የተኙ፣ የባነኑ፣ የነቁ እና የደነበሩ ክፍል ፪(የባነኑ)

፪ኛ የባነኑ

ሳተናው!
የባነኑ ሰዎች ከመኝታቸው በደመነፍስ ተነስተው ለመንቃት የሚሞክሩ ናቸው። ነቅቶ መነሳት አልያም መተኛቱ እንደሚሻል ያልወሰኑ ናቸው።

እነርሱን ያባነናቸው ይመቸናል፣ ይሻለናል ብለው መርጠው ሲያጣጥሙት ከነበረው እንቅልፍ ውስጥ የታያቸው መጥፎ ሕልም(ልክ ነን ብለው በኼዱበት የትዳር መንገድ የገጠማቸው ፈተና) አልያም ከውጭ የተሰማቸው ነገር ይኾናል።

ይኹን እንጂ መባነናቸውን ተጠቅመው ወደ ዓለም ንጋት ወደ ቀኑም እውነት አይነሱም። የመንቃታቸውን ጥሩ አጋጣሚ እንዳይጠቀሙ ግን የቀደመው የእንቅልፍ ምቾት ፣ የመባነኑ ፍርሃት፣ የመንቃቱም ስንፍና ባሉበት አሥሯቸዋል።

ይኹን እንጂ ይኽንን ድካማቸውን ከማረም ይልቅ ለስንፍናቸው “መንፈሳዊነት”፣ ለፍርሃታቸውም “ፍቅር” የተሰኙ የዳቦ ስሞች ሰይመው ከአልጋው ምቾታቸው ጋር አስሯቸዋል።

ከተኙት ግን ቢያንስ የገሃዱ ዓለም ሐቅ አባናቸዋለችና ሌላኛውን የሕይወት አማራጭ ለመታዘብ እድሉን አግኝተዋል።

በአባወራ ገጽ ላይ የሚያነቧቸው ጽሑፎች ከነበሩበት እንቅልፍ ያባነኗቸው ወንዶች ከ10-15 በመቶ ይኾናሉ። እነዚህ ወንዶች እውነታዋ ብልጭ ስትልላቸው ተነስተው የልባቸውን በር ከፍተው ማስገባት ያልቻሉ ናቸው።

ይኽም እንዴት ነው ቢሉ በትዳራቸው ወንድ ልጅ መሪ ራስ እንደኾነ የተረዱ ነገር ግን ይኖሩት ይተገብሩትም ዘንድ ግራ የገባቸው ናቸው። ግራ የሚጋቡትም ስለ ሦስት ነገር ነው፦

፪-፩ ስለ አልጋቸው ምቾት
አልጋ ያልኩት የቀደመ የእንቅልፍ ሕይወታቸውን ነው። ምንም እንኳ ከግጭት ነፃ ባይባልም ነገር ግን በጊዜያዊ ምቾቱ ከቀሪዎቹ ሁለቱ ተመራጭ ስለኾነ ነው። ያባነናቸው ነገር(ሐቅ)ሊነቁለት፣ ሊከተሉት የተገባ ከአልጋቸውም የተሻለ ስለመኾኑ ይጠራጠራሉ።

፪-፪ ስለፍርሃታቸው
ከባነኑ በኋላ ለሚወስዱት እያንዳንዷ እርምጃ ስለሚያስከትለውም መዘዝ እርግጠኛ አይሉምና ይፈራሉ። ከአልጋቸው መውረድ በሩንም መክፈት ሲያስቡት ገና ልባቸው ይመታል።

እነዚህ ወንዶች ሚስታቸውን የመምራቱን ነገር ይሰሙና(ያባነናቸውን) ሊተገብሩት ሲያስቡ ይፈራሉ። “እምቢ” ብትለኝስ፣ “ብንጣላስ”፣ “ብትፈታኝስ” እና የመሳሰሉትን እያሰቡ የሰሙትን እውነት ከመኖር ይታቀባሉ።

ቁምነገሩን ሲያስቡት በፍርሃት ይዋጣሉ። ታዲያ ይኽችን ፍርሃታቸውን “እኔ በፍቅር አምናለሁ” ብለው ይሸፍኗታል።

፪-፫ ስለስንፍናቸው
ከባነኑ ተፈጥሮኣዊውን እውነት ከሰሙ በኋላ ከተመቸው አልጋቸው(ከነባሩ ሕይወታቸው) ለመላቀቅ የሰነፉ ናቸው።

የወንድ ልጅን ሚና ሰምተዋል ነገር ግን ራሳቸውን በዚያ እውቀት ለማነጽና ለመሥራት ስንፍና ያሠራቸው ናቸው። መለወጡ (መንቃቱን) ይፈልጋሉ ነገር ግን ስንፍና ወርሷቸዋል ጥረቱም የላቸውም ምናልባትም ሰማያዊ ተአምር ይጠባበቃሉ።

፫ኛ የደነበሩ…ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *