ወስን! ፫ ምስኪንነትህን ካልጣልክ ያለህን ያስጥልሃል

ሳተናው!

በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ አውቀኽ እና ኾን ብለህም ኾነ ሳታውቅ ምስኪን ኾነሃልን? ወይንስ አይታወቅህም? እንግዲያውስ ልንገርህ ስለምስኪንነት የጻፍኳቸውን ኹሉ ዛሬውኑ መለስ ብለህ አንብብ (“የአባቷ ልጅ” መጽሓፍ ውስጥም አለልህ)።

ምስኪንነት ለሰዎች ያለህን ጥሩነት የምትገልጽበት የፍቅር ጥጉ አድርገህ የምታስብ ከኾነ ተሸውደሃል። ይልቁንስ ምስኪንነት በግልጽ (በሚታወቀውና ሰው በተረዳው)ለሰዎች ጥሩ እኾናለሁ፣ እጠቅማለሁም ብለህ በሕቡዕ(ሰው በማያውቀውና ባልተረዳው) ነገር ግን ከእነርሱ ብዙ የምትጠብቅበት፤ ይኹንና እንደጠበቅከው የማታገኝበት የክስረት መንገድ ነው።

ምክንያቱም የትኛውንም ምስኪን የተባለ ወንድ ፈልግና (አንተም ከኾንክ ራስህን) ውለታ ሲውል ብትታዘበው ከዋለለት ሰው ይጠብቃል። በቃላት ገልጾ ፍላጎቱን ተናግሮ ሳይኾን፤ በዛኛው ወገን ዘንድ ግልጽ ያልኾነና የማይታወቅ የሁለትዮሽ ውል ውስጥ ይገባል።

ነገር ግን ውለታውን የተቀበሉት ሰዎች የሚጠበቅባቸውን ወይም የሚፈለግባቸውን አያውቁምና የምስኪኖቹ ድብቅ ፍላጎት ሳይሟላ ይቀራል። ከዚኽም የተነሳ ምስኪኑ ብስጩ ይኾናል “እንዴት?” ቢሉ እርሱ “ጥሩ” ስለኾነ ሰዎች ጥሩ ይኾኑልኛል፣ እርሱ ስለሰጠ ሰዎች ይሰጡኛል ብሎ ጠብቆ። ይኽ ብስጭቱም ከቀን ወደ ቀን እየባሰበት እየተጠራቀመም ሄዶ በአጉል ጊዜ በአጉል ቦታ ይገነፍላል።

አልያም ደግሞ ገንፍሎ ከምስኪንነቱ ጋር የሚጋጭ ማንነት እንዳይዝና ይኼም መጥፎ ስም እንዳያሰጠው ብስጭቱን በኾዱ ያፍንና የተለያዩ በሽታዎችን ይሸምታል።

ምስኪንነትህን ካልጣልክ ያለህን ያስጥልሃል!
========================================

ሳተናው!
ምን አለክ? ጤና አለህን? እርሱን ታጣለህ
አንተ ይኼኔ በሃያዎቹ መጀመሪያ ትኾንና የምነግርህ ነገር ብዙም ላይሰማህ ይችላል። እኔ ግን  በሠላሳ ስምንተኛው እድሜዬ ላይ ነኝና ከራሴ ስሕተት፣ ከቀደሙት ታላላቆቼም ተምሬያለሁና በማካፍልህ ነገር ላይ እርግጠኛ ኾኜ እነግርሃለሁ። 

በዚህ የምስኪን ጠባይህ የምትቀጥል ከኾነ በኑሮ ውጣውረድ ላይ ያንተ ምስኪንነት ተጨምሮ ጤናህን ያሳጣሃል! ቀድሜ እንደነገርኩህ ከዚህ በፊት እንዳጫወትኩህም ምስኪን ልወደድ ባይ ነው። 

“እንዴዬዬዬ! እንዴት?”

እንዴት ብትል፦ከሰው ምንም እንደማትጠብቅ ለሰዎች መልካም ማድረግ ብቻ እንደሚያስደስትህ ኾነህ ትታያለህ። ይኹን እንጂ “ለሰዎች ጥሩ ስኾን ሰዎች ይወዱኛል፣ ሴቶችም ይቀርቡኛል ከሚያስፈልገኝም አላጣም” እንደምትለው ሳይኾን ይቀራል። በዚኽም ብስጭት፣ ንዴትን፣ ቁጣንም በውስጥህ ታከማቻለህ። 

ሰዎችን መጀመሪያ ካስለመድካቸው ምስኪንነትህ ጋር ንዴትህ አይኼድምና አታወጣውም አትገልጸውም። ነገር ግን “ለሰዎች ጥሩ ኾኜላቸው፣ ለሰዎች ከሚያስፈልጋቸው ነገር ሳላጎድልባቸው፣ ለኔ ለምን አያደርጉልኝም? ለምንስ አንተሳሰብም?” እያልክ በውስጥህ ትብከነከናለህ። ከዚህም የተነሳ የጨጓራ በሽታ፣ የደም ግፊት፣ የልብ ውጋት(stroke)፣ (በተለይም የኋለኛው በወንዶች ዘንድ የተለመደ በሽታ መኾኑን ልብ ይሏል) ታተርፋለህ።…..

ሳተናው!
ምን አለክ? ትዳር አለህን? እርሱን ያሳጣሃል

ምስኪን ከዚኽ አጉል “መልካምነት” ሁልጊዜም የሰውን ጎዶሎ ለመሙላት ከመቸኮሉ(በግልጽ) የተነሳ፤ ነገር ግን ደግሞ ከራሱን ስንፍናና ፍርሃት በመነጨ(በድብቅ) ስኬታማ ሰዎችን ሳይኾን እንደርሱ ሰነፍ፣ ፈሪና ሰበበኛ ሰዎችን ይቀርባል፣ ያቀርባልም። 

ይኽም እነርሱ ሁልጊዜ እንከን አያጣቸውምና እርሱን ሲሹት እርሱ ደግሞ “መልካም” ሰው ለሰውም “ችግር” ደራሽ ነውና የእነርሱን ችግር በመቅረፍ ይጠመዳል። ይኹንና የእርሱን ፍላጎት የሚፈጽምለት ያጣል።

የፍቅር(የትዳር) ሕይወቱም ይኼንኑ ይመስላል። ብዙውን ጊዜ በተፈጥሮ ከባልነቱ ከእርሱ የሚጠበቅበትን ከማድረግ ይልቅ ድብቅ ዓላማውን ይዞ ወደ ትዳር ይገባል። አንድም ሴቶችን “ማሕበረሰቡ፣ ኃይማኖቱ፣ ፖለቲካው ጨቁኗቸዋል” ብሎ አስቦ በተጨማሪም “መልካም ባደረኩላት ቁጥር ትወደኛለች” ብሎ ጠብቆ ወደ ትዳር ይገባል።

የሚመርጣትም ሴት ሁልጊዜ የእርሱን ትድግና የምትጠብቅ ትኾናለች። ስለዚህ…. …. ይቆየን
(ዘርዝረን እናየዋለን)

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *