የሴት ምርጫህ “የአባቷ ልጅ” ትሁን!

*የአባቷ ልጅ ለሚለው ትርጉም ከዚህ በፊት የጻፍኩትን አንብብ።*

አንተ ወንድሜ ስኬታማ፣ትዳር፣ ደስተኛ ቤተሰብ፣ ከራሳቸው አልፈው ስለወገን ስለሃገር፣ ስለዓለም የሚያስቡ ኃላፊነት የሚሰማቸው ልጆች እንዲኖሩህ ትፈልጋለህ? እንግዲያው የሚስት ምርጫህን አስተካክል።

ልብ አድርግ!! ዘመነ ግርምቢጥ ላይ ደርሰን አዋቂዎች አባቶቻችን የነበራቸውን እውቀት ገፍተን ፍቅር በምንለው ፍትወት ተጠምደን እኛ እየከሰርን የከሰረ ትውልድ እያፈራን ነው።የሚገርምህ ነገር ይህ የናቅነው የአባቶቻችን እውቀት ኋላቀርነት ነው ብለን የገፋነው ጥበብ ዛሬ ዋጋ እያስከፈለን ነው።

እስቲ የዛን የድሮውን የደጉን ዘመን ምርጫ እናስታውስ አንድ ወንድ አንዲትን ሴት ለትዳር ሲያስብ የማን ልጅ ናት? አባቷ ማን ነው? እርሷስ በስርዓት ተይዛ ያደገች ወይስ መደዴ መንገድ የለመደች ነች?…እና የመሳሰሉት ጥያቄዎች ይነሳሉ።(ሌሎች ጊዜያዊ ጥቅምን ያማከሉ ለእኛ ጥሩ ምሳሌ አይደሉምና አንጠቀምባቸውም)

የተጠያቂዋ ሴት ልጅ አባት በበኩሉ በጉዳዩ ላይ ይመክርበታል።”ማነው ጠያቂው?” “የማንስ ልጅ ነው?” (ይህ ማለት ቤተሰቡ በስነ-ስርዓት ጉዳይ ይታማል ወይ? ተከብሮስ ያስከብራል ወይ ማለት ነው?)።
እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው አባቶች ለጥያቄዎቻቸው በአግባቡ መልስ ሲያገኙ የሁለቱ ልጆች የወደፊት የትዳር ሕይወት በማይነቃነቅ መሠረት ላይ ይታነጻል።

ውድ ወንድሜ! ይህን ጽንሰ ኃሳብ በተለያየ መንገድ አንስቼዋለሁ ከአእምሮህ የእውቀት ማህደር ወጥቶ በልቦናህ ውስጥ እንዲቀመጥ እፈልጋለሁና ሌላም ጊዜ ቅርጹን ለውጬ እና አደራጅቼ ሳነሳው አትሰልች ምክንያቱም ስለምወድህና ስለምወድህ ብቻ ነው።

በዙሪያህ ካሉ ሴቶች ውስጥ ለትዳር ከደረሱት ተዋውቀህ አንዷን ለትዳር ልታጭ ትችላለህ። ብዙ የምርጫ መስፈርቶች ሊኖሩህም ይችላሉ ነገር ግን ከሁሉ ቀዳሚው ሊሆንልህ የሚገባው “የአባቷ ልጅ ነች ወይ?” ነው። ምንም እንኳ የተለያየ የትምህርት ደረጃ፣ የኑሮ ደረጃ፣ ውበት(ቁንጅና) ሌላም ሌላም ቢኖራቸውም በሴትነታቸው ውስጥ የጋራ የሆነ ባሕርይ አላቸው እርሱም መሪ፣ራስ፣ አስተዳዳሪ፣ደጋፊ፣ፍቅር ሲጪ፣ አዛዥ ወንድ ይፈልጋሉ። ደግሞ ጠይቃቸው አሉ? መጠየቅ የምስኪን ጠባይ ነው ብዬሃለሁ አንተ አባወራ ነህ እውነትን ትመረምራለህ ታደርገዋህ።

ልብ አድርግ!
አንተ ይህንን ድርሻህን ስትወጣ እርሷም ስትቀበል ብቻ ሕይወትህ ጣፋጭ ኑሮህም ቀላል ይሆናል።ይህም በግብረገብነት የታነጸ አባወራነትን ይዘህ ስትመጣ እና የአባቷ ልጅ የሆነችውን ስትመርጥ ይፈጸማል።

ድገመው እስቲ!
አንተ የመሪነት፣የራስነት፣ የአስተዳዳሪነት፣የደጋፊነት፣ የፍቅር ሰጪነት፣ የአዛዥነት ሚናህንስትወጣ እርሷም ስትቀበል ብቻ ሕይወትህ ጣፋጭ ኑሮህም ቀላል ይሆናል። በግብረገብነት ለታነጸው አባወራነትህ የአባቷ ልጅ ብቻ ሕልምህን እውን ታደርጋለች።

ውዱ ወንድሜ ይህችን የአባቷ ልጅ ካገኘህ አይንህን ሳታሽ ዋጋን ሁሉ ከፍለህ ያንተ አድርጋት። ዛሬ ላይ እንደዚህች አይነት ሴት ውድ ናት። ጊዜህን የአባቷ ልጅ ካልሆነችው “ቆንጆ”፣ “የተማረች”፣ “የገባት”፣ “ዘናጭ”፣ “ስኬታማ”፣ “ሐብታም”….. ጋር አታባክን። “መንፈሳዊ” ፣”ቆራቢ” ነች? እያልክም አትድከም እናስ? እናማ የአባቷ ልጅ ነች ወይ? ብለህ ጠይቅ መልሱ አዎ ከሆነ ሌላው መስፈርት ሁሉ ኢምንት ነው።

ይህች የአባቷ ልጅ ግብረገብ የሆነች ብቻ ሳትሆን…….ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *