ወንዱን መስለብ

ሴታቆርቋዥ ወንዶች ክፍል ፪
ሳተናው!

ሴታቆርቋዥ ወንዶች(Feminist men) ተፈጥሮኣዊ ዓላማና ሚናቸውን ሳይለዩ(ሳይረዱ)፣ ግዴታቸውንም ሳይወጡ አባወራውን በተወጣው ግዴታ በለየውም ሚና የሚኮንኑ ናቸው።

እንዲሁም በጭብጨባ እና በውዳሴ ብቻ የቆሙ አቋም እና ወኔ የሌላቸው በሰው(በሴቶች) ለመወደድ ብለው ከእውነት(ከፈጣሪ) የሚጣሉ ናቸው። ለእነርሱ እውነትን፣ የተፈጥሮ ሐቅን፣ ከመመስከርና ከማድረግ ይልቅ የሰውን ጭብጨባ(በተለይም የሴቶችን ይኹንታ የሚያገኙበትን) ተከትለው ይውላሉ፣ እነርሱ የራሳቸው አቋም የሌላቸው ከመኾናቸው የተነሳ የሰው አጀንዳ አጀንዳቸው፣ የሰው ፍላጎት ፍላጎታቸው የኾኑ ናቸው።

ራሳቸውን ፍላጎታቸውን፣ ተፈጥሮኣዊ ጥያቄያቸውን በአግባቡ መግለጽ፣ መግዛትና መምራትም አይችሉም። ከዚኽም የተነሳ ትዳራቸውን (ቤታቸውን)፣ ተቋማትን ሀገርንም ጭምር መምራት አይኾንላቸውም።

ይኽን ማለቴ ግን በአስተዳደግም ኾነ በአኗኗር ዘይቤ ከመጣባቸው ምስኪንነት አልፍ ተርፎም ሴታቆርቋዥ ጽንሰ ኃሳብ ማራመዳቸው ለዚኽ ቢዳርጋቸው እንጂ የተፈጥሮ ውሱንነት ኖሮባቸው አይደለም።

ብዙውን ጊዜ እነዚኽ ወንዶች ከፈረሰ ቤተሰብ በአንድ ወላጅ (አብዛኛውን ጊዜ በእናት) ብቻ ያደጉ አልያም ለስም ብቻ ካለ ትዳር በስነልቦና(psychologically)፣ በመንፈስ(emotionally) እና በአካል (physically) ከልጆቹ የራቀ አባት ካለበት ቤት የሚገኙ ናቸው።

====================================

ሳተናው!

ሴታቆርቋዥ ወንዶች (Feminist Men)ብዙውን ጊዜ ከምስኪን ወንዶች ጋር አንድ የሚያደርጋቸው የጋራ ጠባይ አላቸው። ይኸውም ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ በራስ ያለመተማመን(በተለይም ከሴቶች ጋር ሲገናኙ) አሁንም አሁንም በሚሠሩት ሥራ የሰውን ይኹንታ ሙገሳንም መጠበቅ ናቸው።

በተጨማሪም ሥራቸውን በራሱ በሥራው፣ በፈጣሪም ቃል መዝኖ ልክነቱ አግባብነቱን ከማረጋገጥ ይልቅ ብዙ ሲጨበጨብላቸው ልክ የሠሩ የሚመስላቸው አድናቂ ሲበዛላቸው ሰው ከእነርሱ ወዲያ ላሳር የሚሉ ናቸው።

ይኹንና ሴታቆርቋዥ ወንዶች(Feminist men) ከምስኪኖቹ  በተለየ መልኩ ለሴቶች “ተቆርቋሪ ነን” ሲሉ በአደባባይ ይለፍፋሉ(ይናገራሉ)። “ተቆርቋሪ” መኾናቸው ባልከፋ ራሱን በዓላማ፣ ቤቱንም በስርዓት በሚመራው አባወራ ላይ ብዙውን ጊዜ ቁጣቸው ትነዳለች ብስጩም ይኾናሉ።

የዚኽ ምክንያት ደግሞ በቀደመው ጦማሬ እንደገለጽኩት፤ አባወራው እንደእነርሱ ለሴቶች ሳይሽቆጠቆጥ፣ ልወደድም ብሎ ሴቶችን “ደስ የሚያሰኝ” ሳይሰራ ነገር ግን ሊሠራው የተገባው ነገር፣ በተፈጥሮ የተሰጠውን ሚና፣ ከፈጣሪም የተጣለበትን አደራ፣ ለመሠረተው ቤተሰብም የሚገባውን ግዴታ ሲሠራውና ሲሳካለትም ስለሚያዩ ነው።

እንዲኽም አድርጎ ከእነርሱ በተሻለ ቤቱን ይመራል፣ ልጆቹን በስርዓት ያስተምራል ለቁም ነገርም ያበቃል። ሀብታም ላይኾን ይችላል ነገር ግን በተመጣጠነ ኑሮ ራሱን እና ቤተሰቡን ያኖራል።

ይኽ ታዲያ ብዙ ተጨብጭቦላቸው፣ ብዙ “ተከታይ” አፍርተው፣ ብዙ ለፍልፈውም ነገር ግን የሴቶች(የሚስቶቻቸውን) ልብ መግዛት፣ መማረክ፣ ቤታቸውን መምራት፣ ግዳጃቸውን መወጣት፣ ተፈጥሮኣዊ ፈቃዳቸውንም መፈጸም ያልቻሉትን ሴታቆርቋዥ ወንዶች (Feminist men) ያበሳጫቸዋል።

አንድም ደግሞ ተፈጥሮኣዊ ፈቃዳቸውን ለመፈጸም “እድሉን” ሲያገኙ ጓጉተው፣ ናፍቀውና ደጅም ጠንተው ነውና ከጥግ ሳያደርሱት(በተለይም ሚስታቸውን ሳያደርሷቸው) ይጨርሳሉ። ታዲያ ደግመውና ደጋግመው ብስጭትና ቁጭትም ቀላቅለው ስለሴቶች “መብት” ሲጮኹ ወይም አባወራውን በአደባባይ “አምባገነን” ብለው ሲከሱ (ያቺ የመኝታ ቤቷ እነርሱና ሚስቶቻቸው ብቻ ለሚያውቋት) ለጎዶሎዋቸው መሙያ ለመጠቀም፣ ከተከሳሽነትም ለመዳን ያዘጋጇት የስርቆሽ በር እንድትኾናቸው ይሻሉ፤ አትኾንም እንጂ።

============================================
ሳተናው!

አባወራው ጋር ግን ይኽ ጠባይ አይታይም፤ ሴቶችን(ሚስቱን) ይወዳል  ፈጣሪ የሰጠውን ግዴታም ይወጣል። በሚያደርገው ነገር ተገቢነቱን፣ አስፈላጊነቱን እና አቅሙን አገናዝቦ ያደርጋል እንጂ እወደዳለሁ፣ ወሲብ አገኛለሁ ብሎ አያስብም ስለማያስብም አያወራም፤ ስለማያወራም አያደርግም፣ ያን ጠብቆ ስለማያደርግም ከብስጭትና ከንዴት ላይ አይወድቅም።

ይኽ በራስ መተማመኑ ግን ስለሚያበሳጫቸው የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ወንዱ ራሱን ገዝቶና መርቶ ትዳሩንና ቤተሰቡን ብሎም ሀገሩን እንዳይመራ፣ ፈሪና ደንታቢስ እንዲኾን ስነልቦናውን ይሰልቡታል።

ሴታቆርቋዥ ወንዶች(Feminist men) ሴቶችን ከ”መውደዳቸው” የተነሳ ስለእነርሱ “እንቆረቆራለን” ይበሉ እንጂ አይወዷቸውም።

ምን? አዎን አ.ይ.ወ.ዷ.ቸ.ው.ም እንዴት…. … … ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *