ዘውድ ድፋ ስትባል አታደግድግ

!

ሳተናው!

************************************
እንዲህ ነገሩን በብልት በብልት ከፍዬ፣ በተለያየ አቀራረብ የማጫውትህ ያለፍኩበት ከውድቀቴም የተማርኩበት ስለኾነ ነው።

የእኔ ስንፍናም ኾነ ስሕተት አንተን ቢያስተምርህ ብዬ ጻፍኩልህ እንጂ ጊዜህን እና ገንዘብህን የምታጠፋበት መዘበቻ እንዲኾንህ አይደለም።

ዓላማ፣ ርዕይም አለህ ብዬ አምናለሁና በምለጥፋቸው ጦማሮች ምቾት ካልተሰማህ በገጼ ላይ ጊዜህን አታጥፋ። ዘወትር እንደምነግርህ ልምዴን ላካፍል በተለይም ስሕተቴን እንዳትደግም ከእርሱም የተማርኩትን ልሰጥህ እንጂ አጨብጫቢም ኾነ ተከታይ ለማብዛት አልመጣሁም።

*************************************

ሳተናው!

ሴት ልጅ “የትዳር ጓደኛ”፣ “የኑሮ አጋዥ፣ ረዳት”፣ አጋር” ትፈልጋለች ሲባል እውነት ይመስላል፤ አንተም እንዲሁ ለመኾን ትዳክራለህ።

እኔ ግን እልሃለሁ ይኽ ፍጹም ከእውነት የራቀ ስለመኾኑ እመሰክርልሃለሁ። ይኼ በዘፈኑ፣ በፊልሙ፣ በቴያትሩ፣ በመጽሓፍት፣ በትምሕርት ጋጋታ ከምዕራባውያን የተጋባብን ውሸት ነው።

ሴት ልጅ ከምንም እና ከማንም በላይ ልቧን የሚገዛ፣ ስሜቶቿን የሚያግድ፣ በፍላጎቶቿም የሚወስን፣ እረፍት ወደብም ለሚኾናት ወንድ (“ንጉስ”) ትማረካለች።

ይኽንንም አስባበት ቁጭም ብላ አሰላስላው ሳይኾን ተፈጥሮኣዊ፣ ደመነፍሳዊ ኤና ውስጣዊ ጥያቄዋ ነው።
አንተ ስላዝናናሃት፣ ከምትፈልገውም ስላላጎደልክባት፣ ብዙ ውለታም ስለዋልክላት፣ በጋራም ልጆች ስላፈራችሁም ልቧን ሰጥታሃለች ማለትአይደለም።

“ወዳኛለች እኮ፣ እንነፋፈቃለን እኮ፣ ታስብልኛለች እኮ፣ ታግዘኛለች እኮ፣ ትጠይቀኛለች እኮ…..” እያልክ አትዘርዝር።

ይልቁንስ “ታከብረኛለች ወይ?” ብለህ ራስህን ጠይቅ።

====================================
የተለመደ የወንዶች ስሕተት
ስሕተት አንድ፦ ወንዶች በተለይም ምስኪን ወንዶች ውዴታ፣ ምስጋና፣ ሙገሳ ከሴት በተለይም ከሚወዷት ሲበዛላቸው የመፈቃቀዳቸው ምልክት አድርገው ይቆጥሩታል።

ስሕተት ሁለት፦ ወንዶች በተለይም ምስኪን ወንዶች መከበርን በሕይወት መንገድ ላይ በኺደት በጥረታቸውም የሚያመጡት ይመስላቸዋል(ከንቱ ልፋት)።

ሳተናው!

👌ከመከበርህ ይልቅ መወደድህ እያየለ ሲመጣ አንተ የኑሮዋ ሸሪክ፣ የዚኽች ዐለም የትግል አጋሯ መኾንህን አረጋግጥ።

👌 ከመወደድህ ይልቅ መከበርህ ሲያይል ልቧ ያንተ ግዛት እንደኾነ ተረዳ። ልብ አድርግ! በትውውቃችሁ መጀመሪያ ሰሞን ካልተከበርክ ብዙ ብር በማፍሰስም ኾነ ውለታ በመዋል አታመጣውም።


ከእነዚህ ሁለት መሠረታዊ ስሕተቶች የተነሳ ብዙውን ጊዜ የዛሬ ወንድ ለሚስቱ ራሱን እና ስሜቶቹን የገዛ ለእርሷም የተረፈ ንጉስ ከመኾን ይልቅ አደግዳጊ ነው።

እንደ ማደግድጉም ትዳሩ ከይፋዊ ፍቺ ቢርቅ “በብዙ ጥረት፣ ብልሃትም ትዳሬን አቆየሁት” ይላል።

👉 እውነታው ግን በቤቱ፣ በልጆቹም ፊት ሞገስ የሌለው፣ የማይከበር ነው።

👉 በሚስቱ ልብም የተናቀ የቁሳዊ ኑሮኣቸውን ጉድለት ለመሙላት የተጎዳኘ ወዳጅ ነው።

👉ከእርሷም ጋር በምንጣፋቸው ተለማማጭ፣ ጉጉ(የሚጓጓ) ነገር ግን የማያሳርፍ፣ የተለመደውን አሰልቺ ተራክቦ ከመፈጸምም ውጪ የማይናፈቅ ነው።

ሳተናው!

ለንጉስነት ስትፈለግ ላገልጋይነት አታደግድግ የተመኘኸውን ቦታህን ሰጥታህ ንጉሷን ፍለጋ ትኼዳለችና።

ምስኪን ያለሚናው ገብቶ ሚናውን ላወቀ ወንድ ሚስቱ ልቧን ስትሰጥ ኃሜታ ይጀምራል። ወንድሜ ለሴት ልጅ ምክንያተኝነት፣ ትምሕርት፣ ስልጣኔ፣ መንፈሳዊነት ቦታ የላቸውም ስሜቷን የሚገዛ ልቧን የሚያሸንፍ እንጂ።

ከዚኽም የተነሳ ብዙ ሴቶች(እጅግ ብዙ) ጨዋ፣ መንፈሳዊ፣ የተማረ፣ ረዳት…. የተባለ ባላቸውን ከፈለገው ያገልጋይነት ቦታ(ከቤት) አስቀምጠው በምግባሩም ኾነ በስርዓቱ ከተናቀ ዱርዬ ጋር ይወሰልታሉ።

ልብ አድርግ! ማሕበረሰቡን፣ ጓደኞቿን፣ ቤተሰቦቿን ፈርታ እንጂ ልቧንስ የሚገዛው ይኽ “ዱርዬ” ነው። እንዴት አትለኝም?

1ኛ የራሱን ቦታ በሚገባ ያውቃል፦ ልወደድ ብሎ አያደገድግም፣ ልመረጥ ብሎ አይለማመጥም

2ኛ የራሱን ቦታ ያውቃልና እርሷንም በቦታዋ ይሰይማታል፦ ይኽንንም ለማድረግ ስብሰባ አይጠራትም

እንደ እኔ እና እንዳንተ ያለው ምስኪን ግን ቦታውን ባለማወቁ በሚደርስበት ንቀትና መገለል ቢጤውን ሰብስቦ ሴቱን ያማል(ኃሜት)።


ሳተናው! ንሳ ንግስና(ራስህን ገዝተህ ሚስትህን የራስህ የምታደርግበት) ገንዘብህ ነው። እርሱን የናቅክ ዕለት ሚስት አንተን መናቅ የምትጀምርበት ዕለት እንደኾነ አስተውል።

…ይቆየን
Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

2 Responses

  1. Firew says:

    በርታ ወንድሜ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *