የትዳርህ ሸክም ሙሉ ለሙሉ ያንተ እና የ..አ..ን..ተ ነው!

ልብ በል! የትዳርህ ስኬት ሙሉ ለሙሉ ያንተ እና የ..አ..ን..ተ ኃላፊነትና ግዴታ ነው!! አንተ በትዳርህ ውስጥ ያለውን የማቀድ፣ የመምራት ሚና ስታውቅ የፍቅር ሕይወትህ የስኬት ጉዞ ቀላል እንደሆነ ትረዳለህ። ነገር ግን አሁን ያለው የተሳሳተ ወንድነትን የሚሰልብ(የሚያከስም) ጾታዊ ግንዛቤ እና ልክ ባልሆነ መንገድ አርአያ የሆኑን አባቶች(ወንዶች) ዛሬ ላለነው ወንዶችም ሆነ ለትዳር አጋሮቻችን(ሴቶች) የትዳርን ስኬት አርቀውብናል።

ትዳርህ ሙሉ ለሙሉ አንተ ትከሻ ላይ ነው!!

አንተ ወንድሜ እልሃለሁ፦ትዳርህ ስኬታማ እንዲሆን ትፈልጋለህ? ስሜታዊ ሆነህ በዘፈን፣ በፊልም፣ በትያትር፣ በልብወለድም መጽሐፍ በአጠቃላይም በመገናኛ ብዙኃኑ ለትርፍ ተብለው የሚሠሩትን ጽንሰ ኃሳቦች አትከተል። እነርሱ የሕዝብን ስሜት ኮርኩረው፣ ስስ ብልቱንም ነክተው ብዙ ገንዘብ እና ዝና ለማትረፍ ይሰራሉ እንጂ ለትውልዱ እውነትን ነግረን ብንከስርም እንከሰር አይሉም።

ዛሬ ላይ የምትኖረው ኑሮ የትላንት ውሳኔህ የጥረትህም ጅማሮ እንደሆነ አስብ።ዛሬ እያገኘህ ላለኸው ውጤት(በሥራ መስክ፣ በትምህርት ቤት፣…እና በሌሎችም የተሰማራህባቸው መስኮች) የትላንቱ ውሳኔህና ጥረትህ ትልቁን ሚና ይጫወታሉ። በዚህም ትይዩ ዛሬ ላይ የሚታየው ትዳርህ የአንተ የትላንት ውሳኔህና ድርጊትህ ድምር ውጤት ነው። ለውጤትህ አለማማር በሰው አታሳብብ፦ በጓደኛ፣ በቤተሰብ፣ በሃብት፣ ኑሮን ልታሸንፍበት በተማርከውና ዓለም የምስክር ወረቀት፣ ዲፕሎማ፣ዲግሪ፣….. ብላ በሰጠችህም ጥበብ በተለይም ደግሞ በሚስትህ አታሳብብ። ሰበቦችህ በበዙ ቁጥር መፍትሄ ፈላጊ፣ መፍትሄ አመንጪ እና የመፍትሄውም አካል መሆንህ ይቀርና ችግሩን አባባሽ፣ ከድጥ ወደ ማጥ ተጓዥ ሆነህ ታርፈዋለህ።

ስለዚህ፦ ስለዚህማ ወደራስህ መለስ ብለህ ራስህን መርምር
1ኛ ትላንት የወሰንከው ውሳኔ ትላንት ያደረግከው ድርጊት በእውነተኛ እና ተፈጥሮአዊ እውቀት ታጅቦ ቢሆን ለዚህ ባልበቃህ ነበር። እናም ችግሩ ያንተ ነው።
2ኛ “እኔማ ብዙ ተምሬ፣ ሠልጥኜ፣ አውቄ ነው ወደ ትዳር የገባሁት ችግሩ ያለው ከሚስቴ እንጂ” አትበል። እርሱም ቢሆን ያው ያንተ የአለማወቅ የመሃይምነት ስህተት ነው። ብታውቅማ ኖሮ ከመጀመሪያው ከጥንስሱ ከምርጫ መስፈርቶች ሁሉ የሚልቀውን “የአባቷ ልጅ ነች ወይ?” የሚለውን ባስቀደምህ ነበር። ይህን የምርጫ መስፈርት ብታስቀድም ኖሮ ሌላው የፍቅር ጥበብ ሁሉ አልጋ ባልጋ በሆነልህ ነበር።
3ኛ “እንዴዬ እኔማ ‘የአባቷን ልጅ’ ነው የመረጥኩት ውጤቱ ግን እንደጠበኩት አልሆነም” ካልከኝ ደግሞ አንተ የ”አባቷን ልጅ” ከመምረጡ እንጂ ከመያዙ፣ ከመምራቱ፣ እና ከመንከባከቡ መሃይም ነህ እልሃለሁ።

ልብ አድርግ! ያለምንም ማለዘቢያ ቃላት እንዲሁ እንደጠነከረ፣ ያለምንም ማጣፈጫ እንዲሁ እንደመረረ፣ ያለምንም ሽክርክሪት በቀጥታ “አንተ” እያልኩ የማወራህ ስለምወድህ ነው።
በቃ እወድሃለሁ!!! ላተርፍብህ፣ ልነግድብህ፣ ልመጻደቅብህ ሳይሆን አንተ ስትለወጥ በእውነት ደስ ስለሚለኝ፣ ያንተም ትርፍ ትርፌ ስለሆነ፣ ትውልድንም ማትረፍ ግዴታዬ ነው ብዬ ስለማምን፣ ሀገሬንም መታደግ በደምና በአጥንት ማህተም ከአባቶቼ የተቀበልኩት አደራ ስለሆነ እንዲህ አልኩህ።

መጠንከር አለብህ፤ መጨከን አለብህ፤ መበርታት አለብህ፣ ጣፋጭ፣ ቀላዋጭ፣ እና አሳሳች የሆነውን የዓለምን አሳሳች ወሬ ትተህ በፈተና የተሞላውን፣ መራሩን፣ ግን ደግሞ ቀጥተኛውን፣ ተፈጥርአዊውን እውነት ልትጋፈጥ ግድ ይልሃልም ብዬ ስለማምን ነው።

ወንድሜ! በዓለም የኪሳራ ጽንሰ ኃሳብ ልብህ አይጥፋ! ኃላፊነትህ ትልቅ፣ ሸክምህም ብዙ፣ መንገድህም ሩቅ ነው።ለምን ጊዜህን በእንቶ ፈንቶ ታሳልፋለህ!?

አስተውል! ትዳርህ የአንተ እና የ..አ..ን..ተ.. ኃላፊነት ነው።

ይህ አሁን የምንኖርበት ዓለም ተፈጥሮአዊ እውነትን አማናዊ እውቀትን ይዞ ከመኖር ይልቅ እንሰሳዊ ስሜቱን ብቻ እየተከተለ ዓላማውን ስቷል። አንተ ግን አባወራ ነህ ስሜት ቢኖርህም ዓላማህን የማትስት፤ እርሱም የመኖርህ ምክንያት ነው።…… ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *