ወንዱን አልጫ ማድረግ ዘመናዊ ባርነት

ሳተናው ዐለም ለጥፋት ሥራዋ ይረዳት ዘንድ የሰውን ዘር በባርነት ቀንበር ሥር (የዳቦ ስሙን ነፃነት በማለት) ለመግዛት ዘወትር ትታትራለች። ለዚህ ደግሞ ቀንደኛ መሣሪያዋ ትውልዱ ተፈጥሮውን እንዳያውቅ፣ ራሱን እንዳይኾን ማድረግ ሴቱም የሴት መልክ/ውበት ወንዱም የወንድ ልክ እንዳይኖረው ማንነቱን ማጥፋት ነው።

በተጨማሪም ወንዱ ተፈጥሮውን እንዳያውቅ፣ የሚያሳውቀውም እንዳይኖር ብቻ ሳይኾን አውቆም ያወቀውን እንዳይኖረው ታሸማቅቀዋለች። በቤቱ ስነስርዓትን ማስፈን ሚስቱንና ልጆቹን ስነምግባር ማስተማር ሲፈልግ አምባገነን ትለዋለች።

ጀግንነትን የሚሰብኩ፣ ቆራጥነትን የሚያስተምሩ፣ አትንኩኝ ባይነትን የሚያስተጋቡ መልዕክቶች ይታፈናሉ። ምክንያቱም “ዘመኑ የፍቅር ነው…” ይሏችኋል

ይኹን እንጂ ወገኔ ግን አትሸወድ፤ አጥላልተው የሚቀልቡህ ያባቶችህ ታሪክ ሀገርህን ከነሉዓላዊነቷ፣ ዜግነት ከነክብሯ ያቆየልህ ነው።

ሳተናው!
ልብ አድርግ! አኹን አኹን የሚመጡት መንግስታት ትውልዱ እንደ ባሪያ አቀርቅሮ እንዲሠራ ከዚያ በተረፈ ጊዜው ግን በመዝናናት ስም በዝላይና ፈንጠዚያ እንዲያሳልፍ እንደኾነ አያያዛቸው ያስታውቃል። አንተም ኾንክ ሴቷ እህትህ ተፈጥሮኣዊ ጸጋችሁን እንድታውቁት በእርሱም ተጠቅማችሁ ትውልድንና ሀገርን እንድትጠቅሙ አያበረታታም።

ይልቁንስ ወንዱን ከሴቷ ሴቷንም ከወንዱ የሚያምታቱ በስልጣኔ ስም የሚሳቡ ዐዳዲስ ባሕሎችን ያስተዋውቀናል።

አመንዝራዋ ዐለም ይኽንን ለመተግበር በቀላሉ የምትጠቀምበት ዋነኛው መሣሪያ መገናኛ ብዙኃኑን(በተለይም TV) ነው። በዚህ ቀንደኛ ወንዱን ማለጫ መሣሪያ በስልጣኔና ዘመናዊነት ስም ወንዱ የአቋም ሰው፣ ለዓላማው የሚኖር፣ ቃሉን ጠባቂ፣ የስነስርዓት ልክ፣ የስነምግባር አርአያ፣ አሸናፊ፣ ደፋር፣ የትዳሩም መሪ ተደርጎ አይቀርብም።

ይልቁንስ ጥቅመኝነት፣ ሸማችነት፣ ፌዘኝነት፣ ፈሪነት፣ ሽቁጥቁጥነት፣ ተሸናፊነት፣ ስሜታዊነት፣ ኾደ ቡቡነትና፣ አስገድዶ ደፋሪነት፣ የመሳሰሉት በኪነጥበብም ኾነ በዜና ተሠርተው ይቀርቡለታል።

እነዚህ የመገናኛ ብዙኋኑ ትውልድ አፍራሽ መርሃግብሮች ታዲያ አኹን አኹን ትውልዳችን ውስጥ ሥር እየሰደደ በመጣው ጤናማ ያልኾነ የአመጋገብ ሥርዓት ሲታገዝ ጉዳቱ የከፋ ይኾናል። የታሸጉ ምግቦችና የተለያየ የፋብሪካ የምርት ሂደትን ያለፉ ጣፋጭ ምግቦች ዋነኛ ጎጂዎቻችን ናቸው።

ወንድሜ ለዛሬ ግን ከእነዚህ ውጪ የኾነና በተፈጥሮ የምናገኘውን አኩሪ አተር ላስተዋውቅህ።

አኩሪ አተር(ወኔ ሰላቢው ጥሬ)

አኩሪ አተር አስፈላጊ የተባሉ አሚኖ አሲዶችን በውስጡ ስለሚይዝ ከእፅዋት የሚገኝ የተሟላ ሊባል የሚችል ፕሮቲን ነው። ለምግብነትም በተለያየ መንገድ ይውላል በዘይት፣ “ስጋን በሚተኩ” ምርቶችና በወተት መልክም ይቀርባል።

ይኹን እንጂ አኩሪ አተር ውስጡ በሚገኘው phytoestrogen አማካኝነት የወንዶችን ተፈጥሮኣዊ ወኔ የመስለብ አቅም እንዳለው ተደርሶበታል። ይኽ ንጥረነገር በተፈጥሮ በወንዱም ኾነ በተለይም ደግሞ በሴቷ ውስጥ እንደሚገኘው oestrogen ተመሳሳይ ሥራን የሚሠራ ነው። በነገራችን ላይ የልብ ሕመምንና ካንሰርን በመዋጋቱ ላይ ጠቃሚ አስተዋጽዖ አለው።

Oestrogen የሴት ሆርሞን ተብሎ ሊጠራ የሚችል ሴቶች በተፈጥሮ ሴት የሚያደርጋቸውን ጠባይና አካላዊ ዝግጅት አስቀድሞ በማሰናዳቱ በኩል ዋነኛውን ሚና የሚጫወት ነው። አኩሪ አተርን በምንመገብበት ጊዜ ታዲያ ይኽ ሆርሞን በከፍተኛ ኹኔታ የሚነቃቃ ሲኾን የTestosterone ተጽዕኖንንም ያደበዝዘዋል።

ከዚህም የተነሳ ተመጋቢው ወንድ በተፈጥሮው ሊያሳያቸው የሚገቡትን ወንዳዊ ጠባያት እየለቀቀ ወንድም ሴትም መኾን እየቸገረው መሐል ሰፋሪነቱ ያይላል። ምናልባትም ጡቱ ሲንጠለጠል ሰውነቱ ሲሰባ “ወፍሬያለሁ”ብሎ ከመጨነቅ ውጪ ይኼ ይኾናል ብሎ የሚገምት አይኖርም።

የወሲብ ፍላጎቱ ሲከስም፣ ማስረገዝ ሲሳነው፣ ከዓላማው ይልቅ ለመልኩ ሲጨነቅ ማየትና መስማት እየተለመደም ይኼዳል። በኪነጥበብ ስም ከሴት(ከሚስቱ) ፍቅር ውጪ መኖር እንደማይችል፣ የመኖሩ ምክንያት የሕይወቱም ግብ እርሷ እንደኾነች አድርጎ ከሽኖ ሲያቀርብም ይወደሳል።

አኹን የሰምኑን የስጋና የወተት ገበያ ሳስበውና የዋጋቸውንም መናር ስታዘብ መጪው ትውልዳችን የ”አኩሪ አተር ትውልድ” እንዳይኾን እፈራለሁ ምዕራብያውያኑ Soy boy እንዲሉ።
http:// http:// https://www.urbandictionary.com/define.php?term=Soy%20Boy

ይኽ ደግሞ ስለሀገሩ፣ ስለአባቶቹ፣ ስለፈጣሪው፣ ስለወገኑ፣ ስለ ስነስርዓት ግድ የማይሰጠው ከእጅ ወደአፍ በኾነ ኑሮ ታጥሮ የሚኖር ሲጠሩት አቤት ሲልኩት ወዴት ብቻ የሚል፣ ራሱን ለቁምነገር አብቅቶ ሚስቱንና ልጆቹን ወደዚያ የማያመራ፣ ከመምራት መመራት የሚቀናው፣ የማይጠይቅ የማይመረምር እና ከተፈጥሮው በራቀ ጠባይም የሚኖር ፍዝ ይኾናል።

ሳተናው! ዐለም ከቃጣችብህ አንተን አልጫ የማድረግ ሴራ ራስህን ጠብቅ ትውልድንም ታደግ…. ይቆየን

ወላጆች በተለይም ለወንዶች ልጆቻችሁ ለትምሕርት ቤት ምሳ ከአኩሪ አተር ውጪ በተለይም እቤት ውስጥ በሚዘጋጁ ምግቦች ተኩ።
http:// https://steemit.com/blog/@thauerbyi/deep-soy-and-the-emasculation-of-men

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *