የተኙ፣ የባነኑ፣ የነቁ እና የደነበሩ ክፍል፫(የደነበሩ)

፫ኛ የደነበሩ

ሳተናው!
እነዚህ ወንዶች ከእንቅልፋቸው በአንድ ገሐዳዊ እውነታ አልያም አስፈሪ ሕልም ከተኙበት ደንብረው የፈረጠጡ ናቸው።

ይሕ ለችግሩ መፍትሔ መስጠት ሳይኾን ደመነፍሳዊ የኾነ ችግሩን የመሸሽ ውሳኔያቸው ራሳቸውንም ኾነ ሌላውን ይጎዳሉ።

በእንቅልፋቸው ሳሉ የደነበሩ ሰዎች ከአልጋቸው ተስፈንጥረው በመነሳት መድረሻቸውን ሳያውቁ በር ከፍተው እስከመሮጥ ይደርሳሉ ።

ልብ አድርጉ! የሚያስደነብሯቸው ሁለት ነገሮች ናቸው፦አንደኛው ውጪያዊ ሲኾን ሌላኛው ደግሞ ቀድመው በመረጡት እንቅልፍ ውስጥ የተከሰተ ሕልም ነው።

እነዚህ ወንዶች እንግዲህ ስለተፈጥሮኣዊ ጸጋችን፣ በሁለቱ ጾታዎች መካከል ስላለው ልዩነት በዚህም ልዩነት የተነሳ ስላለን ሚና ሲነገራቸው ለመስማት ፈቃደኛ አይደሉም።

ከተፈጥሮ እውነት ከፈጣሪም ስርዓት(ትዕዛዝ)ይልቅ የአመንዝራዋን ዓለም የ”ጾታ እኩልነት” አምነው በዚህም እምነት ተጠርንገው የጠፉ (የተኙ) ናቸው።

ይኹንና አንድ ቀን ዓለም እንደሰበከችላቸው እና እንደጠበቁትም ሳይኾን ያልጠበቁት፣ ለማመን የሚከብደው፣ ለመቅመስም የሚመረው ሐቅ አፍጦ ሲመጣ ይበረግጋሉ፤ ይደነብራሉም።

አስረጅ፦ ሚስትህን አንተ ትወዳት እርሷም ታከብርህ ዘንድ የሠራን፣ ያበጀን፣ የፈጠረን፣ በደንብም የሚያውቀን ፈጣሪ የሰጠን መመሪያ ነው። ከዚህም የተነሳ ወንድ ልጅ በተፈጥሮው መከበርን ሲሻ ሴት ልጅ ደግሞ ፍቅር(መወደድ) “ምግቧ” ነው።

ይኹን እንጂ ዓለም ግን ይኽን መለኮታዊ ቃል በስልጣኔ ስም አጣማ “ተከባበሩ፣ ተዋደዱ” እንጂ “አክባሪ ተከባሪ፣ ወዳጅ ተወዳጅ የለባችሁም” ስትል ሚዛን “ላደላደል” ትላለች።

ምስኪኑ ወንድ ታዲያ ይኽን ውሸት አምኖ ይቀበላል። ነገር ግን መከበር መፈለጉ ተፈጥሮኣዊ ነውና ከሚስቱ ክብርን ሲሻ አያገኘውም። በቤታቸውም ከእርሱ ይልቅ ወንድ ልጁ በሚስቱ ዘንድ(በልጁ እናት) ክብርና ሞገስ እያገኘ ይመጣል(ቤትህን ታዘብ)።

ይኽም ያበሳጨዋል፣ ብስጭቱ ተጠራቅሞም አንድ ቀን ይፈነዳል።

ሌላ አስረጅ፦ ቤትህን ቆፍጠን ብለህ ምራ ፣ ሚናህን ለይ፣ ማዘዝንም ተለማመድ ስትለው በራድ ኾኖ ይኖራል። ሚስቱ ደግሞ ተፈጥሮዋ ቆፍጠን ያለ፣ የፈለገውንም መውሰድ ለሚችል ወንድ ትማረካለችና ለእርሱ ያላት ፍላጎት እየቀነሰ ከ”ዱርዬ” ስትገጥም ይበረግጋል ይደነብራልም።

እነዚህ ወንዶች መተኛቱ ይበቃችኋል ተው ተነሱ ስትሏቸው እንቅልፋቸውን (የዓለምን ድለላ) አምነው ይተኛሉ፤ ሲነቁም ይደነብራሉ።

፬ኛ የነቁ .. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *