ዐላማ ሲኖርህ የመጣህበቱ

ዐላማ ሲኖርህ የመጣህበቱ
ምክንያቱም ተጽፎ በየመጽሐፍቱ
ነፍሴ ነሽ ሕይወቴ በነግህ በሌቱ
ሴቲቱን ማለምህ ይኾናል ስተቱ

የሕይወትህን ዐላማ የመኖርህን ትርጉም በተመለከተ ሌላ ጊዜ በሰፊው እመለስበታለሁ። ለዛሬ ግን ይቺን ያዝ።

፩ የተፈጠርክበትን ምክንያት የተጠራህበትን ዐላማ ለማወቅ ይረዳህ ዘንድ የተሰጡህን ቅዱሳት መጻሕፍት አንብብ(እነርሱ አንተ እንዴትና ለምን እንደተሠራህ የሚያትቱ manual ናቸው)

፪ ራስህን በጥልቁ የሚያስደስትህ ብትሠራው ሐሴትን የሚሰጥህን ፈትሽ

፫ በእነዚህ ውስጥ ከምትቀበለው የምትሰጠው፣ ከምታገኘው የምታካፍለውን፣ ለሚያስፈልጋቸውም የምትለግሰው(ለሀገርህ፣ ለሰው ዘር) ምን ሊኾን እንደሚችል ተረዳ።……

ሚስትህን የሚያስደስተው

ወንድሜ በዋናነት ከላይ የጠቀስኳቸውን ሦስት ነጥቦች ይዘህ ዐላማህንም ሰቅለህ ወደ እርሱ ተጓዝ። ምንም ዐይነት የሕይወት አጋጣሚ ቢያዘገይህ እንኳ እንዲያስቀርህ ዕድል አትስጠው(ሴትም ብትኾን)።

በፍቅር ሰበብ “ለፍቅር ስል፣ ለሚስቴ ስል፣ ከምወደው ሥራ፣ ከምወደው ትምሕርት…. ..” እንዳትጨርሰው። ይኼን ምክንያት አድርገህ ከዓላማህ ፈቀቅ ያልክ እለት ሚስትህ አንተን የምትንቅበት አንተም ክብርህን የምታጣበትን ቀን በይፋ ማስጀመርህን እወቅ። ምክንያትህ ምንም ይኹን ምን ውስጧ የሚረዳህ(የሚያውቅልህ) የዓላማ ጽናት እንደሌለህ ነው።

የሕይወትህ ዐላማ በምንም የማትቀይረው፣ የማትደራደርበት ሲኾን የምትወዳት ታከብርሃለች። የሕይወትህ ዐላማ በ”ፍቅር” ሲሸነፍ ምን ያክል ደካማ፣ ጽናትየለሽም እንደኾንክ ታሳብቃለህ። ልትደገፍህ የማትችል ድኩም ስትኾን ደግሞ ትንቅሃለች። አንተ “ወድጄሻለሁ” ብለህ ትነፋረቃለህ እርሷ ደግሞ ላይኗ ትጠየፍሃለች። ብዙዎች የተጠሩበትን ዐላማ ገፍተው(ትተው) ሴት አሳደው ያተረፉት ነገር ቢኖር በተራቸው መገፋትን፣መናቅን ነው፤ ታሪክን የኋሊት ዘክር።

ወዳጄ ሚስትህ የምታከብርህ፣ ሚስትህ የምታደንቅህ፣ ሚስትህ ካንተ ጋር ረጅም የፍቅር ዘመናትን ለማሳለፍ ራሷን አሳልፋ የምትሰጥህ ግልጽ የኑሮ ዐላማና ካ’ለት የጠጠረ ጽናትም ሲኖርህ ነው። “አመልክሻለሁ፣ አፈቅርሻለሁ፣ ካላንቺ መኖር አልችልም፣ እሞትብሻለሁ፣ ጉዳዬ…..ነሽ።” እነዚህ ኹሉ አንድ ሰሞን ገላዋን(ወሲብ) ቢያስገኙልህ እንጂ ልቧን አይማርኩልህም። ምን አለፋህ ት….ን…..ቅ…..ሃ…..ለ……ች።

እኚህን በልብ መዝግብ
፩ ሚስትህ ኖረችም አልኖረችም፣ መጣችም ቀረችም የማትቀይረው የምትኖርለት ዐላማ ይኑርህ፤ ይኽ ዐላማ ግን እርሷ አትሁን።

፪ ለዚህም ዐላማህ ጽናት ይኑርህ

፫ ራስህን ገዝተህ ሚስትህን ቤትህን ምራ

፬ የተሰጠህን ክብር ጠብቅ

፭ ክብርህን አስጠብቅ፦ ሴት ልጅ ክብሩን ጠብቆ የሚያስጠብቅ ወንድ ይማርካታል

፮ ቃልህን አክብር፦ ለትንሽ ትልቁ ቃል አትግባ፤ ከገባህ ጠብቀው። የተናገሩት ከሚጠፋ…

፯ ቃልህን(ትዕዛዝህን) አስከብር፦ ሲያሻት የምትክበው አልያም የምትንደው አይኹን

፰ ነገርህን ግልጽ አድርገህ አስቀምጥ። ከወገብህ ጎብጠህ፣ አንገትህን ደፍተህ በትኅትና ሳይኾን ከደረትህ ነፋ ከአንገትህ ቀና ብለህ ዐይኗን እያየህ በልዕልና በንጉሳዊ ሞገስ ይኹን።
፱ ያለከውን እርሱን እንጂ ካልከው ያነሰ የምትወስድ ምስኪን፣ የምታደርግ ድኩም፣የምትረሳም ዝንጉዕ አትኹን።

፲ ለታዛዥነቷ ሙገሳህ ለእምቢተኝነቷ ደግሞ ወቀሳህ(ቁጣህ) እንደ ስኳርና ጨው ናቸው(ኹለቱም ቢያጣፍጡ በልክ፤ አገባባቸውም ለየቅል ነው)። ትኅትናዋን በፍቅር መግቦት ካልካስከው ግርድና ኾኖ እንዳያሳዝናት፤ ትዕቢቷን በተግሳጽህ ካልገረዝከው (ባትነግርህም “ባይወደኝ እንጂ” ብላ) እንዳትጠፋ ካንተ አይለዩ።

ብንኖር ……ለንጉሱ(ለአባወራው) ሚስት ማን ትኹን?….. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *