ወንድነትህ ሲነቀፍ አብረህ አታጨብጭብ

ሳተናው!

ሰዎች ወንድነትህን ሲነቅፉ አትስማቸው፤ በጭራሽ! አስተውል! አንተ ጀግና ጻድቅ፣ ካህን፣ ንጉስ ባለጸጋ አልያም ደግሞ ፈሪ፣ ደሃ፣ ማጅራት መቺ፣ ብትኾን እነዚህን በመሥራትህ አንተው ትጠየቅበት እንደኾነ እንጂ አንተም ኾንክ ሌላ ሰው በወንድነትህ(በተፈጥሮህ ላይ) ማመካኘት እርሱንም መክሰስ አይችልም።

የሰው ልጅ አስቦና አቅዶ ወዶና ፈቅዶም በሠራው ሥራ ይወቀስ እንጂ ፈጣሪ በዓላማ በሰጠው ተፈጥሮኣዊ ጸጋ መውቀስ ጸጋውንም ማናናቅ የተሰጠበትን ጥቅምና ዓላማ አለመረዳት አልፎ ተርፎም የፈጣሪን ዕቅድና ሀሳብ መቃወም ነው።

ሰዎች የሚሠሩት የትኛውም መልካምም ኾነ ክፉ ሥራ ከጾታቸው፣ ከዘራቸው፣ ከቀለማቸው ጋር  የማይገናኝ ነው። ስለዚህም ለሥራቸው ራሳቸው ግለሰቦቹ ኃላፊነት ቢወስዱ እንጂ ዘራቸው፣ ቀለማቸው ጾታቸው አይጠየቅም። 

እንዲኹም ደግሞ እኛ በሠራነውም ሥራ(ደግም ኾነ ክፉ) “እኔው ራሴ አደረግኩት” ማለት ሲገባን በተፈጠርንበት ኩነት ማሳበብ ኃላፊነት ላለመውሰድ የሚደረግ ሽሽት ነው።

አለበለዚያ ግን የድርጊቱ ፈጻሚዎች(ድርጊቱ ክፉ ከኾነ) መቼም መለወጥ መሻሻል የማይልጉ፣ አንሻሻልም ብለውም ተስፋ የቆረጡ የተገኙበትን ዘር(ብሔር) የሚረግሙ፣ የተሰጣቸውን ቀለም የሚጠሉ፣ በጾታቸው የሚሸማቀቁም ይኾናሉ።

ጠላት ደግሞ ይኼን አጋጣሚ ብሔራችንን(ሀገራችንን) ለማጥቃት፣ በቆዳ ቀለማችን ለማግለል፣ ተፈጥሮኣዊ ጾታችንን ለማንኳሰስ ይጠቀምበታል።

ሳተናው!

ወንድነትህ ባንተ ውስጥ ያለ፣ አንተን የሚገልጽ፣ በዓላማ የተሰጠህ፣ ተፈጥሮኣዊ ጸጋህ ኩነትም ነው። እግዚኣብሄር አንተን የፈጠረበትን ዓላማ የምታሳካበት ዓይነተኛ መሣሪያም ነው። 

ትኩስ ወይም በራድ መኾንህን አስተውለህ ራስህ ተገልግለህ፣ ፍጥረትን ልትንከባከብበት ፈጣሪንም ልታገለግልበት ተሰጥቶሃል።

አንተ ተፈጥሮኣዊ ወንድነትህን በተንከባከብከብውና በተለማመድከው ቁጥር ራስህን፣ ተፈጥሮህን እየመሰልክ ወንዳወንድ ወንድ እየኾንክ መኼድህ እሙን ነው። 

ለምሳሌ፦ ወንድ በተፈጥሮው ከሴት ይልቅ ከደረቱ ሰፋ ከዳሌው ጠበብ ብሎ ሰውነቱ በአነስተኛ ስብ በጡንቻ የዳበረ አልያም ለመዳበር የተመቸ ነው። ታዲያ አንተ ይኼን ተፈጥሮህን ተቀብለህ ታዳብረዋለህን?

ይኹን እንጂ ውፍረት ካላስቸገረን በሽታንም እስካላስከተለ ድረስ ስፖርት መሥራት፣ ብንሠራም የአንድ ሰሞን ዝላይ ከመኾን አያልፍም። ሰውነትን በጡንቻ መገንባት፣ ጥንካሬን ማዳበር እና ስፖርትን የሁልጊዜ የሕይወት ልምምድ ማድረግ ብዙም አይበረታታም።

አንተስ?

ሳተናው!

ዛሬ ዛሬ የያዙትን ከፍተኛ የትምሕርት ማዕረግ፣ የጨበጡትን ስልጣን፣ ያላቸውንም ተጽዕኖ ፈጣሪነት ተጠቅመው ባገኙት አጋጣሚ ይኽን የትዳር፣ የቤተሰብ፣ የትውልድ፣ የሀገር መሠረት የኾነውን ወንድ  በግልጽ ራሱን፣ ባሕርያቶቹን እና ስልጣኑን የሚቃወሙ መጥተዋል።

ይኽንንም ሲያደርጉ ተራውን ሕዝብ ለማሳመን አስተምረው ካስመረቋቸው ምዕራባውያን የተገለበጡ የሐሰት ጥናት እና ድምዳሜ ይዘው ይቀርባሉ። 

አንተ ግን አስተውል! ወንድነትህ የፈጣሪ ስጦታ ነው። መግራት፣ ማሰልጠን ለተሰጠህ ዓላማ በተፈለገው መጠንም መጠቀም ያንተ ኃላፊነት ነው። በወንድነትህ ውስጥ ባሉ ኃብታት ተጠቅመህ ፍጥረትን ብትበድል ተጠያቂው ባለዕዳው አንተ እንጂ ወንድነትህ አልያም እርሱን የሰጠህ ፈጣሪ አይደለም። 

ተፈጥሮህን ከሚያንቋሽሹት ጋር አብረህ አታጨብጭብ!!! 

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *