የምስጋና ሕይወትህ ጋሬጣዎች

አባወራ ስራሱ ሕይወት፣ ስለትዳሩ፣ ስለሚስቱ፣ ስለልጆቹ፣ ስለሀገሩ…. ያመሰግናል

ምንም እንኳን ብዙዎች አመስጋኝነት መልካም እንደኾነ ቢስማሙም ጥቂት ብቻ ናቸው። ዘወትር ስለተደረገላቸው ነገር እና ላደረገላቸው አካል ለምስጋና የሚቆሙ።

ስለተደረገልን ነገር ለማመስገን እንቅፋት የሚኾኑትን ነቅሰን ስናወጣ ለምስጋና ጊዜ እንሰጣለን።

፩ኛ “ጊዜ ማጣት”
ዛሬ ዛሬ ስለተደረገልን ነገር ላለማመስገን ጊዜ ማጣትን እንደትልቅ ሰበብ እናቀርበዋለን። ጊዜያችንን በሚያጠፉ ሕይወታችን ላይ ግን ረብ ያለው ጥቅም በማያመጡ ጉዳዮች አጥፍተነው ስናበቃ ለምስጋና የሚኾን ጊዜ እንዳጣን እንኾናለን።

ይኼንንም “ጊዜ ማጣት” ተከትሎ ዐለማዊውንም ኾነ መንፈሳዊውን ሕይወታችንን ወደኋላ የሚጎትት ዝንጋዔ(ዝንጉነት) ይቆጣጠረናል።

፪ኛ ከስጦታችን ጋር መላመድ
የተደረገልን ወይም የተሰጠን ነገር መጀመሪያ ላይ ስናገኘው ደስታችን ወደር የለውም። ለምሳሌ ሥራ ስናገኝ፣ የትዳር ጓደኛ ስናገኝ፣ ጤና ስናገኝ፣ ቤት ስናገኝ… ወዘተ ምስጋናችን በግልጥና በተደጋጋሚ ይኾናል።

ችግሩ ታዲያ ከእነዚህ ስጦዎቻችን ጋር ስንላመድ አብረውን ሲቆዩ በእነርሱ ላገኘነው ኹሉ ምስጋና የተገባቸው መስሎን አለመታየቱ ነው። ስላገኘነው ሥራ፣ ስለምንኖርበት ቤት፣ ስላወቅናቸው ጓደኞች፣ ስለትዳር አጋራችን፣ ስለአብራካችን ክፋዮች ምን ያክሎቻችን እናመሰግናለን?

፫ኛ ቅናት
ሰዉ ኹሉ በየቤቱ፣ በየማሕበራዊ አጋጣሚ፣ በየአደባባዩ፣ በየድረ -ገጹ ያለውን ለማሳየት የእዩልኝ ማስታወቂያ በሚሠራበት በዚኽ ጊዜ የሌሎችን ቅንጡ ኑሮ እያዩ በራስ ባለን ደስተኛ መኾን እያቃተን ነው።

የሰዎችን በማየት እንደመቅናት ባለን ደስተኛ እንዳንኾን የሚያደርገን የለም። በሰዎች ትዳር፣ በሰዎች ቤት፣ በሰዎች መኪና፣ በሰዎች ኑሮ…. መቅናት የተሰጠንን ካለማመስገን፣ እርሱንም ካለማሳደግ አቃቂርም ከማውጣት ይመነጫል።

ምን አለፋችሁ የራስን ችላ ብሎ ሰዎች ባላቸው ነገር ኹሉ መቅናት የምስጋና ሕይወታችንን የሚያጠፋብን፣ ደስታችንን የሚነጥቅብን መጨረሻችንንም ምሬትና ተስፋ መቁረጥ ውስጥ የሚከትብን ነው።

የምስጋና ሕይወትን የማትለማመድ ከኾነ ያንተ ወርቅ ከጎረቤትህ መዳብ አንሶ ይታይሃል፤ ያንተ አልማዝ ከሌላው ጠጠር አንሶ ይታይሃለ። በዚኽም ጊዜ ለስግብግብነት በእርሱም ምክንያት ለሚመጣ ጭካኔ ተላልፈን እንሰጣለን። የሰሞኑን የሀገራችንን የቀድሞ ባለስልጣናት ድርጊት ልብ ይሏል።

፬ኛ ኩራት
ከላይ የጠቀስናቸው ሦስቱን የምስጋና እንቅፋት ካደረግናቸው ኩራት ደግሞ ፍጹም የሚጋርደን ግድግዳ መኾኑ ነው።

ብዙ ነገር ከማሕበረሰባችን ወስደን ሳለ በራሳችን ጥረት እዚህ እንደደረስንና የማሕበረሰባችንም እዳ እንደሌለብን በኩራትና በትዕቢት እንታጀራለን፤ ምስጋናንም እንሸሻታለን።

ቅናት የምስጋና ሕይወታችንን ሲያበላሽ ኩራት ግን ጨረሰን እንዳናውቀው ያደርገናል። አንተ ግን ስለተሰጠህ ነገር ኹሉ ከነ”እንከኑ” አመስግን።

ጀግናው ወንድሜ አንተ ምስጋናን ተለማምደህ እንቅፋቶቹንም አልፈህ የግልህ አድርገው። አንተ ፍጹም ተነባቢ (የሚታይ) የምስጋና ሕይወት ቢኖርህ ለሚስትህም(ምንም እንኳ ዋና አርአያዋ እናቷ ብትኾንም) ኾነ ለልጆችህ አርአያ ትኾናቸዋለህ።

…..ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *