የተኙ፣ የባነኑ፣ የነቁ እና የደነበሩ

ሳተናው!

ዐዲሱን ዓመት እንዴት ለመቀበል አስባችኋል? ራስን ለመለወጥ የግድ ዘመን መለወጥ(ጠብቆ ይነበብ) ባይኖርበትም እንኳ ከዐዲስ ዓመት ጋር ግን ዐዲስ ዕቅድ መያዝ የተለመደ ነው።

ላለፉት ሀያ ስምንት ወራት ከአንድ መቶ ሀምሳ በላይ ጽሑፎችን በአባወራ ገጻችን ላይ አንብባችኋል። እነዚህን ጽሑፎች ልዩ የሚያደርጋቸው ደግሞ ሁሉም ወንዶች ተፈጥሮኣዊ ጸጋቸውን እንዲያውቁ፣ እንዲጠብቁ፣ እንዲንከባከቡ፣ እንዲያሳድጉ ታስበው መዘጋጀታቸው ነው።

በዚህ ወቅት በተለይ የጾታ “እኩልነት”፦
? ተፈጥሮኣዊውን ዋልታነታችንን በሻረበት(ወንድና ሴት)
? የወንድና የሴትን ሚና በደመሰሰበት
? የፈጣሪን ትዕዛዝና ስርዓት ባፈረሰበት ጊዜ በመኾኑ የ”አባወራ” ገጽን ወቅታዊ ሲያሰኘው

ጉዳታችንንም ስናስብ፦
?ጾታዊ ግንኙነታችን መሻከሩ
?መሠረታዊውና ጥንታዊው ትዳር መነቅነቁ
? ትውልዳችን ፍዝ(በራድ)፣ ሰነፍ፣ ሱሰኛ፣ ጥገኛ፣ ሴሰኛ፣ ሰበበኛ፣ ስሜታዊ.. መኾኑ ገሃድ የወጣ ሐቅ ነው።

ይኹንና እነዚህ ጽሑፎች ያሉትን ችግሮች እየጠቆሙ መፍትሔ ነው ያሉትን መራር መድኃኒት ሲጠቁሙ፣ ተፈጥሮኣዊ እውነትንም ለማስጨበጥ ሲሞክሩ ቆይተዋል። እኔ ግን በተለያየ አጋጣሚ ያገኘኋቸውን ወንዶች ከመራሩ እውነት አንጻር እና ከግብረመልሳቸውም በመነሳት በአራት ዐበይት ክፍሎች ለይቼ አስቀምጫቸዋለሁ።

እነርሱም፦ የተኙ፣ የባነኑ፣ የነቁ እና የደነበሩ ናቸው።

፩ኛ የተኙ

ይኽ ክፍል ስገምት ከሰባ አስከ ሰማንያ ከመቶ የሚኾኑት ወንዶች የሚገኙበት ነው። እነዚህ በዘመን አመጣሹ “የጾታ እኩልነት” አጀንዳ ተጠልፈው፣ በስልጣኔም ሰበብ ታዝለው የተኙ ናቸው።

አኹን ከተኙበት አልጋ ውጪ የተሻለ ያለ የማይመስላቸው፤ ቀስቅሳችሁ ስለ ገሃዱ ዓለም ብትነግሯቸውም ስለ አልጋቸው ምቾት፣ ስለሙቀቱ የሚነግሯችሁ፤ ቆመው እንዲኼዱ እንዲሠሩ፣ እንዲለወጡና እንዲለውጡ ቢፈጠሩም የመኝታውን ምቾት የመረጡ ናቸው ።

በ#አባወራ ገጻችን ላይ አጽንዖት ሰጥተን ከምንወያይባቸው መሠረታዊ/ተፈጥሮኣዊ እውነቶች ውስጥ አንዱ ወንድ ልጅ የቤቱ መሪ የሚስቱ ራስ መኾኑን ነው። ይኹን እንጂ እነዚህ የተኙ ወንዶች ከዚህ ተፈጥሮኣዊ ሐቅ ይልቅ የዓለምን “የእኩልነት” ስብከት ተቀበለው በዚያም መንገድ ትዳራቸውን ለማስኬድ የሚሞክሩ ምስኪኖች ናቸው።

በእነርሱም እይታ “የፍቅር ጥጉን እና የስልጣኔም ወጉን” ይዘነዋል ብለው ስለሚያስቡ ተፈጥሮኣዊውን ሐቅ ፣ መለኮታዊውንም ትዕዛዝ ሰምቶ ከመፈጸም ይልቅ የውሸታሟን ዓለም ልፋፌ ያምናሉ፣ ይቀበላሉ ይፈጽማሉም።

እነዚህንም ውሸቶች ከልጅነታቸው ጀምረው በየመገናኛ ብዙኃኑ፣ በዘፈኑና በፊልሙ የሚለቀቁትን “የጥበብ” ሥራዎች እየሰሙ አድገዋልና አንድም በትምሕርት ተምረዋልና የሚያምኑት እነርሱን የሚኖሩትም የነገሯቸውን ነው።

ይኹን እንጂ ከተፈጥሮ ስርዓት ውጪ ይኖራሉና የድካማቸውን ፍሬ አያገኙም።

፪ኛ የባነኑ…ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *