የሰው ልጅ ሕልውና ላይ የተቃጣ ጥቃት

ሳተናው!

አኹን በምንኖርበት ዘመን የሰውን ልጅ ቤተሰባዊ ኑሮ፣ ማሕበራዊ እሴት፣ ዘርን የማስቀጠል ሚና፣ ስነልቦናዊም ኾነ አእምሮኣዊ ደኅንነት በአጠቃላይም የሰውን ልጅ ሕልውና ያጠቃሉ የምላቸው ሦስት አካላት አሉ።

እነርሱንም በቁጥር ሦስት አድርጌ ባስቀምጣቸውም የሰውን ልጅ ሕልውና ከፈጣሪም ጋር ያለውን ዝምድና ለመለየት የሚያጠቁት የሕብረተሰብ ክፍል ግን በተለይ አንድ፤ እርሱም ወንድን ነው።

ከሦስቱ ሁለቱ የሰውን ዘር ባጠቃላይ የመጉዳት/የማጥፋት ተልዕኮ ይዘው ሲነሱ ወንዱ ላይ ያነጣጠሩበት ዋነኛ ምክንያት ደግሞ ትዳርና ትውልድ የታነጸበት መሠረቱ እርሱ እንደኾነ በደንብ ስለሚያውቁት ነው።

፩ኛ በቀጥታ ወንድን፣ ወንዳወንድ ባሕርይን እና ስልጣኑን የሚቃወሙ እና የሚያጠቁ

የተሰጣቸውን ማሕበራዊ፣ ኃይማኖታዊ እና ሀገራዊ ስልጣን ተጠቅመው “የፈቀድነውንና የወደድነውን የመናገርና የመኾን ነፃነት አለን” ብለው በግልጽ ወንድን፣ የወንድ ባሕርያትን እና ስልጣኑን የሚገፉ

፪ኛ ለሰው ዘር ተቆርቋሪ መስለው በሕቡዕ(በድብቅ) የሚሠሩ

በተለይም ደግሞ እንደ እኛ ወግ አጥባቂ ሀገር ላይ ተቀባይነት እንደማያገኙ አውቀው ዓላማቸውን ደብቀው ደካሞችን(ሴቶችንና ሕፃናትን) ተጠቅመው ወንድ ላይ የዘመቱ

፫ኛ በየዋህነት የሚነዱ

ከላይ የተጠቀሱት አካላት ሰይጣናዊ አጀንዳ ሳይገባቸው
ከስሜታዊነት በመነሳት በስልጣኔና ጨዋነት ሰበብ ትውልዱን(ወንዱን) በመስለብ (በስነልቦና)፣ ሰነፍ፣ ጥገኛ፣ ፈሪ፣ ምስኪን፣ ሱሰኛ በማድረግ ለቀደሙት ሁለቱ የሚያዘጋጁትና የሚገብሩትም ልሂቃን ናቸው።

ሳተናው!

ልብ አድርግ በዘመንህ ያለውንም አስተውል! አንድ ሕንጻ መሠረቱ ከተናጋ ሕልውናው እንዲያከትም፤ አንተ እና እኔ መሰል ወንድሞቻችንም ወኔያችን ተሰልቦ ተፈጥሮኣዊ ወንድነታችን ጠፍቶ የሚቆም ትዳር፣ የሚጸና ቤተሰብ፣ የሚታነጽ ትውልድ እና ሉዓላዊት ሀገርም አይኖሩንም።

ስለኾነም እነዚህን ሦስቱን የሀገራችንን ልዕልና፣ የማሕበረሰባችንን ወግ፣ የቤተሰባችንን ስርዓት፣ የትዳርን አንድነት የሚያፈርሱ የዘመናችንን ጠላቶች እስቲ ባጭሩ እንያቸው።

፩ኛ በቀጥታ ወንድን፣ ወንዳወንድ ባሕርይን እና ስልጣኑን የሚቃወሙ እና የሚያጠቁ፡

ይኼም እንዴት ነው ቢሉ፦ አስገድዶ መድፈር፣ ጦርነት፣ ሌብነት፣ ማጅራት መቺነት፣ ሙስና፣ ለከፋ እና የመሳሰሉት የወንዶች የጥፋት ሥራዎችና መገለጫዎቻቸውም ናቸው ብሎ ወንዶች ላይ ቀጥተኛ የኾነ የማሸማቀቅ ሥራ የሚሠሩ ናቸው።

እነዚህ አካላት የጨበጡትን ሥልጣን፣ የያዙትን የመገናኛ ብዙኃን፣ ያላቸውን ተሰሚነት፣ የጫኑትን የትምሕርት ማዕረግ መሣሪያ በማድረግ ዓላማቸውን በግልጽ ይፈጽማሉ።

ይኽንንም ለማስረዳትና ለማሳመን ወንድ፣ ባሕርይው እና ስልጣኑ በማሕበረሰቡ ሰላም ላይ፣ በቤተሰብ አንድነት ላይ በትውልድም ነፃነት ላይ “አደጋ አለው” ሲሉ ተምረው በተካኑበት የውሸት ጥናታቸው ያስረዳሉ።

ከዚኽም የተነሳ በአደባባይ ተፈጥሮኣዊውንና በባሕላችን ቅቡል የኾነውን ወንድነትን የተላበሱ ወንዶችን ሲያዩ ይዘልፋሉ፣ ይንቃሉ፣ ያሸማቅቃሉ። እንደዚህ ዓይነት ወንዶች ማሕበራዊ ኃላፊነት የሚወጡ፣ ተሰሚነት ያላቸውና የማሕበረሰብ አንድነት ላይ ጠንካራ የአቋም ጽናት ያላቸው ሲኾኑ ደግሞ “የሀገርና የመንግስት ስጋት” ይባሉና ይጋዛሉ፣ ይገደላሉም።

እነዚህ የወንድ ጠላቶች “ሴቶች ናቸው” ብላችሁ ካሰባችሁ ተሳስታችኋል፤ ይልቁንም ከፈረሰ ቤተሰብ የወጡ፣ በአስተዳደግ የተበደሉ፣ የእንደዚሁ ዓይነት ጥቃት ሰለባ የኾኑና አንዳንዴም በግልጽ የሰይጣንን ፈቃድ ለመፈጸም በነፍሳቸው የማሉ፣ ከዚሁም ዓላማ ጎን የተሰለፉ ወንዶችም ኾነ ሴቶች እንጂ።

ምሳሌ፦ በዚህ ዘመን ያሉት ሴታቆርቋዦች(Feminists)፣ ግራ ዘመም የኾኑ ምዕራባውያን ልሂቃን.. እና የመሳሰሉት ናቸው

በዚኽ ተጽዕኗቸውም ወንዱ፦

፨ ፈርቶ እና ተሸማቆ እንዲኖር፣ ወንጀሎችን(አስገድዶ መድፈር፣ ለከፋ፣ ግድያ) በሰማ ቁጥር በወንድነቱ እንዲሳቀቅ

፨ ወንድነቱን እና የወንድ የኾነውንም ኹሉ እንዲጠላ

፨ ቤቱን፣ ትዳሩን እንዳይመራ በዚህም ሚስቱም ኾነ ልጆቹ መረን እንዲወጡ

፨ ሚስቱም ኾነ ልጆቹ እንዳይታዘዙትና እንዲያምጹበት

፨ ፈጣሪ በለገሰው ወሲባዊ ሕይወቱም ራሱንም ኾነ ሚስቱን የማያሳርፍ ነገር ግን ሴሰኛ እንዲኾን

፨ ትዳርንም እንዲፈራ ብሎም እንዲጠላው

፨ ለሀገሩ፣ ለኃይማኖቱ፣ አባቶቹም ላቆዩለት ስርዓትና ለወገኖቹም ሕልውና እንዳይሟገት

፨ ራሱንም ኾነ ቤተሰቡን ከማንኛውም ዓይነት ጥቃት እንዳይከላከል ያደርጉታል።

በውጤቱም፦

፨ እግዚኣብሄር አምላኩ የኾነለትን ሕዝብ ተፈጥሮውን ክዶና ጠልቶ ሴትን፣ ገንዘብን፣ ስልጣንን፣ ኾዱን፣ ምቾትን…… አምላኪ እንዲኾን

፨ የተፈጠረበትን ዓላማ እንዳያውቅ እንዳያሳካውም በዚህም ከፈጣሪው እንዲለይ

፨ በቀላሉ ጥቂቶች ብቻ የሚነዱት ባርያ ማድረግ

፨ በስተመጨረሻም ወዶና ፈቅዶ ለሰይጣን እንዲገብር ማድረግ ነው

ምሳሌ፦ ትላንት ኃይማኖተኛ በተለይም ክርስትያን የነበሩ ዛሬ ግን በኺደት ሰይጣንን በግልጽ የሚያመልኩትን ምዕራባውያን ተመልከት።

====================================

፪ኛ ለሰው ዘር (በተለይም ለሴቶችና ሕፃናት) ተቆርቋሪ መስለው በሕቡዕ ወንድ ላይ የጥቃት ፍላጻ የሚወረውሩ
.
.
. ለሳምንት ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *