የቤት ውስጥ ሥራና ጾታዊ ቁርኝቱ

በዘመነኛው ስልጣኔ የቤት ውስጥ ሥራ ጾታ እንደማይለይ ይነገረናል። የዛሬን አያድርገውና በድሮው ዘመን ወንዱ ውጪ በእርሻና በሌሎችም ሥራዎች ውሎ ወደቤቱ በሚገባበት ዘመን ሴቶቹ ሙሉ በሙሉ የቤት እመቤት በመኾን የቤት ውስጥ ሥራውን ከሌሎች የቤተሰቡ አባላት ጋር ይፈጽማሉ።

ነገር ግን አኹን ባለንበት ዘመን ሴቷም እንደወንዱ ሥራ ውላ በምትገባበትና የቤት ውስጥ አጋር(የቤተሰብ አባላት) በቀነሱበት ዘመን የወንዱን እገዛ አማራጭ የለሽ ያደርገዋል። እገዛው ግን “ምን” እና “እስከምን” የሚለው ጥያቄ ይኾናል።
ምክንያቱ ደግሞ ሰው ሥራን እንዲቀርጽ ሥራም ደግሞ ሰውን ይቀርጻልና የተሳተፈባቸው ሥራዎች ተፈጥሮኣዊ ወንድነቱ ላይ የሚያሳድሩት ጫና የማታ የማታ ወንድነቱ ስቧት የመጣችውን ሴት አያርቃትም ወይ?

የትኛውም ዐይነትሥራ ከመሠራቱ በፊት የአካልም ኾነ የአእምሮ ዝግጁነት የመንፈስ ቁርጠኝነትን ይሻል። ይኼን ዝግጁነት ደግሞ ተፈጥሮ ራሷ በልግስና ትደግፈዋለች።
አስረጅ 1 ፦ የጉልበት ሥራ
ከሥራው በፊት ባለ ዝግጅት፡ የጉልበት ሥራ መሥራትን ስታስብ ቀድሞ በተፈጥሮ የተለገሰህን ጡንቻ ወይም ወደ ጡንቻ ማደግ የሚችል ሰውነት መሰጠትህን አስተውል። ስለዚህም ይኼን ስጦታህን በማበልጸግ ብቻ ራስህን ማዘጋጀት ትችላለህ።

ከሥራው በኋላ የሚደርስብህም የሥራው አሻራ ቀድመህ ስታበለጽገው የነበረውን ሰውነትህን ያደረጅልሃል። በዚህም የአካል ብቃትህ ይጨምራል።በዚህም ከመንጋው ወንድ መሐከል አውራ መኾን የሚችለውን ለመለየት የሴቷ ደመነፍስ በቀላሉ ይጠቀምበታል።

በተቃራኒው ደግሞ ሥራህ ምንም ዐይነት ጉልበት የማይጠይቅ ከኾነና አንተም አካላዊ እንቅስቃሴን ከማድረግ የተቆጠብክ ብትኾን የሰውነትህ እየሟሸሸ ይኼዳል። ሰውነትህም በስብ እየተሞላ በደረት ጡንቻ ፈንታ ጡትና ቂጥ ታወጣለህ።

በአንጻሩ ግን ይኼን የጉልበት ሥራ ሴቷ አትሠራውም ማለት አይደለም። ፈጣሪ ግን ከፍተኛ የጉልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ የሰውነታቸውን ቅርጽ አልሠራውም(ከወንዱ አንጻር) ። እንሥራ ቢሉ ግን ተፈጥሮ ከለገሰቻቸው አካላዊ ቅርጽ፣ መጠንና ጠባይ የተለየ ባዕድ መልክ ያመጣሉ።

በውትድርና፣ በጉልበት ሥራና በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች የሚሳተፉ ሴቶችን መታዘብ ይቻላል። በሴትነትና በወንድነት መካከል የሚዋዥቁ አልያም ጭርሱኑ ወንዲሎ(ወንዲላ) የሚኾኑ አይደሉምንም? ይኼ አካላዊ አቋማቸውስ በወንዶቹ ዘንድ ተወዳጅ ነውን?
የቤት ውስጥ ሥራ ጾታዊ ቁርኝት

በዘመነኛው ስልጣኔ የቤት ውስጥ ሥራ ጾታ እንደማይለይ ይነገረናል። የዛሬን አያድርገውና በድሮው ዘመን ወንዱ ውጪ በእርሻና በሌሎችም ሥራዎች ውሎ ወደቤቱ በሚገባበት ዘመን ሴቶቹ ሙሉ በሙሉ የቤት እመቤት በመኾን የቤት ውስጥ ሥራውን ከሌሎች የቤተሰቡ አባላት ጋር ይፈጽማሉ።
ነገር ግን አኹን ባለንበት ዘመን ሴቷም እንደወንዱ ሥራ ውላ በምትገባበትና የቤት ውስጥ አጋር(የቤተሰብ አባላት) በቀነሱበት ዘመን የወንዱን እገዛ አማራጭ የለሽ ያደርገዋል። እገዛው ግን “ምን” እና “እስከምን” የሚለው ጥያቄ ይኾናል። ምክንያቱ ደግሞ ሰው ሥራን እንዲቀርጽ ሥራም ደግሞ ሰውን ይቀርጻልና የተሳተፈባቸው ሥራዎች ተፈጥሮኣዊ ወንድነቱ ላይ የሚያሳድሩት ጫና የማታ የማታ ወንድነቱ ስቧት የመጣችውን ሴት አያርቃትም ወይ?

የትኛውም ዐይነትሥራ ከመሠራቱ በፊት የአካልም ኾነ የአእምሮ ዝግጁነት የመንፈስ ቁርጠኝነትን ይሻል። ይኼን ዝግጁነት ደግሞ ተፈጥሮ ራሷ በልግስና ትደግፈዋለች።
አስረጅ 1 ፦ የጉልበት ሥራ
ከሥራው በፊት ባለ ዝግጅት፡ የጉልበት ሥራ መሥራትን ስታስብ ቀድሞ በተፈጥሮ የተለገሰህን ጡንቻ ወይም ወደ ጡንቻ ማደግ የሚችል ሰውነት መሰጠትህን አስተውል። ስለዚህም ይኼን ስጦታህን በማበልጸግ ብቻ ራስህን ማዘጋጀት ትችላለህ።
ከሥራው በኋላ የሚደርስብህም የሥራው አሻራ ቀድመህ ስታበለጽገው የነበረውን ሰውነትህን ያደረጅልሃል። በዚህም የአካል ብቃትህ ይጨምራል።በዚህም ከመንጋው ወንድ መሐከል አውራ መኾን የሚችለውን ለመለየት የሴቷ ደመነፍስ በቀላሉ ይጠቀምበታል።

በተቃራኒው ደግሞ ሥራህ ምንም ዐይነት ጉልበት የማይጠይቅ ከኾነና አንተም አካላዊ እንቅስቃሴን ከማድረግ የተቆጠብክ ብትኾን የሰውነትህ እየሟሸሸ ይኼዳል። ሰውነትህም በስብ እየተሞላ በደረት ጡንቻ ፈንታ ጡትና ቂጥ ታወጣለህ።

በአንጻሩ ግን ይኼን የጉልበት ሥራ ሴቷ አትሠራውም ማለት አይደለም። ፈጣሪ ግን ከፍተኛ የጉልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ የሰውነታቸውን ቅርጽ አልሠራውም(ከወንዱ አንጻር) ። እንሥራ ቢሉ ግን ተፈጥሮ ከለገሰቻቸው አካላዊ ቅርጽ፣ መጠንና ጠባይ የተለየ ባዕድ መልክ ያመጣሉ።

በውትድርና፣ በጉልበት ሥራና በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች የሚሳተፉ ሴቶችን መታዘብ ይቻላል። በሴትነትና በወንድነት መካከል የሚዋዥቁ አልያም ጭርሱኑ ወንዲሎ(ወንዲላ) የሚኾኑ አይደሉምንም? ይኼ አካላዊ አቋማቸውስ በወንዶቹ ዘንድ ተወዳጅ ነውን?
አስረጅ 2፦ መግቦት(nurturing)
አቅርቦት(providing) ለወንድ ልጅ እንደኾነ መግቦት(nurturing) ደግሞ በተፈጥሮ ለሴት ልጅ የተሰጠ ነው።እንኳንስ ግዕዛን(ማስተዋሉ)የተሰጠን ሰዎች አይለንም እንሰሶች እንኳን ይኼን ይለያሉ።በመግቦት ቅድመ ግብር የሥራ በፊት ዝግጅት ፈጣሪ ራሱ ሴቷን በአካል ከወንዱ በተለየ ጥበብ አዘጋጅቷታል። ወተትን የሚያፈልቁ ጡቶች፣ ለወት ማምረቻ ሚኾኑ የስብ ስንቆችና የመሣሰሉት ይገኙበታል። በአእምሮ ጥበቧ ደግሞ የልጇን ለቅሶ ሰምታ የረሃብ፣ የበሽታ፣ የፍርሃት፣ የሽንት አልያም የሌሎች ጥያቄዎች መኾናቸውን ትለያለች። በመንፈሷ ደግሞ ስሜተ ስስ መኾኗ ቀድሞ ለሰማቻቸውንና በእውቀት ለለየቻቸው ልቅሶዎች አፋጣኝ መልስ መስጠት ያስችላታል። ለረኃቡ ለቅሶ ምግብ፣ ለጥቃቱ ለቅሶ መከታ፣ ለሕመሙ ለቅሶ መድኃኒት እንድታቀርብ ሲያግዛት ይኼንንም ለማድረግ በቅርብ ርቀት እንድትኾን ግድ ይላታል። በዚህ መልክ እንክብካቤ አግኝተው የሚያድጉ ልጆች ጤናማና ጠንካራ ስለመኾናቸው ምንም ዐይነት ጥርጥር አይኖርም።
እንግዲህ አንዲት ሴት ልጅ ለዚህ መግቦት ለመዘጋጀት ብትፈልግ ፈጣሪ የሰጣትን በመንከባከብ ማበልጸግ ብልህነት ነው።
ድኅረ ግብር ተጽዕኖ ይኼን የመግቦት ሥራ ከሠራች በኋላ በአካሏ፣ በአእምሮዋና በመንፈሷ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ተፈጥሮዋን የሚያፈካ፣ ሴትነቷን የሚያጎለብት ቢኾን እንጂ ለተፈጥሮዋ ባዕድ ጠባይን አያሸክማትም።
በተቃራኒው ምንም እንኳ ለመግቦት የሚኾን ስጦታ ብትይዝ በተለያዪ ምክንያቶች(በሥራ፣ በትምህርት፣ አሻፈረኝም ብላ) ልጆቿን ከመንከባከብ ልትርቅ ትችላለች። ከዚህም የተነሳ ልጆች የአመጋገብ ሥርዓታቸው የተዛባ፣ ጤናቸውም የተቃወሰ ይኾናል(በእናቶች እጅ የሚያድጉና በሞግዚት ክብካቤ የሚያድጉ ልጆች መካከል ያለውን ልዩነት ልብ ይሏል)።

በአንጻሩ ደግሞ ይኼን የመግቦት ሥራ በአቅርቦቱ ላይ ደርቦ ለመሥራት ወንዱ ሲዘጋጅ በውስጡ ያልተሰጠውን ገንዘብ ለማድረግ ሲጣጣር ይስተዋላል። የልጆቹን ለቅሶ ለመስማት ሰምቶም የምን ጥሪ እንደኾነ ለመለየት፣ ይሞክራል ፈጣን መልስ ለመስጠት ደግሞ ቆዳው ስስ መኾን(ስሜታዊ መኾን) ይጠበቅበታል። የልጆቹ ደስታ የሚያፈካው፣ ለቅሷቸው የሚረብሸው፣ ጨዋታቸው የሚያሳቅቀው፣ ለጩኸታቸውም ድንጉጥ፣ ጥፋታቸው የሚያስከፋው እንዳይቀጣቸውም ደግሞ ኾደ ቡቡ ይኾናል።

ብንኖር የሴቶች እኩልነት ለማረጋገጥ ሲባል በቤት ውስጥ ሥራ እየተጠመደ በመጣው ወንድ
ላይ የደረሰው የአካልና የስነልቦና ስልብነት እና የትዳር አደጋ…….. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *