የሕግ ትምክሕት ይቅር

ክፍል ፩

ፍርድ የጠየቅነው ወንጀለኞችን ለመበቀል ወይስ ለፍትሕ

ሳተናው!
የመገናኛ ብዙኃኖቻችን ትውልዱ ስሜታዊ መኾኑን በደንብ አውቀውታል። ስለዚህም ራሱ የሚለወጥበትንና ሀገሩን የሚለውጥበትን ዶክመንተሪ ከመሥራት ይልቅ ልቡን የሚገዛላቸውን፣ ስሜቱን የሚኮረኩርላቸውን እና አጀንዳ የሚሰጥላቸውን ርዕስ እየፈለጉ ያቀርቡለታል።

የቀረበው ነገር እውነት ቢኾን እንኳ የሚቀርብበት መንገድ ፍትሕን ሳይኾን ፍርድን ፍለጋ ነው። ፍርድ ደግሞ ያጠፋን ቢቀጣ እንጂ ሰዎችን እንዳያጠፉ አያስተምርም።

ፍርድ ነገ የሚመጣውን ትውልድ ከተመሳሳይ አጥቂነትም ኾነ ተጠቂነት አይጠብቅም፤ ትውልድንም በተገቢው መልክ አያንጽም። ለዚህ ደግሞ ምሳሌ ከእኛ የተሻለ የሕግ ስርዓት ያላቸውን ሀገሮች ማየት ይቻላል።

ነገር ግን ብዙዎቻችን “ፍርድ!” እያልን እንጮሃለን ልክ ብለናል። እንዴት? እኛ ራሳችን ወንጀለኞች እንደኾንን ልቦናችን ያውቀዋልና። ወንጀለኛ ሕሊናው ስለሚከሰው በእርሱ ዓይነት ወንጀል ሌላውን ሲያገኝ ሕጉ በሚፈቅድለት ሁሉ ዱላውን ያሳርፍበታል።

“እኛ ምን ሠርተን ነው ወንጀለኛ የምንባለው?”….

ሕግ ይኼን ያህል አያስመካም

ከላይ እንደጠቀስኩት ወንጀለኛ መኾናችንን ኅሊናችን ያውቀዋልና ወንጀለኛውን እኛን የቀጣነው ይመስል የኛ ቢጤ ወንጀለኛ ላይ ዱላ እናበዛለን።

ከዚህም የተነሳ ፈጣሪያችን በፍቅር ከሰጠን ስርዓት ይልቅ(እርሷን መፈጸም ከብዶን) የእኛን “አግዘው፣ ፍለጠው፣ ቁረጠው፣…” ሕግ እናጠነክራለን፤ በእርሱም እንመካለን።

የትኛውን የፈጣሪ ትዕዛዝ አፈረስን?
?ምነው አንተ በቤትህ ራስነትን ተሹመህ ቤትህን(ሚስትህን) ልትመራ፣ ልታስተዳድር፣ ራስህን አሳልፈህም በመስጠት ልትወዳት እንዲገባ የፍቅር ስርዓት አልተሠራልህምን?

? ምነው ልጆችህን በአርጩሜ እስከመግረፍ በደረሰ ተግሳጽ በልጅነታቸው በሕግና በስርዓት ልትመራቸው እንዲገባህ አታውቅምን?

? ምነው አንቺስ ባልሽን ልትታዘዢው፣ በስርዓቱም እንድትሄጂና በዚህም ለልጆችሽ አርኣያ እንድትኾኚላቸው አልተማርሽንምን?

እንግዲህ የፈጣሪህ ቃል እንዲህ እያለ አንተ ግን ያደረግከው ሁሉ እርሱ የማይከብርበት ነበርና፣ ራስህን ከእርሱ በላይ “አዋቂ”፣ “የፍቅርም ሰው” አድርገህ የሁለቱን ጾታዎች ሚና ደበላልቀሃልና፣ የራስህንም ክብርና ዝና ፈልገሃልና ወንጀለኛ ነህ(አንቺም ብትኾኝ)።

የወንጀለኛ ልዩ መለያው ደግሞ ቀላሉን የፍቅር ሕግ አልፈጽምም ብሎ ከባዱ ተግባራዊ እንዲኾንበት መማጸኑ ነው።

ሳተናው!
የምንሰማውን ክፉ ሥራ በፍርድቤት ቅጣት አናስቀረውም። መፍትሔውንም የምናገኘው ከፍርድ ቤት ሳይኾን ከእኛው ከራሳችን ዘንድ ነው። ከፍርድ ቤቶች ፍርድ ቢሰጥ እንጂ ፍትሕ አይገኝም። ፍርድ ቤቶች ያጠፋ ቢቀጣባቸው እንጂ የተወለደ አያድግባቸውም።

ነገ ይኼን የመሰለ አስነዋሪ ድርጊት ልጆችህ እንዳይደግሙ ከፈለግህ ይኼንን አምጥተህ የለጠፍከውን የምዕራባውያን የ”እኩልነት” እና የ”ስልጣኔ” ድሪቶ አርቅና ተፈጥሮኣዊ ማንነታቸውን በጠበቀ ስርዓት አሳድጋቸው።

ሕግ ማጠንከር፣ማብዛትና በእርሱም መመካት የኦሪታውያን ትምክሕት ቢኾን እንጂ በተለይ ለእኔና ለእንዳንተ ዓይነቱ ክርስቲያን ፍጹም አይመጥነንም።
እምቢ ካልክ ግን ኺድና ሞክረው ወንድነትን የሚጠየፉ፣ ገንዘብ ከፍለው ወሸላቸውን የሚያስቆርጡ፣ ወንዶችን ማሳደግህ አይቀርም፦ ከምዕራባውያን ተማር።

ከዚህ ይልቅ ግን ሁሉን የሚጠብቀውን፣ በተፈጥሮኣችን አይለን በልጽገን ወደ ተፈጠርንለት ዓላማ የሚያደርሰንን ስርዓት አትከተለምን?
❤ ራስህን ግዛ፣ ራርህን ምራ
❤❤ ሚስትህንና ቤትህን ምራ
❤❤❤ ሚስትህንም ኾነ ልጆችህን በስርዓትና ምራ፣ በምግባርም አሳድግ።

አንቺም ራስሽ ከተጠያቂነት የማታመልጪበትን ሕግ “ካልጸደቀ” አትበይ። መጀመሪያ ግዴታሽን ተወጪ ለመኾኑ ለልጆችሽ የስርዓትና የምግባር አርኣያ ኾነሻቸዋል፣ ለትኅትና ምሳሌስ ትኾኛለሽን? ለባልሽ፣ ለአባታቸውም በትኅትና ተገዝተሻልን?

ካልኾነ ግን ከንቱ ደከምሽ። ከዚኽች ከቀላሏ ሕግ ይልቅ ዓለም ቃል ስለገባችልሽ “እኩልነት”(ትዕቢት) በልጦብሽ ልጆችሽ ተጣመው ካደጉ በኋላ በሕግ ምሳር መቁረጥ ያርማቸዋልን?

አጣመሽ ያሳደግሻቸውን ልጆችሽን በሕግ “ትፈለጣላችሁ ትቆረጣላችሁ” ማለት ፍትሓዊ ነውን? ወይስ ራስሽን ከክስ ለማራቅ ማምለጫ የስርቆሽ በርሽ ናት? አልያም ደግሞ ሁላችንም ወንጀለኛን ሰው ብቀላና ፍትሕ ማስፈን ተምታቶብናል።

ክፍል ፪….. ይቀጥላል
https://t.me/abawera

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *