ዛሬ ዓለም “ትክክል” የምትልህ ስሕተቶች ክፍል-፪

ሳተናው!

ባለፈው ሳምንት ዓለም “ልክ” አልያም “ተገቢ” አድርጋ ከምትነግርህ እና አንተም ከምትከተላቸው ሰባት ስሕተቶች ውስጥ ሁለቱን አይተናል ዛሬ ደግሞ ሦስቱን አይተን በመጪው ሳምንት ደግሞ ቀሪዎቹን ሁለቱን እናያለን።

፫ኛ ካለ እርሷ መኖር እንደማትችል ስትነግራት ስታውቀውም

በአመንዝራዋ ዓለም ዘፈን ተወስደህ ፍቅርህን የገለጽክ ያስወደደህም መስሎህ ሚስትህን “ካላንቺ መኖር አልችልም” ስትላት በአፏ ባትነግርህም  ትንቅሃለች። አስተውል አንተ ሚስትህን ልትጠብቃት (ልትንከባከባት) ወጥተህ ወርደህ የሚያስፈልጋትን ልታቀርብላት እንዲሁም ትውልድ የሚቀጥልበትን ዘር ልትሰጣትና በፍላጎቶቿ ላይም ልትወስን ሲገባህ ሚናህም እንደኾነ መረዳት አለብህ። 

የምትኖርበት ምክንያት እርሷ አይደለችም። ይኼን ደግሞ ስትሰማው ደስ ቢላትም ደመነፍሷ ግን መነሻህን፣ ዛሬ ያለህበትን እና መድረሻህን የማታውቅ መኾንክን ይነግራታል።

መስኪን ሠላሳ ዓመት ሙሉ ካለ እርሷ ኖሮ በሠላሳ አንደኛው ዓመቱ ቢያገኛት “ካላንቺ አልኖርም” ይላል፤ ብትንቀውስ ይገርማል?

፬ኛ እርሷን ካንተ ስታስቀድማት

ሳተናው!
ያንተ ተፈጥሮ ከፊት ኾነህ እርሷን እንድትመራ እርሱንም በኃላፊነት ልትፈጽም የታዘዝህ ነህ። ሚስትህ ደግሞ ልትከተልህ፣ ልትታዘዝህ እና ልታግዝህ የተፈጠረች በዚህም እንድትኖር የታዘዘች ናት። 

ስለዚህ አንድም ተፈጥሮህ ወዲህም ትዕዛዝ ነውና ያንተ ከፊት መቅደም(ራስህን ማስቀደም) በምስኪኑ አእምሮህ እንደምታስበው ራስ ወዳድነት ሳይኾን ከተፈጥሮህ ጋር ስምም መኾን ትዕዛዝንም መጠበቅ እንጂ።

ከማሕበራዊ ሕይወት ጀምረህ፣ ከእልፍኝህ ተግባራችሁ እስከ መኝታቤት ወሲባዊ ተራክቧችሁ ቀዳሚው፣ መሪው፣ ቀስቃሹ አንተ ነህ። አንተ ስትቀድም ብቻ እርሷ ልከኛ ተከታይ ግጣምም ትኾናለች።

አልያ ግን እርሷን ከፊት ከፊት ማድረግ ወግ መስሎህ፣ ስለአንተም ኾነ ፍላጎቶችህ ስትናገር ስልጣኔ አድርገህ፣ ካንተ የሕይወት ዓላማም እርሷን ማስበልጠህ፣ ለተራክቦኣችሁም እርሷን ማስቀደምህ ላንተ መዘመን ሲመስልህ እርሷ ግን ትንቅሃለች።

ያስወድደኛል ባልከው ትናቃለህ! ራስወዳድነት ራስህን ማስቀደም ሳይኾን ያለማቋረጥ ስለራስህ ማሰብና ማውራት እንጂ! 

ትዳርህን የምትመራው አንተ ስትቀድም ብቻ ነው!!!

፭ኛ ሁል ጊዜ እሺ ስትላት 

ሳተናው!

“አይኾንም” ማለት ምን ያክል ታላቅ ሥራን መስራት የሚችል ከፍተኛም አቅም ያለው ቃል እንደኾነ እስካልተለማመድከው ድረስ አታውቀውም። ስትደርስበት ግን እሺ ያልክባቸውን ትረግማለህ።

ዓለም ለሰዎች መልካም እንድንኾን ስትነግረን መልካምነታችን ግን ስለሚይዘው ጥግ ወይም ገደብ አትነግረንም። አልያም ለመልካምነታችን ገደብ መኖሩ በራሱ ክፋት ራስ ወዳድነት ለሰዎች አለማዘን አድርጋ ትነግረናለች።

ከዚህም የተነሳ ሚስትህን የማይኾነውን በግልጽ አይኾንም ማለት፣ በእርሱም መጽናትና እርሱንም ማስፈጸም ይሳንሃል።

አይኾንም ስትል ጥላቻን ያሳየህ ፍቅርን የገፋህ ክፉ የኾንክ ይመስልሃል። አይነውሃዋን እያየህም አይኾንም ማለት ሲከብድህ ቢወጣህም እንኳ በቅጽበት ይጸጽትሃል። ካለቀሰችብህማ ወደ ቀደመው”አፍቃሪ”ነትህ ትመልስህ ዘንድ እግሯ ላይ ወድቀህ ትለምናታለህ።

እውነቱ ግን ከዚህ የራቀ በጣምም የሚገርም ሊያናድድህም የሚችል ነው። እርሱም ምን መሰለህ ሴት ልጅ በቅጽበት ለሚለዋወጠው ስሜቷና ፍላጎቷ “አይኾንም” ስትላት ብቻ አንተን ማክበሯ ነው። 

እርሷ ራሷ ለመረዳት ከምትችለው በላይ ግን መቀበል ባትፈልገውም ልክነቱ ሲሰማት ጥልቅ ወሲባዊ ዝንባሌም ያሳድርባታል። ግራ ሊያጋባህ ይችላል ግን ይኼ የእኔ ቃል ቢኾንም የእርሷ ስሜት እንዲህ ስለኾነ ብቻ ነው።

ለእርሷ በምርጫዎቿ፣ በፍላጎቶቿ፣ በውሳኔዎች ላይ “አስቀይማታለሁ አላስቀይማትም” ሳትል ስትወስን ቆራጥ አቋም ያለው አባወራ በመኾንህ ታከብርሃለች።

ምስኪን ግን “ልወደድ” ባይ ነውና አንድም “ያስወድደኛል” ባይ ነውና፣ አንድም ደግሞ “እወደድ ዘንድ” ሲል “አይኾንም” ወይም “እምቢ” ማለት ዳገቱ ነው። ይኹን እንጂ ራሱን ችሎ መቆም እስኪያቅተው ጊዜውን፣ ገንዘቡን፣ ጤናዉን… አሟጦ ይጨርሳል፤ ውስጡ የሚቀረውም ንዴት፣ ብስጭት፣ ድብርት ይኾንና ወይ በልብ ውጋት(stroke) አልያም በራሱ እጅ ይጠፋል።

ReplyForward

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

2 Responses

  1. Firew says:

    Good job keep it up

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *