የሴታቆርቋዡ (Feminism) የትመጣ፣ ምንነት እና መገለጫዎቹ

ለሴቶች “እኩልነት” እታገላለሁ ብሎ ወደ ዐለማችን የመጣው ሴታቆርቋዥ(Feminism) የተሰኘ እሳቤ አነሳሱ(አጀማመሩ) ከቀለም አብዮት ጋር የተወዳጀ ነበር።

የቀለሙ(የጥቁሮች ጭቆና በተለይ) አብዮት “ሰዎች ኹሉ አንድ ናቸው በቀለም ምክንያት ሥራ፣ ትምሕርት፣፣ ማሕበራዊ ሕይወት ላይ ልዩነት አይኑር” ሲል አግባብነት ያለው ጥያቄ ጠይቋል። እርሱን ተከትሎ የመጣው የሴቶች መብት ግን በሴቶች እና በወንዶች መካከል ያለውን ተፈጥሮኣዊ (አካላዊ፣ አእምሮኣዊም ኾነ ስሜታዊ) ልዩነት ግምት ውስጥ ያልከተተ እንዳው የአፍኣ “እኩልነት” ብቻ አቀነቀነ።

በይፋ ከወጣበት ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በብዙ መልኩ ቅርጹንና ትልሙን እየቀያየረ ተጠናክሮ እስከዛሬ ቀጥሏል።

መገለጫዎቹን እስቲ በሦስት ቦታዎች እንያቸው
፩ በአደባባይ (በሥራ፣ በትምሕርት፣ በኃይማኖትና በሌሎች ማሕበራዊ መስተጋብሮች)
በሥራ
የሴት አቆርቋዡ (Feminism) እሳቤ ሴቶችን ከላይ በጠቀስናቸው አደባባይ ላይ በሚውሉባቸው መስኮች ላይ ከወንዶች እኩል እንደኾኑና ከእነርሱ እኩል መሥራትም መጠቀምም የተገባቸው መኾኑን ያጸናል።

ይኹንና ሴቶች በተሰማሩባቸው የሥራ መስኮች ሥር ከአካላዊ ብቃት አንጻር የሚፈጠረውን ክፍተት ወንዱ በውዴታም(“እርሷ እኮ ሴት ነች አቅም የላትም ተባበራት”ተብሎ) አልያም በግዴታ እንዲሞላ ይደረጋል።

እነዚኽን በችግር ጊዜ ወንዱን የሚያስጠሩ ሥራዎች ሴቶቹ ራሳቸው እንዲሞሉ ቢደረግ ግን የጉልበት ሥራ ቢኾን የሴትነት ልስላሴያቸው፣ የቅርጻቸውም ክበብ ይጠፋል። አእምሮኣዊ ቢኾን ደግሞ እነዚያን የቁጥርም ኾነ የምርምር ሥራ ሲሠሩ በዚህም ሲልቁ ወይም የላቁ ሲኾኑ የሴትነት ወዛቸው እየጠፋ የእናትነት ፍቅራቸው እየቀነሰ አለባበሳቸውም ከቀሚስ ሙሉበሙሉ ወደ ሱሪ እየተቀየረ ፊታቸውም ፀጉር እያበቀለ ይኼዳል።

አለባበስና ጉንተላ
የሴታቆርቋዡ እሳቤ ከመጣ ወዲህ ግልጽነት እና ነጻነት በሚሉ ሽፋኖች ሴቶቻችን በከፊል ዕርቃናቸውን መታየት የተለመደ ክስተት ኾኗል። ሴቶቹ እንደፈለጋቸው ሲለብሱ አለባበሳቸው ስቦት የነካቸው ወንድ በደለኛ(abuser)፣ በአትኩሮት የተመለከተው ደግሞ ወሲብ አዳኝ(sexual predator) የሚባሉ ስሞች ይሰጡታል፣ ካስፈለገም ይከሰሳል።

ልብ አድርጉ! ሴቶቹ በነጻነት ስም ለሚለብሱት አለባበስ ይኹንታን ሲያገኙ፤ ወንዱ በሴቶቹ አለባበስ ለሚደርስበት የስሜት ጫና እንዲኹም የወሲብ ትኩሳት ከዚህም የተነሳ ለሚፈጽማቸው ስሜታዊ ድርጊቶች እንዳይዳረግ ምንም አይነት ከለላ የለውም። በሥራህ ያውጣህ ነው ነገሩ።
ልዕልና
የሴታቆርቋዡ (Feminism) እሳቤ ሴቷን በፍጹም ለወንድ አትገዢ በወንድ ሥርም አትኹኚ ብቻ አይደለም ወንድ እንዳይበልጥሽም ጭምር ብሎ ይመክራታል። ስለዚህም በትዳሯ ውስጥ ባሏ በሥራው በትምሕርቱ ራሱን እንዲለውጥ በአፍኣ ትደግፈው እንጂ ማደግና መለወጥ ሲጀምር ትረበሻለች። የእርሱ የአደባባይ ልዕልና ወደ እልፍኙና መኝታቤቱም ገብቶ የእርሷን ትኽትና ይጠይቃልና አትቀበለውም።
አስተውል!!!!!
በተለይ ደግሞ የአባቷ ልጅ ባልኾነችው ላይ ሴታቆርቋዡ(Feminism) ተጨምሮ (በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ) ይኾናል። እናቷ ጋር ያየችውን አባቷ በምስኪንነት ሲኖር የነበረውን ሕይወት መድገምን እንጂ ለፍቅር መሸነፍን አታውቀውም ፤ መበደል ይመስላታልና።

እውነተኛና ትክክልም የሚመስሉ ምክንያቶችም ፈልጋ ታጨናግፈዋለች። ተመልሶም ከእጅ ወደኣፍ ኑሮው ሲመጣ አለኹልህ ትለዋለች እንደታደገችውም ታወራለች። በዚህም ኹልጊዜም የወንድነቱ ልዕልና እንዳይሰምር በራሱም መተማመን የሌለው ፈሪ እና ከመዳፏ የማይወጣ ምስኪን እንዲኾን ትፈልጋለች። …………
፪ በእልፍኝ
የሴታቆርቋዡ (Feminism) እሳቤ ሴቷን በቤቷ ውስጥ ለወንዱ እንዳትገዛ፣ እንዳትታዘዘው እና በኃሳብም እንዳትሸነፍለት ይመክራታል። ይኽ በመኾኑም፦
፪፥፩ ውስጧ በተለይም በወሲባዊ ተራክቦዋ አታርፍም (እረፍት አይሰማትም)
፪፥፪ ሕይወቷ በምሬትና በብስጭት የተሞላ ይኾናል(ዘወትር በቤቷ ላለመሸነፍ ሙግት አለና)
፪፥፫ ለልጆቿ የመታዘዝ አርኣያ አትኾናቸውም
፪፥፬ ልጆቿ ምን ጭምት ቢመስሉ የማይታዘዙ ልጆች(ትውልዶች) ይኾናሉ። (ዛሬ ዛሬ እኔ ሰው አዞኝ ከምሠራ ራሴ አስቤ ስሠራ ደስ ይለኛል የሚሉ ትውልዶች መፈጠራቸውን ልብይሏል)
፪፥፭ ቤቱ መሪ ያጣ የፉክክር ቤት ይኾናል
፪፥፮ ስነ ሥርዓትን “ጭቆና” ቁጣና ተግሳጽንም “አምባገነንነት” ቁንጥጫ ከተከተለ ደግሞ “አረመኔነት” ቅጠቢስ ሕይወት እንዳትመራ ለከለከሏት የባሏ ኃላፊነቶች የምትሰጣቸው ስሞች ናቸው።

ሳምንት ብንኖር
፫ በመኝታ ቤት እንዲኹም የሴታቆርቋዡ (Feminism) እሳቤ የዛሬ ወንዶችን እንዴት አልጫ እንዳደረጋቸው።
… ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *