የሴት ምርጫህ የአባቷ ልጅ ይሁን(ክፍል ሦስት)

እንዴት ሰነበታችሁ?
ስለ አባቷ ልጅ ስናወራ ሦስተኛ ቅዳሜ መጣ።በእርግጥ ሀምሳ ሁለቱንም ቅዳሜዎች ስለእርሷ ቢወራ አይበዛባትም፦”ልባም ሴትን ማን….”መጽ.ተግ.31፥10ተብሏልና።ዛሬ ስለ አባቷ ልጅ ስናነሳ ካልኾነችው ጋር በንጽጽር ለመወያየት መንስዔ ይኾነን ዘንድ የሚከተለውን አባባል እጠቀማለሁ።

“ተፈጥሮን ተመክሮ አይቀይረውም”

ይህ አነጋጋሪ እና አመራማሪ አባባል ነው። ላዩን ስናየው በተፈጥሮ የተሰጠንን ጠባይ ተመክረን አንቀይረውም የሚል አንድምታ አለው። (ከተፈጥሮ ባሕሪይ እንጂ ጠባይ እኛው ከማሕበረሰባችን የምንቀዳው ኾኖ ሳለ) ነገር ግን ጠባይ በተፈጥሮ ከተሰጠን ለበጎውም ለመጥፎውም ጠባያችን ተጠያቂው ፈጣሪ ሊኾን ነው። በባሕሪው ሕጸጽ እና ግድፈት የሌለበትን ፈጣሪ የእጁ ሥራ ሕጸጽ እና ግድፈት አለበት ብሎ ማመን ባሕሪውን ካለመረዳት ይመነጫል(አነጋጋሪነቱ ይህ ነው)። ታዲያ እዚህ አባባል ላይ “ተፈጥሮ” የተባለው ቃል ማንን ወክሎ ተገኘ(ስንመራመር)። ስንወለድ ይዘነው በመጣነው እንደብራና ተሰናድቶ በተወደረ አእምሮአችን ላይ ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ የተጻፈውን ከአካባቢያችን የቃረምነውን እና እኛነታችንን የሚገልጸውን አመለካከት(አስተሳሰብ)፣ እምነት እና ድርጊት ነው።

ይህ በዘልማድ “ተፈጥሮ” ያልነውን ሰው ተለወጥ ስላልነውው ሳይኾን ግለሰቡ ራሱ ወዶ እና ፈቅዶ ሊቀየር ካሰበ አስቦም ካመነ አምኖም ቢያደርገው ይለወጣል። ነገር ግን እርሱ እኮ/እርሷ እኮ የሰው ነገር አይሰማም/አትሰማም ተፈጥሮው/ተፈጥሮዋ ነው እንላለን።

የአባቷ ልጅ
ይኼን አለም ከተቀላቀለችበት ቀን አንስቶ አባቷ ከጎኗ ነው። በተሰጣት ነጭ ወረቀት መሳይ አእምሮዋ ላይ ያ መልካም አባት ወደፊት ዐለምን የምታይበትን፣ የምትመዝንበትን እና የምትኖርበትን ዕውቀት፣ጠባይ ይቀርጻል። ወንድን(የምታገባውን) ፍቅር መጋቢዋ፣ መከታዋ፣ መሪዋ፣ ከለላዋ፣ …… እንደኾነ እየሆነ እያደረገ ይቀርጽላታል። ይህንንም ይዛ ታድጋለች። በእውቀት ላይ የተመሠረተ በራስ መተማመን፣ መልካሙን ሁሉ የምትፈልግና እርሱም ላይ የምትገኝ ልባምም ትኾናለች። እኛም በዘልማዳዊው አባባል ተፈጥሮዋ ነው እንላለን አባቷ በድግግሞሽ የቀረጸውን።
ትዳርንም ስታስብ ምንም እንኳ ቢያደክማት እነዚያን የአባቷን ምርጥ ስብዕናዎች የያዘ ወንድ ትፈልጋለች። ፍለጋዋም አባወራውን ስታገኝ ያበቃል በእርሱ ጥግብ፣ እርክት ፣ እርፍ ትላለችና።

አባቷ ያ ነጩ ወረቀት አእምሮዋ ላይ በአንድም ይኹን በሌላ ምክንያት መልካም ስብዕናን መቅረጽ ካልቻለ ግን ከተራ ጉራ እና ድንፋታ የዘለለ በእወቀት እና በእውነት ላይ የተመሠረተ በራስ መተማመን አይኖራትም። ኹለተኛም ምንም በወንድ ብትወደድ ወዶ የሚያሳያት ያ የወንድ ፈር ቀዳጅ አባት አልነበረምና(በአካል ቢኖርም ሴት ልጁን ከማቅበጥ ውጪ ሌላ የማያውቅ ወይም ግዴለሽ ነበርና) በስሜት ተጋግላ የገባችበት ትዳር ይቀዘቅዛል።ከዚህም የተነሳ ምክንያቱ ምን እንደኾነ የማታውቀው ያለመጥገብ፣ ያለመርካት፣ እና በባሏ ያለማረፍ ስሜት ይጎበኛታል(አሉታዊ ጉብኝቱ ይበልጥ ወሲባዊም ነው)። ከልጅነቷ ጀምሮ ከወንድ ፍቅር የማግኘት፣ የመበረታታት፣ የመሠልጠን(ለስርዓት)፣ የመገራት(በምግባር)፣ የመመራት….ስብዕናዎች አልተቀረጹባትም። ይህም ተዋህዷታልና በዘልማዳዊ አባባል ተፈጥሮዋ ነው እንላለን። ባልየውንም “እንግዲህ ችለህ ኑር፤ ትዳር ተቻችሎ መኖር ነው” እንላለን።

አንተ ግን በዚህ የሕይወት አዙሪት ተይዘህ ስታማርርና ስትማረር ከምትኖር አስቀድመህ ምርጫህን አስተካክል። የምታገኘው የፈለግከውን እና የመረጥከውን ነውና። አእምሮ የተሰጠህ ቀይ እና ጥቁር፣ ወፍራምና ቀጭን፣ አጭር እና ረጅም…. እንድትለይበት አይደለም ይህንንማ ውሾችና ድመቶችም ይለያሉ። አንተ ግን መርምር “ይህቺ ልቤ የከጀላት ልጅ የአባቷ ልጅ ነች?” ብለህ።

በሌላ ጊዜ ከምታገኛቸው ሴቶች መሐከል የአባቷ ልጅ የኾነችውን እንዴት ነቅሰህ እንደምታወጣት እጠቁምሃለው። ልባምን ሴት ማን…. ይቆየን።

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *