ዓለም አባወራነትህን አትወደውምና አታግዝህም

ሳተናው!

ዓለም ወንዶችን አልጫ፣ ምስኪን እና ሴታውል ብታደርግ እንጂ ርዕይ ያላቸው፣ ዓላማን የሰቀሉ፣ ጸጋቸውን የተረዱ፣ ሚናቸውን የለዩ፣ ኃሳባቸው ከቃላቸው ቃላቸውም ከግብራቸው የተስማማላቸው፣ ትዳራቸውን (ቤታቸውን) በመምራት ሀገር ተረካቢ ትውልድን የሚያፈሩ አባወራዎች አድርጋ አትሠራም።

ዛሬ ዛሬ በዓለም ላይ ባሉ አብዛኞቹ ተቋማት(መንፈሳዊ፣ መንግስታዊ፣ ማሕበራዊ፦ ትዳርን ጨምሮ) ውስጥ ስንፍና እየተበረታታ፣ ሴታውልነት እየተሞገሰ፣ አፈ-ቅቤነት እያስወደደ፣ ውሸት እያስከበረ፣ ነፃነት እየተምታታ፣ እኩልነት እየተጭበረበረ፣ መብትም ቦታውን እየሳተ፣ በመንጋ ማሰብ መሥራትና መሸለም ግድ ሲባል ይስተዋላል።

በተቃራኒው ደግሞ ቆራጥነት እያስናቀ፣ ጀግንነት እያስነቀፈ፣ ሥነ-ስርዓት ዋጋ ቢስ እየተደረገ፣ ልዩነት እየተወገዘ፣ ግለሰባዊነት እየተነቀፈ፣ የጾታ ድንበር እየፈረሰ፣ ባልነትና ሚስትነት ጣዕም እያጣ፣ አባትነትና እናትነት በፈረቃ እየኾነ ኑሮኣችን ከድጥ ወደ ማጥ ኾኗል።

ሳተናው!
ቁምነገሩ ዓለም አባወራነትህን አታግዝህም ነው! እውነትን እየተገለጠችልህ አንተም በእርሷ መኖር ስትጀምር ጉዞህ የብቸኝነት ይኾናል።

ይኹን እንጂ ብዙኃኑ ወደ ‘ሚነዱበት የቅዠት ዓለም ከቶም ልታመራ አይገባም። ይልቁንስ ሐቁን ሲረዱትና ሲኖሩት ከሚገፉት ጋር ተወዳጅተህ ራስህን፣ ትዳርህን፣ ትውልድህንና ሀገርህን ከጥፋት ታደግ።

ዓለም ለሴቶች ጠበቃ የኾነች በማስመሰል ከምንግዜውም በበለጠ እና በከፋ ኹኔታ ፈጣሪ የመሠረተው ተቋም፦ ትዳር ላይ ከፍተኛ የጥፋት ዘመቻ ከፍታለች።

ከዚህም የተነሳ የአንተ የተፈጠርክበትን ዓላማ፣ የተለየልህን ሚና እና የተሰጠህንም ጸጋ ተረድቶ በልበሙሉነት መመላለስ ሌሎችንም ማንቃት ይረብሻታልና ብታገልህ፣ ብትገፋህ አልፎተርፎም ብታሳድድህ እንጂ አታግዝህም።

ሳተናው!
ከዚህች ዓለም ገፊነት ተስፋ አስቆራጭ ፈተናም የተነሳ ወንዱ ዓላማውን እንዳያውቅ እንዳይኖርውም፣ የኑሮ ልክ እንዳይኖረውና በቆራጥ አቋምም እንዳይጸና ስንፍናንና ፍርሃትን በስልጣኔና በመንፈሳዊነት ስም ይጋታል።

ይህንንም ሥራ መገናኛ ብዙኃኑ በተሳካ ኹኔታ ያቀላጥፉታል። በስተመጨረሻም ፈሪ፣ ሰነፍ፣ ክብሩን ማስጠበቅ የማይችል ባጣቆይ ትውልድ ይገኛል።

ባጣቆየኝ፣ ባጣቆይ፣ ባጤ……

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *