢአትም ጋር አዛምዶት ለቆየው ልባችን የድርጊቱን ዝርዝር ጉዳይ አይደለም አምላካዊ ስጦታነቱን እና ዓላማውን እንዳንረዳው ይይዘናል።

እውነታው

፩ኛ ወሲብ አንድን ወንድ እና አንዲትን ሴት አንድ የማድረግ ኃይል አለው።
በጋብቻ የሚጀመረው በሠርግም የሚበሰረው ትዳር ተጋቢዎቹን ከኹለት ወደ አንድ የሚያመጣቸው ተፈጥሮኣዊው መስሕብ እርሱ ወሲብ ነው። (ዘፍ 2፥24 ፣ 1ኛ ቆሮ 6፥13 ፣15-16) እስቲ ለአፍታ ቆም ብላችሁ ለምሳሌ የሚበቃ ወሲብ የለሽ ትዳርን አስቡ፤ ማግኘት ይቻላልን?

፪ኛ ወሲብ መኝታው በንጽሕና ያጌጠ መኾኑ ከራሱ ከባለጸጋው ከሰጪው የተመስከረለት ነው። በሰውነታችን በስሜት ሕዋሶቻችንም አማካኝነት ከምናገኛቸው ደስታዎች፣ እርካታዎች ውስጥ አንዱ እና ከፍተኛው ወሲብ ነው። ይኽን ስጦታ በአግባብ እና በስርዓት መፈጸም፤ ከእርሱም የሚገኘውን እርካታ በዓለም ላይ ካሉ ሰዎች ኹሉ ከምንወደው፣ ከምንቀርበው እና ከማንጠግበው ሰው ጋር መጋራትስ ታዲያ እንዴት ኾኖ መቆሸሽ ከክብርም ማነስ ይኾናል?

፫ኛ ሌላው ያልተረዳነው በሰው እና በእንሰሳ መካካል ያለው ወሲብ ምንም እንኳ አካላዊ ክንውኑ መመሳሰል ቢኖረውም ለእንሰሶች ከሚሰጠው የመራባት ጥቅም ባሻገር ለሰዎች ያለውን አለመገንዘብ ነው።

ይኼም ወሲብ ለእንሰሶች አራትም፣ ስድስትም፣ ስምንትም…. ወራትን እየጠበቀ ከሚመጣው የመራቢያ ወቅታቸው ጋር የተያያዘነው። ለሰዎች ግን እንዲህ አይደለም ዐመቱን ሙሉ ተመሳሳይነት ያለው የወሲብ ፍላጎት ይስተዋልባቸዋል። ይኼም ከመራባት ባለፈ ባለ ፈርጀ ብዙ ጥቅም ያደርገዋል፦ ፍቅርን መጀመሪያ እና መግለጫ መኾኑ በዚህም የርቢ ወቅት አለመከተሉን ልብይሏል፣ የተጀመረውን ማጠንከሪያ መኾኑ በዚህም ትዳር መጽናቱን ቤት መመሥረቱን ልብ ይሏል ፣ በቀጣይ ለሚመጣውም ፍቅርም እንደ ጸጋው መጠን ዋስትና መኾኑ በዚህም ምክንያት ልጆች ማደጋቸውን ቤተሰብ፣ ሕብረተሰብ፣ ማሕበረሰብ፣ ትውልድም መገንባቱን ልብ ይሏል።

ሌሎች በደረጃ ወደፊት የምናያቸው እውነታዎች
፩ ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ከፍተኛ እና እምቅ የኾነ የወሲብ ፍላጎት እንዳላቸው።(ዱርዬው ያውቀዋል)
፪ ወንዶች ያቺኑ ያለቻቸውን ፍላጎት በሚያሳብቅ እና በግልጽ መግለጻቸው እንጂ ሴቶች በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ ወሲብ የመፈጸም አካላዊ ዝግጁነት እንዳላቸው(ዱርዬው ያውቀዋል)
፫ ይኼንን እምቅ የወሲብ ፍላጎት ገድበው የያዙት ሴትነት፣ ባሕል እና ኃይማኖት መኾናቸውን(ዱርዬው ያውቀዋል)
፬ የትዳርህ ኾነ በእርሱ ውስጥ ላለው ወሲብ መሪ የመደረግህ ምክንያትም ይኼንን እምቅ ኃይል በኃላፊነት ለተሰጠበት ዓላማ እንድታውለው እንጂ መደዴ ኾነህ መጥፊያህ እንዳይኾን።(አባወራ ብቻ ይኖረዋል)

፨ ከላይ ያሉትን ሦስቱን መያዙ ዱርዬውን ከምስኪኑና ከሴት-አውሉ ይልቅ ቢያስመርጠውም አባወራው ግን በተጨማሪ አራተኛዋን መለያው ኾና ምትክ የለሽ ታደርገዋለች።

እነዚህን እና የመሳሰሉትን በርካታ ተፈጥሮአዊ እውነቶች ስታውቅና ስትረዳ በራስመተማመንህ ይጨምራል። በዚህም ትዳርህን የምትመራበት ምክንያትና ውጤቱንም ታውቃለህ።

(እነዚህ ያነበብኳቸው ብቻ ሳይኾኑ በሕይወትም በተግባር የለወጥኳቸው አስረግጬም ገንዘብ ያደረግኳቸው ናቸው። አንተንም አባወራ ትኾን ዘንድ ይጠቅሙሃል።)

ሳምንት ብንኖር የወሲብን ስጦታ ለተሰጠበት ዓላማ ያለመጠቀማችን ነገር .. .. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *