የሚስት ታዛዥነት

ይኼ እንደ ርዕስ ውይይት ብናደርግበትም ለእኛ የአባቷ ልጅ ስለኾነችውና ቃልህን ስለምትጠብቀው ልጅ ላወራነው ግን በተዘዋዋሪነት የተዳሰሰ ከቀደሙትም ጋር የተሰናሰለ ጭብጥ ነው።
አባወራ ሚስቱ ወይም ለሚስትነት ያሰባት ሴት ታዛዡ ናት። ይኼ ተፈጥሮአዊ የኾነ እውነት መለኮታዊ በሆነ ትዕዛዝ ተተይቦ ተሰጥቶናል። ማስተዋል ለምንሻው የየራሳችንን ተፈጥሮ ልብ ማለት ብቻ በቂ ነው።ይኽ ለከበደንና ካልተጻፈልን ለምንለው ግን ሠሪያችን ለምን ዓላማ እንደሠራንና ያንን ዓላማም ለማሳካት ያለንን ጾታዊ ሚና በመመሪያ(manual) ጽፎልናል(አጽፎልናል) እናም እርሱን መመልከት እንችላለን። አልያ ግን እንደ እንሰሳ በስሜት የምንነዳ ወይም መስማት ያለብንን ሳይሆን መስማት የምንፈልገውን ብቻ የምንሰማ ለራሳችን እንኳ የማንበጅ ነገር ግን ራስ ወዳዶች እንሆናለን።
ልጄ፣ ወንድሜ፣ ወዳጄ የሚስትህ እሺታ ላንተ ከሺዎች ጭብጨባ፣ ከእልፍ ሽልማት፣ ከአእላፋትም ስኬት፣ የበለጠ ብርታትን የሚሰጥህ ነው። የትኛውም ምግብ የትኛውም መጠጥ እንደ ሚስትህ ከአፍአ ያልሆነ ከልብ የመነጨ እሺታ ቤትህን ለመለወጥ ራስህን ወደ ስኬት ማማ ለመስቀል ጉልበት የለውም። በተቃራኒው ደግሞ የሚስትህ እምቢተኝነት አንተን ለማድከም፣ወንድነትህንም ለመናድ የመሥራት፣ የመለወጥ፣ የመምራትና ለሚስትህ ወንዳወንድ ባል የመኾን ወኔህን የመስለብ አቅም አለው። ስለዚህም አንተ ያላገባኸው ታዛዥነትን ከአባት እናቷ ቤት የለመደችውን እጫት። ያገባኸው ደግሞ በኺደትም ቢኾን ታዛዥነትን አለማምዳት ምንም እንኳ ታዛዥ ሚስት እንዳገባው ኺደቱ ቀላል ባይኾንም ውጤቱ ግን በቃላት የማይገለጽ
የሚስት ታዛዥነትን ስናነሳ ታዛዥነቷ ለአባወራው ነውና በውስጠ ታዋቂነት የእርሱ አዛዥነት አለ። አዛዥ ያልኾነ አባወራ ታዛዥ ሚስት አለችው ማለት አንችልም። ምክንያቱም ልቧ የፈቀደውን ትሠራለች እንጂ እርሱ በአንድም ኾነ በሌላ ምክንያት እርሷን አያዛትምና ነው። “ይኼ አስባ መሥራቷማ ይበል ያሰኛል እንጂ እንዴት ያስነቅፋል?” ብትለኝ አስባ መሥራቷ በራሱ የሚያስነቅፍ ኾኖ ሳየኾን መታዘዟ አስባ ከሰራችው ይልቅ ውጤታማ ስለኾነ ነው። “ያን ያኽል ውጤታማ አትኹን እንጂ በመጠኑም ቢኾን ውጤታማ ካደረጋት መታዘዙ ቢቀርባትስ?” ለጊዜው ይምስል እንጂ ሲውል ሲያድር ባልየው የወንድነቱን ሚና ላይ የመቀዛቀዝ ስሜት ሲታይበት እርሷ በበኩሏ ይኼ ነው ብላ የማትገልጸው ስልቹነትና ድብርት (በእልፍኙም ኾነ በመኝታ ቤቱ ሕይወቷ)ያድራሉ።
አንድ ወንድ የማትታዘዝ ሚስት አግብቶ አለመታዘዟን በውድም ይኹን (በውድ አልን እርሷን አተርፋለሁ ትወደኛለች፣ ላስደስታት ብሎ) በግድ (በግድ አልን ምናባቴ ይሻለኛል ጥላኝ ትኼዳለች፣ ቤቴ ይበጠበጣል፣ ብሎ በፍራቻ) ተቀብሎ ቢኖር ወንድነቱ መሰለቡ የማይቀር ነው በዚኽ ስልብነቱ ደግሞ አንደኛ ደረጃ ተጎጂ እርሷው፣ ምሬተኛም እርሷው ሚስቱ ትኾናለች።
አባወራ በቤቱ ከሚታወቅባቸው መገለጫዎቹ አንዱ የኹሉ አዛዥ መኾኑ ነው ለልጆች ታዛዥነት አርአያዋ ሚስት እንጂ ባል አይደለም። አባወራው ያዛል ሚስት እሺ ትላለች ታደርግማለች ልጆችም የመታዘዝን ፈለግ ከእናታቸው እግር ስር ይማራሉ።
እርሱ ሲያዝ እና እርሷ ስትታዘዝ በይበልጥ ኹለት ነገሮች ይኾናሉ፦
እነርሱም 1ኛ ለልጆች አርአያነት በእርሷ በኩል ይፈጸማል
2ኛ የእርሱን መሪነት ሲያጎለብት ተራክቦአዊ እርካታን ያጎናጽፋታል።
1ኛ ዛሬ ዛሬ የራሳችንን ተፈጥሮአዊ ሚና ሳንወጣ(ወንዱም ያዛዥነቱን ሚስትም የታዛዥነቷን)። ፈጣሪም ልጆቻችን የምናሳድግበት መመሪያ ያልሰጠን ይመስል “የዛሬ ልጆች መች የሰው ነገር ይሰማሉ ” እንላለን።ማን አርአያ ኾናቸውና? እኩል ነን በሚል የተዋረደ ጽንሰ ኃሳብ ማንም የማንም አዛዥ አለመኾኑን ካሳየን በኋላ ልጆቻችን መልሰው እኛኑ የማይታዘዙ ለመምህራን የማይመቹ ለአካባቢያዊም ኾነ ለአገር አስተዳደር የማይተባበሩ አመጸኞች ከኾኑ በኋላ “የዛሬ ልጆችማ ….” እያሉ መውቀስ የኛን ጥፋት እነርሱ ላይ መለደፍ፤ የአባዬን ለእማዬ ይሉት ፈሊጥ ነው። ሴቷ ታዛዥ መኾንን መሰልጠንና ማወቅ እንዳለባት ኹሉ ወንዱም ቅጠኛ አዛዥ መኾንን ይማራል። ግን በቤታችን አዛዥ እና ታዛዥ በመኖሩ አንድ አካል ጨቋኝ ሌላው ኹሉ ግዞተኛ አይኾንም ወይ?..ሳምንት
2ኛ በቤቱ መሪ በመሪነቱም አዛዥ ያልኾነ ባል ምን ቢደክም ሚስቱን እርፍ የሚያደርግ የወሲብ እርካታ መስጠት አይችልም። የሚገርመው ታዲያ መሪነቱ፣ አዛዥነቱ፣ ተሰሚነቱ እርካታ ቢስ ፍትጊያ ትርፉ ንዝንዝ፣ ጭቅጭቅ ነው። የባሏን ቃል ጠባቂ እና ታዛዥ ያልኾነችውም ሚስት ተራክቦአቸው ጉድለት እንዳለበት ስታውቅ የእርካታው መጥፋት ምክንያት ግን እንቆቅልሽ ይኾንባታል።
ከንቱ ልፋት ከንቱ ጩኸት ፤
ሚስትህ አንተን መታዘዝ ያቆመች ዕለት ነው። እንዴት ….ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *