“ዛሬ ዓለም “ትክክል” የምትልህ ስሕተቶች ክፍል፫

ሳተናው!

፮ኛ ለወሲብ ስታስፈቅዳት ትንቅሃለች
ሳተናው ትዳር ስትይዝ ወይም ለመያዝ ስታስብ ልብህ የመረጣትን ሴት መጠየቅ የእርሷን ፈቃድ ስታገኝ ደግሞ አባቷን ማስፈቀድ ወግ ነው። ይኼን አስቀድመህ ብትተኛት “አስነወራት” አትባልም ምክንያቱም ፈቃዷን አግኝተሃልና።

አንድ ጊዜ ያገኘከውን ፈቃድ ደግሞ ደግመህ ደጋግመህ በመጠየቅህ ብትከለክለው እንጂ የፍቅር መግለጫ የፈቃድ መጠየቂያ ኾኖ አያገለግልህም/ አያተርፍህም።

በተቻለህ መጠን እርሷን ወደተሻለ ስሜት ማምጣት እንጂ ማስፈቀድ ጭርሱን ስሜቷን የሚያሳጣ ፍላጎቷንም የሚዘጋ ነው። ማስፈቀድህ ትሕትናህን፣ ዘመናዊነትህን ሳይኾን የሚያሳየው ለምን እንዳገባሃትና ምን ልታደርግ እንዳገባሃት አለማወቅህን ሲኾን እርሷም የምትረዳው ይኼንኑ ነው፤ ደግሞ “ነው እንዴ?” ብለህ ጠይቃት አሉ።

በተለይም ትልቁ የምስኪን ወንዶች ስሕተት ሴትን ከወንድ ያነሰ የወሲብ ፍላጎት ያላት አድርጎ መቁጠርና ይልቁንም ከወለደች በኋላ ይኸው ፍላጎቷ እንደሚያሽቆለቁል የተሳሳተ ግንዛቤ መያዛቸው ነው። ከዚህ የተሳሳተ ግንዛባቸው ተነስተውም ይጠይቃሉ።

ሳተናው!
“ወንድ ሴትን ይጠይቃል”።፣ “ወንድ ሴትን ቢጠይቅ ወግ ነው” ሲባል ከላይ የጠቀስኩልህን ከጋብቻቸው በፊት የእርሷንም ቢሉ የአባቷን ፈቃድ መጠየቁን ሲያጠይቅ(ሲያስረዳ) እንጂ የእርሱ ከኾነች በኋላ መጠየቅ ኖሮበት አለመኾኑን ልብ በል።

ጥያቄ አንዴ ይፈጸማል፤ እርሱም ተጠያቂዋንና ቤተሰቧን ያከበረ እርሱንም ያስከበረ ነበር። ከዚህ በኋላ ግን ቢጠይቅ በሴቷ ዘንድ በሕቡዕ (በድብቅ) ቢያስንቀው እንጂ አያስከብረውም።

፯ኛ ኢ-ስነስርዓታዊም ኾነ ኢ-ስነምግባራዊ ድርጊቶቿን ስታልፋቸው ትንቅሃለች

ሳተናው!
ላንተ የፍቅር መግለጫ መስሎ ይሰማህ ይኾናል ነገር ግን ምኪንን ሚስቱ ከምትንቅባቸው ጠባዮቹ አንዱ እርሷ ከስሜቶቿ መለዋወጥ የተነሳ መቆጣጠር ያልቻለቻቸውን ድክመቶች ማለፉ ነው።

ይኹንና ደመነፍሷ የሚነግራት አንተ ራስህ የምትኖርበት የምትመራበት ስርዓት የሌለህ ከዚኽም የተነሳ ትዳርህን፣ ቤትህን፣ ልጆችህን እርሷንም ከስሕተት መታደግ/መመለስ የማትችል የማትፈልግም አድርጋ ታስብሃለች።

አንተ የቤትህ ስነስርዓት አውጪ አስፈጻሚ እና አስተማሪም ነህ። ከሚስትህ ጀምሮ ልጆችህም ኾኑ ሌሎች በቤትህ የሚኖሩ ሰዎች ይኽን የቤትህን ስርዓት ሊጠብቁ፣ ባስተማርካቸው ስነምግባርም ሊገኙ ይገባቸዋል። ይኽንንም ያለምንም ይሉኝታና ድርድር ማስጠበቅ ይገባሃል።

በቤትህ ውስጥ ካሉት ኹሉ በቅድሚያና በዋነኛነት ባንተ የሕይወት መቃን ውስጥ ማለፍ ያለባት እና በመኖርም፣ በመታዘዝና በመፈጸምም ያንተን መሪነት ለሌሎች (በተለይም ለልጆች) የምታስተምርበት እርሷ ናት። ወንድሜ ሚስትህ ያንተን ሰርዓት ንቃ ለጆችህ አያከብሩትም።

ስለኾነም አንተ ባስቀመጥክላት የስርዓት መቃን ማለፍ ካልፈለገች ልጆችህንም ኾነ ሌላውን እንዲያልፉበት አታበረታታም። አንተ በምትመራው ቤት ከከባቢህ ከልለህ ባጠርከውም አጥር ሚስትህ ልጆችህን አስከትላ መጥታ በቀረጽከው መቃን የማይገቡ ከኾነ በአጥር የሚንጠላጠሉ፣ በመስኮት የሚዘሉ ስርዓት አልበኞች መኾናቸው የማይቀር ነው።

ልብ አድርግ! ኢ-ስነስርዓታዊ እና ኢ-ስነምግባራዊ ንግግሮቿንም ኾነ ድርጊቶቿን እንደማትታገሰው ኹሉ ለመልካሞቹ ግን አሞግሳት። አስተውል ግን ለመልካሞቹ ነው ያልኩህ ሚስትህ በሰውነት እኩያህ መኾኗን አትርሳ መልካም ስትሠራ ካንተ በላይ ፣ ስትስት ካንተ በታች አይደለችም አንተም እንዲሁ ነህና።

ስለዚህም ጥሩም ኾነ መጥፎ ብትሠራ በጅምላ የምትመሰገን አልያም የምትወቀስ አይደለችም። እንደስርዓትህ ስትሄድ ልትመሰገን ከስርዓትህም ስትወጣ ደግሞ ልትገሰጽ ይገባታል። በትዳርህ በቤትህ ይኼንን የማድረግ ስልጣኑም ኾነ ኃላፊነቱ ያንተ ነው።

መልካም እድል… .. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *