የአባቷ ልጅ(የአባወራው እጮኛ) ስትገለጥ

 

አዎን! ይህች የአባቷ ልጅ ነች ያልናት ሴት የአንተ የአባወራው ትክክለኛ ምርጫ ነች። እንዴት? ብትለኝ አንተ በአባወራ ማንነት ታንጸህ ስትገነባ ሥነ-ስርዓትን ወይንም የኑሮን ቅጥ ለሚስትህም ሆነ ለልጆችህ ማስተማር፣ እንዲከተሉትም ማድረግ ያንተ እና ያንተ ግዴታ ስለሆነ ነው!!!! ከዘረጋኸው ሥርዓት ካስቀመጥክላቸው ቅጥ ሲወጡ ግን በምክር ጀምረህ በተግሳጽ ደግመህ በቅጣት አሠልሰህ ታዛዥ እና ግብረገብ ቤተሰብ ትገነባለህ!!!

ሲቀጥልም ኃላፊነት፣ የሚሰማው ሀገሩን ኃይማኖቱን ተረካቢ፣ ወገኑን ወዳጅ ሰውን የሚያፍር ፣ፈጣሪውን የሚፈራ፣ ሽማግሌ የሚያከብር ትውልድ የማነጽ ሀገራዊም፣ ኃይማኖታዊም፣ ከሁሉ በላይ ደግሞ ተፈጥሮአዊ ግዴታ እና አደራ አለብህ!!!!!!

ታዲያማ ትዳርን ስታስብ አንድም የፈጣሪን አንድም የሀገርን አንድም ደግሞ ፈጣሪህን ያወቅህበትን ኃይማኖት አደራ ሳትረሳ የምታግዝህን ሴት መምረጥ ደግሞ ትልቁ የህይወትህ ምርጫ እና ውሳኔ ነው።ይህን ጊዜ ነው የአባቷ ልጅ ትገባሃለች የምልህ።

ይህቺ ሴት እንደ”ዘመነኞቹ” ለቤታቸው እንግዳ ደጅ ደጅ ባይ፣ ሙግት ወዳጅ እንደሆኑት አይደለችም፣ እንደ እናታቸው ስኬታማና የባላቸው አጋዥ ከመሆን ተፎካካሪ እንደሚሆኑትም አይደለችም። እርሷስ የአባቷ የሥርዓቱ፣ የቅጡ፣ የቅጣቱ ውጤት የሆነች፣ ለእናቷ አጋዥ ክንድ፣ ታዛዥ ልጅ፣ የሙያዋ ወራሽ፣ስልጡን በጠባይዋ ስንዱ በቤቷ የሆነች ነች።

ይህች የአባቷ ልጅ ታዲያ አባቷ የወንድ፣ የጥንካሬ ፣ የአሸናፊነት፣ የደህንነት የመሳሰሉት ምሳሌ ነውና እርሱንም ደግሞ የወደፊት ባሏን በዓይነ ሕሊናዋ ትቀርጽበታለችና አንተ አባወራ ስትሆን ይህን ቦታ ትወስዳለህ። በዚህም ከመጀመሪያው ያንተ የቤቱ አባወራነት የተረጋገጠ የቤትህንም ሥርዓቱን፣ ቅጡን የርዕይህንም መንገዱ ለማሳየት ባለሙሉ ሥልጣን ትሆናለህ። ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ግን “እርሱን አዛዥ ናዛዥ ያደረገው ማነው እኔም እኩል ባለመብት እኮ ነኝ” እየተባለ የተናቀ ባል እና ሥልጣን አልባ “አባወራ” ትሆናለህ፤ መልስህም ሁሉ “ቆይ እስቲ ላማክራት” ይሆናል።

አንተ በቤትህ ባለሙሉ ሥልጣን መሆንህ ምን ጥቅም አለው? እውነትስ የዛሬ “የሴቶች መብት ተሟጋች” ነን እንደሚሉት የቤተሰብህን መብት(በተለይም የሚስትህን) መጨፍለቅ ነውን?
መልሱ፦አይደለም!!!! አይደለም!!!ነው።

ይኸውልህ ልጄ ዘመኑ ግልብ ስለሆነ አንተም ግልብ ንባብ ሳትጠቀም በጥሞና ተከተለኝ። አባቶቻችን “ነገርን ከሥሩ ውሃን ከጥሩ” ይላሉና እኔም ለነገሩ ሁሉ አስገኚው ፈጣሪ ከሰጠህ ተፈጥሮ ልጀምርልህ። ወንድ ልጅ ሲፈጠር ከስልጣን ጋር ነው። ዓለምን እና ውስጧ ያለውን ሊነዳ፣ ሊገዛ፣ ሊያስተዳድርም ለፍላጎቱም ሊያውል ከፈጣሪው በታች ባለሙሉ ስልጣን(እንደራሴ)ነው። ይህ ውስጥህ የተሳለ ተፈጥሮህ ነው።ዓለም በድምጽ ብልጫ ሲያሻት የምትደግፈው ሲያሻትም የምታወግዘው አይደለም። አንተ ራስህ እንኳ ብትፈጽመው ታዛዥ በትሸሽ ግን ተወቃሽ ትሆናለህ እንጂ እውነትነቱን ልትጠራጠር አልተጠራህም።

አንተ ታዲያ ባለሙሉ ስልጣን መሆንህ ቤትህን በሥረዓቱና በቅጡ ለማስተዳደር በቅብብሎሽ ለመጣውም አደራ እና ኃላፊነት የበኩልህን ለመወጣት ይረዳሃል። በዚህም ቤተሰብህ ቅጠኛ፣ የቤተሰብህም አባላት በየተሰማሩበት ተግባር(ምንም ትንሽ እና ትልቅ ቢባል ቅሉ)ለቤቱ መቆም ጠቃሚ በመሆናቸው ራሳቸውን ባለዋጋ በማድረግ ለከፍተኛ የስነልቦና ጥንካሬ ይበቃሉ። በአንጻሩ ግን ያንተ ስልጣን የስም ከሆነ ፣ቤትህን ሥርዓት ማስያዝ ለስልጣን ሽኩቻ ከዳረገህ፣ ቤትህ ቅጥ ያጣል ብዙዎችም የሚያማርሩት የዘመኑ የፍቅር ሕይወት ነቀርሳም ቤትህ ጎጆ ይቀልሳል።

ዛሬ ላይ ታዲያ ይህንን እውነት “ጨቋኝ” ነው ብላ መቀበል የማትፈልገው ዓለም ህልውናዋን ለሚፈታተን ባልተማረውም ሆነ ተማረ በምንለውም የህብረተሰብ ክፍሏ ለሚፈጸም ሥርዓት አልበኝነት፣ ፍቺ(የጋብቻ) ፣አባቱን ወይም እናቱን ለማያውቅ ወይም ወላጅ(አሳዳጊ) አልባ ትውልድ፣ የትውልድ እርካታ ቢስነት እና ተስፋ ቆራጭነት እንዲሁም ሌሎች ጥፋቷን(ሞቷን) የሚያፋጥኑ እውነቶች ለመቀበል(ለመጋት) ተገዳለች(ትገደዳለች)።

ይህች ሴት(የአባቷ ልጅ) ታዲያ በተገራችበት ጠባይ ለአባቷ የተማረከች(በታዛዥነት) በአባቷ የተማረከች (በፍቅሩ) ነች። አንተ የወንድነት ክብርህን ጠብቀህ ብታገባት ምርኮነቷ ላንተም ይቀጥላል። ለአባቷ ያልተማረከችው ግን ሺህ ጊዜ ወደድኩህ ብትልህ ለእርሷም ልትገልጸው በሚቸግራት መልኩ ላንተ አትማረክም። የሴት ልጅ በትዳሯ ለባሏ መሰጠት ወይም መማረክ ቀድሞውኑ ወላጆቿ ቤት ከአባቷ ጋር የነበራት ግንኙነት ይወስነዋል።

ይህ ምርኮ በዘፈን፣ በጨዋታ ያለ የፌዝ አይደለም ከልብ ከውስጥ የሆነ በዘመናት ኺደት አባቶች በሴቶች ልጆቻቸው ላይ የሚያሳድሩት ምርጥ የሴት ልጅ ስብዕና እንጂ። ምንም እንኳ ብትወድህ ለአባቷ ጥሩ ቦታ የሌላት የማታከብረው ሴት(ስለምወደው ነው ብትልህም) ልቧን አትማርከውም።

አንተም ብዙ ሴቶች የማማለል፣ የማውጣት ልምድ ቢኖርህም ልቧ ምርኮህ ካልሆነ ድካምህ ሁሉ(በተለይም ወሲባዊው) ከንቱ ነው። የእርሷ ባንተ ላንተ መማረክ በትዳር ሕይወታችሁ ውስጥ በተለይ በወሲብ እርካታዋ(ያንተውማ ቀላል ናት) ወደር የለውም። ይህ ደግሞ በራሱ ለትዳራችሁ ገንቢ አንድምታ አለው። ግን እንዴት?…….የሳምንት ሰው ይበለን ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *