የሴት ምላስና የወንድ ጉልበት

(እንደተለመደው ኾደ ባሻዎች አታንቡት)

በወንድና በሴት ተፈጥሮ ውስጥ በጉልህ ከሚታዩት ልዩነቶች መካከል የወንድ ልጅ ከሴቷ የበለጠ ጉልበተኛ መኾንና የሴቷ ከወንዱ የበለጠ ምላሰኛ ወይም ወሬኛ መኾን ናቸው።

ይኼ ልዩነት ግን ፈጣሪ በምክንያትና በዓላማ የሰጣቸው እንጂ እነርሱ ከፍጥረት/ከውልደት ወዲህ ያመጡት ችሎታ አይደለም። በእርግጥ ወንዱ ፈርጣማ፣ ጉልበተኛ ለመኾን በሥራ በእንቅስቃሴ ቢያዳብረውም። ሴቷም ባሏት ማሕበራዊ ግንኙነቶች ብታበለጽገውም መሠረታዊ ግኝቱ ግን ከፈጣሪ ነው።

በዚህ መልክ እንደየጾታችን ልዩነት ለየቅል የተሰጠንን ሀብት “ስጦታ ነው” ብለን ስንቀበለው ለምን እንደተሰጠንም ስንረዳው እናዳብረዋለን፣ እንጠብቀዋለን(እንዳይጠፋ)፣ እንጠቀምበታለን እንዲሁም እንጠቅምበታለንም።

የሴት ምላስ(አንደበት)

በምንኖርበት ቤተሰብ፣ ማሕበረሰብ፣ በተማርንበት ትምሕርት ቤት በሥራ ገበታችንም ቢኾን ሴቶች ከወንዶች ይልቅ እንደሚያወሩ ግልጽ ነው።

ምን አወሩ? ስለማንስ? እንዴት? ለምንስ አወሩ የሚለውን እንተወውና ሴቶች በአብዛኛው ወሬ ማውራትን ይወዳሉ። ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ብዛት ያላቸው ሴቶች አብረው ቁጭ ብለው ካላወሩ እነዚያ ሴቶች ተጣልተዋል አልያም ተደባብረዋል ብትሉ ልክ የመኾናችሁ እድል ሰፊ ነው።

ይኼ ወሬ መውደዳቸው ግን ተፈጥሮኣዊ ነው። ተፈጥሮኣዊ ነው ስል ፈጣሪ በምክንያት ለዓላማ የሰጣቸው ነው ለማለት ነው።

ለምን?
ወሬ ወይም ንግግር ሰዎች ራሳቸውን የሚገልጹበት፣ የሚያስተዋውቁበትና የሚግባቡበት ነው። እርሷ ደግሞ በቤት ውስጥ ልጅ የምትወልድ፣ የምታጠባ የምትንከባከብ ናትና ከልጆቿ ጋር ለሚኖራት ግንኙነት ይረዳት ዘንድ ቋንቋን(ወሬን፣ ንግግርን) ትጠቀማለችና ነው።

በዚህ ውስጥ ያለው ዓላማ ታዲያ በወሬዋና በንግግሯ ከልጆቿ ጋር ፍቅርን፣ አንድነትን በመግለጽና በመመሥረት መቀራረብ እንድትችል ነው። ይኼም ሲኾን ልጆቿ ፍላጎታቸውን በግልጽ ለማቅረብም ኾነ ለጥያቄዎቻቸው መልስ ለማግኘት ያስችላቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም መፍትሔ አገኙለትም አላገኙለትም፣ አብዛኛውንም ጊዜ መፍትሔ ፍለጋ ሳይኾን ጭንቀታቸውን ችግራቸውን በወሬ ያስተነፍሱታል።
ይኹን እንጂ ይኼ ለሴቶች የተሰጣቸው ምላስ ለማንኛውም ለሰው ልጆች እንደሚሰጥ ጸጋ እንክብካቤን እንዳይበላሽ፣ ጥበቃን በጠላት እንዳይጠፋ፣ ስልጠናን በአግባቡ ለመጠቀም ይሻል።

ለዚህ ደግሞ በአርአያነት ዋነኛ አስተማሪዋ እናት ናት። እናት በአንደበቷ ፈጣሪዋን ስታመሰግንበት፣ ባሏን ስታገንበት/ስታደንቅበት ፣ ልጆቿን በፍቅር ቃል ስትጠራበት ለሴት ልጇ ምሳሌን እየተወችላት ነው።

በተቃራኒው ደግሞ እናት ፈጣሪዋን ስታማርርበት፣ ባሏን ስታማበት አልያም የምንዴት ቃል ስትመልስበት፣ ልጆቿንም ስታንጓጥጥበትና ስታመናጭቅበት እንዲሁ ትኾን ዘንድ እያሰለጠነቻት ነው።

አጠቃቀም
በአግባቡ ካልተጠቀምንበት የምላስ አጥፊነት ፍጹም ከባድ ነው። ስለዚህም አባት ልጆቹን የተፈጥሮ ጸጋቸውን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው በስነስርዓትና በስነምግባር ሲቀርጽ እናት ደግሞ አርአያ በመኾን ታግዘዋለች።

ይኹንና የአጠቃቀሙን ነገር ስነስርዓትና ስነምግባር ማስያዝ ተገቢ ቢኾንም ተፈጥሮኣዊውን የቃላት ድርሻቸውን ግን መገደብ መዘዙ ብዙ ነው።

እንዴት?……… ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

2 Responses

  1. solomon says:

    betam arif new henoke bewebsite bememtath des bilognal

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *