የሴት ምርጫህ የአባቷ ልጅ ትሁን (ካለፈው የቀጠለ)

ይህች የአባቷ ልጅ አባቷ በስርዓት ያሳደጋት ስለሆነች አንተ(ባሏ) ለምታወጣው የቤታችሁ ቅጥ(ስርዓት) ልትሰጥ የምትችል ገራም ነች።
አስረጅ፦ የ”IT expert” የሆናችሁ ከተሳሳትኩ አርሙኝ። አንድ የኮምፒውተር ሶፍትዌር ወይም ኮድ ምርጥ ከሚያስብሉት ነጥቦች ውስጥ ማሻሻል ሲፈለግ በቀላሉ ይሻሻላል ወይ(upgrade) ፣ ማስተካከል ሲፈልግስ (maintainable) ነው ወይ የሚሉት ይገኙባቸዋል።

ለሴቷም እንዲሁ ነው። እርሷ በቤትህ ድንቅ ጥበብ የተቸራት አጋርህ ነች። ስለዚህ እነዚህን ጥያቄዎች አስባቸው፦ አንተ ቤትህን በኃላፊነት ለማስተዳዳር ስትጀምር የምትመርጣት ሴት በትዳር ተወስና የልጆችህ እናት ለመሆን ትፈልጋለች ወይ(ካልፈለገች ማስገደድ ኢ-ሰብኣዊ ነውና በውለታም ቢሆን)፣ ሲቀጥል መምከር፣ ማስተማር ብትፈልግ ወይም በጥፋቶቿ መሐከል ተግሳጽን ትቀበላለች ወይ? ይህ ደግሞ የአባቷ ልጅ ነች ወይ? ማለት ነው።

ወንድሜ የአባቷ ልጅ ያልሆነች ቆንጆ ሴት አግብተህ “ቆንጆ ሚስት አለችህ” ሲሉህ አፍህ እየሳቀ ውስጥህ ግን እያረረ መኖር ትፈልጋለህ? የአባቷ ልጅ የሆነችው መልካም ስታስብላትም ሆነ ስታደርግላት ላንተ ያላትን አክብሮት ሲጨምረው አባቷ ያላሳደጋትን ግን ውለታ(ዕዳ) ታበዛባታለህ እንጂ ላንተ ያላትን አክብሮት አይጨምርም። ምስጋናውም አክብሮቱም ቀርቶ ጭራሽ “ይሄማ ግዴታው አይደል” በሚል የንቀት ንግግር ታቆስልሃለች።

እንዲህ የአባቷ ልጅ፣ የአባቷ ልጅ፣ የአባቷ ልጅ እያልኩ ስነዘንዝህ አንተ ደግሞ ለወደፊቱ ለሴቷ ልጅህ ሕይወት አስበህ በስርዓትና በፍቅር ኮትኩተህ እንደምታሳድጋት ተስፋ አለኝ።

በስርዓት ውስጥ ማደግ ለተዘረጋው ስርዓት መገዛትን፣ ለስርዓት አውጪው መታመንን እና መታዘዝን ይጠይቃል። በዚህ የሕይወት ልምምድ መኖር በኋላ ሕይወታችን በምንሳተፍባቸው ትዳር፣ ሥራ፣ ማሕበራዊ ሕይወት…..እና ሌሎችም በቅጠኛ ስርዓት(system) በሚመሩ ተቋማት ውስጥ ለሚኖረን ሱታፌ አይነተኛ ሚና ይጫወታል።

አሁን አሁን ስርዓትን የሚያስተምር ቤቱን በቅጡ የሚመራ አባት እየጠፋ ነው በአካል ቢኖርም ቤቱን ቅጥ የማያሲዝ ይሆናል። በዚህ ቤት የምታድግም ልጅ ምን መንፈሳዊ ብትባል ተግባራዊ የወንድ ታዛዥነት ይጎድላታል። በሥራ ገበታዋ፣ በማሕበራዊ ሕይወቷ፣ በመንፈሳዊ ሱታፌዋ፣ በምትማርበት የትምህርት ተቋም ሁሉ ብዙዎች ለተገዙለት ስርዓት ስትገዛ በቤት ውስጥ ግን ለባሏ ዳ ተ ኛ ነች።

ይህ ግን የእርሷ ጥፋት ሳይሆን በዋናነት የአባቷ ነው (ሲቀጥል ግን የእናቷ ለስርዓቱ ያለመገዛት አርአያነት ነው)። ምክንያቱም ደግሞ ፍቅርን በስርዓት አጥሮ ማስተማር የተገባው እርሱ ነበርና።

እኔ በዚህ ላይ መንፈሳዊ ናቸው የተባሉ እድሜያቸው አርባ፣ ሀምሳ እና ስድሳ፣ የሆኑ በትዳርም ሀያ እና ከዛ በላይ የቆዩ ቤተሰቦችን ታዝቤያለሁ። ቤታቸውን ቅጥ የሚያስዙ ከሚስታቸው (የአባቷ ልጅ)ጀምረው ልጆቻቸውን በስርዓት የሚያስተዳድሩት ልጆቻቸው ግብረገብና ስኬታማ ናቸው። እነዚያ ግን ቤታቸውን ለማስተዳደር ከሚስታቸው ጋር ሙግት የሚገጥሙት ሚስት የአባቷ ልጅ አይደለችምና የሙግት አርአያ ትሆናቸዋለች። ሴቷ ልጃቸውንም መንፈሳዊ ነች ብለህ ብታገባት ቤቴን ላስተዳድርበት ብለህ ለምትዘረጋው ስርዓት ልቧ ይከብድባታል። በአጭሩ አትታዘዝህም። ካልታዘዘችህ ምን እወድሃለሁ ብትልህ አታከብርህም። አንተ ደግሞ ሴት ልጅ ከላከበረችህ እርሷ ፊት ወንድነትህ ይልፈሰፈሳል…….መወደድ እኮ የእርሷ ነው።

የሚገርምህ ነገር ይህ ላንተ ቃል ያላት እምቢተኝነት እጇን በእጇ የምትጎዳበት ነው። “እንዴት?” እንዴት ማለት ጥሩ። አንዲት ልጅ በህቡዕ በሚንቀሳቀስ እምቢተኝነት ታጥራ ስታድግ በእልፍኝህም ሆነ በውጭ ከሚፈጠረው ያለመታዘዝ ችግር ይልቅ የመኝታ ቤቱ ይበረታል። ወንድን ማመን፣ ላመነችው ወንድ መታዘዝን መጀመሪያ የምታቀው ወንድ(አባቷ) ልቦናዋ ውስጥ አልቀረጸውምና። ይህ መታዘዝ የምልህ ነገር በአፍኣ ያለ ሳይሆን በፍጹም የተማረከ ልብ የሚታዘዘውን ነው።
ምን ስጋ ቢፋተግ የእርካታው ጥጉ የሚገኘው ከልብ በሚመጣ መሰጠት የሆነበት ወሲብ(ተራክቦ) ነውና ወሲቡ(ተራክቦው) ለእርሷ ባዶ፣ ከንቱ፣ የበይ ተመልካች የሚያደርጋት ይሆናል።(አንተ ስትረካ እርሷ ቅምም አይላትምና አ ታ ረ ካ ት ም ና ነው።)

ከዚህ በኋላማ አንተ ልትቋቋመው የማትችለው ንቀት በዓይነት፣ በብዛት፣ በመጠን ገዝፎ ይመጣል ቤትህም የንዝንዝ እና የጭቅጭቅ መናኻሪያ ይሆናል፣ ማጣፊያውም ይቸግርሃል……. ይቆየን።

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *