የተኙ፣ የባነኑ፣ የነቁና የደነበሩ ክፍል ፬(የነቁ)

ሳተናው!

በመጨረሻም በዚህ “ሰለጠነ” በሚባል ዘመን የወንዶቹን አንድ ከመቶ የሚይዙት(1%) የነቁት ናቸው። እነዚህ ጊዜያዊውና ጣፋጭ ከኾነው እንቅልፋቸው ምቹ ከኾነውም አልጋቸው ጨክነው የነቁ ናቸው።

ምንም እንኳ የተመቸ አልጋ ላይ ቢተኙ፣ እንቅልፉም ቢጣፍጣቸው ገሃዱ ዓለም ከፊት ለፊታቸው ነቅቷልና(ነግቷልና) ይነሳሉ። ይኼም ገሃዱ ዓለም ውርጭ፣ ዝናብ ፣ ፀሐይ፣ ሐሩር ቢኾንም እርሱን ተቋቁመው ወደ የማይቀረው ጉዳያቸው ይነሳሉ።

እነርሱን ያነቃቸው አስጨናቂ ሕልም(በፈተና የተሞላ ትዳር) አልያም ከውጪ የመጣ ቀስቃሽ ኃይል ይኾናል።

ለነቀቱት ወንዶች እውነት በተፈጥሮ ውስጥ ከፈጣሪ የምትገኝ እንጂ ፓለቲከኞች ጠፍጥፈው የሚጋግሯት፣ የሚኖሩበትም ሕብረተሰብ የሚሰይማት እንዳልኾነች ያምናሉ። እርሷን ለማወቅ፣ ለመጨበጥ፣ ለመኖርም ይጥራሉ።

መማራቸውና ማወቃቸውም ተፈጥሮንና ፈጣሪን ለመረዳት እንጂ በዓለም ውሸት ተደልሎ ለመተኛት ስላልኾነ መርምረው ይቀበላሉ።

ከደረሱበትም እውነት በመነሳት የአባወራነታቸውን ሚና የጠበቁ ናቸው። አባትነታቸውን፣ ባልነታቸውን፣ ወንድነታቸውን እና ራስነታቸውን አውቀው እና ጠብቀው ይኖራሉ። እርሱንም ለመለማመድ የሚያስፈቅዱት፣ የሚያሳውቁት እና የሚለማመጡት ሰው አይኖርም።

ተፈጥሮኣቸውን መቀበል፣ እርሱንም መንከባከብ እና ማሳደግ መለማመዱም ጭምር የተፈጥሮን እውነት ገንዘብ ማድረግ(ማወቅ) ያስችላቸዋል። ከዚህም የተነሳ በስሜት ከመወሰን፣ ከብዙኃኑ ጋር ከመነዳት ሲጠበቁ፤ ሰዎች(ራሳቸውም ቢኾን) ደስ የሚላቸውን ሳይኾን ትክክለኛውንና መራራውን እውነት መቀበል/መፈጸም ይመርጣሉ።

በዚህ ዐቢይ ክፍል ውስጥ የምናገኛቸው ወንዶች ከጣፋጭ እና ደላይ ኃሳቦች፣ ከምቾት ኑሮም ይልቅ ለመራርና ጥሬ እውነቶች፣ በፈተና እየተሠራ ለሚያድግ ሕይወት ያደላሉ። ከዚህም የተነሳ ለራሳቸው ሕይወት እንደማይራሩ ኹሉ ለዚህ በጎ ዓላማ በቤተሰባቸው ላይ ይጨክናሉ(ጨክነው ያስጨክናሉ)።

አንድም እነዚህን እውነቶች ገንዘብ(የግል) ለማድረግ ሥነ-ስርዓት ይሻልና የሥነ-ስርዓት ሰው ናቸው። እነርሱም አብሯቸው ከሚኖረው ሰው ይኽን ይጠብቃሉ። ድርጊታቸው ከ”ምንችግራለው” እና ከ”ምናለበት” የራቀ ከእውቀትም የተነሳ ነው።

ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *