የአባቷ ልጅ ላንተ መማረክ ያለው ወሲባዊ አንድምታ

የአባቷ ልጅ የሆነች ለአባቷ መማረክን መሰጠትን ተለማምዳለችና አንተን የሕይወት አጋሯ ፍቅረኛዋን ስታገኝ ይህ መሰጠት ለአንተ ይሆናል። ይህ ታዲያ በትዳር ሕይወታችሁ ውስጥ በተለይም ወሲባዊ ዳራውን እናያለን።
በቅድሚያ
የሴት ልጅ ወሲባዊ እርካታ ፍጹም አእምሮአዊ እንደሆነ ታውቃለህ? ምንም እንኳ የእርሷም ግምት፣ ምኞት፣ ጥረት፣ እና ስሜት ስኬትን ቢፈቅድም ውጤታማ የሚሆነው ግን ሙሉ በሙሉ አእምሮአዊው በሆነው መሰጠት (መማረክ) ነው።
>ግምት አልን “እስከዛሬ ይኼ፣ ይኼ አላሳረፈኝም(አላረካኝም) እንዲህ አይነቱ ሳይሻል አይቀርም ” ስትል፦በተለይ በዚኽ ስር ሴቶች ላለመርካታቸው ምክንያቱ የባላቸው አካላዊ ትንሽነት ነው ብለው ይገምታሉ(ፍጹም ስህተት ነው)
>ምኞት አልን “ይኼ ክንድ ቢያቅፈኝ፣ እርሱ ቢተኛኝ” ስትል፦ በእርካታ አለማረፋቸውን ብቻ አስበው በተለያየ ጊዜ ከተለያየ ወንድ ጋር መውጣትን ያስባሉ (እርካታ በአንድ ወንድ እና በአንዲት ሴት ብቻ ምሉዕ መሆን ይችላል-ወደፊት የምናየው)
>ጥረት አልን ወደ እርካታ ማማ የሚደረጉ ማንኛውንም ስነልቦናዊ እና አካላዊ(ስጋዊ) መውተርተሮችን(ሴቶች አእምሮአቸው መሰጠትን ሳይለማመድ ካደገ ሌላው ኹሉ በድንጋይላይ ውኃ ማፍሰስ ነው)።
>ስሜት አልን ለእዛ ለተወደደ ወንድ የሚሰማ ደስ የሚያሰኝ በተለይም ወሲባዊ ስሜቶች ሁሉ ።

እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው መንገዶች ወንዱም ኾነ ሴቷ በተሳሳተ መልኩ በተራክቦ ለሚገኘው እርካታ ጠቃሚ እና ወሳኝ ናቸው ብለው ያስባሉ ነገርግን ፍጹም ስህተት ነው። አንተ ትደክማለህ፣ ትገነባለህ እርሷ ትንዳለች፤ “ምን ወደድኩህ” ብትልህ ብዙ ብትደክሙም አእምሮዋ አንተን አምኖ እርሷን አይሰጥህም(ይኽ ከእርሷ የእውቀት ድርጊት ውጪ በደመነፍስ የሚኾን ነው)። እርሷም በተራክቦው ኺደት ውስጧ ሲጠቀለል፣ ሲቆለል፣ ሲታመስ እና ሲታመቅ ከቆየው ውጥረት ነጻ አትወጣም። ይኽ ከታመቀው የተራክቦው ስሜታዊ ውጥረት አለመላቀቋ ታዲያ ለድብርት፣ ለኩርፊያ፣ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ለኾነ የግጭት ምክንያት ይዳርጋታል(ችግሯ ከላይ ያየነው ፣የምትናገረው ግን ሌላ ይሆናል)።
እርካታው ቢሳካም ደግሞ ለሴቷ የማያሳርፍ፣ጥምን የማይቆርጥ ከወዳጇ ጋርም የፍቅር ጉድኝት(intimacy) የማይፈጥር ባዶ የስጋ ድካም ይኾናል።
የአባቷ ልጅ የኾነችው ግን አእምሮዋ ከእነዚህ ከጠቀስናቸው ወጥቶ መማረኩ(መሰጠቱ) ላይ ያተኩራል። ይኽ ሲኾን ካንተ ስጋዊ ልፊያ ቀድሞ ድምጽህ ብቻ የእርካታን ጉዞ የሚገምስላት፣ ትንፋሽህ ሰውነቷን “ውርር” ፣”ውርር” የሚያደርጋት፣ስትነካት ልቧ ስውር የሚልባት፣ ስትደርስባትማ ዓለሟ አስር የሚኾንላት ትሆናለች። እንግዲህ አንተ አባወራው ቤትህንን በቅጡ ትመራበት ዘንድ ሚስትህንን የምትመርርጥበት የመጀመሪያውና ወደር የማይገኝለት መስፈርት ነው። ናፖሊዮን ኺል የተባለው ጸሐፊ እንዲህ ይላል አንተ በሕይወትህ ከምትወስናቸው ወሳኔዎች ውስጥ ትልቁ ውሳኔ ቀሪ ዘመንህን አብረህ የምትኖራትን ሚስት መምረጡ ነው ይላል።
ልብ አድርግ ለአባቷ ታዛ፣ በአባቷ ተገስጻ፣ ተመክራ፣ ተቆንጥጣ ፈርታው ያላደገች እንዳውም ደፍራው፣ ክብር ከሌላት ዓለም ግን ካጨበጨበችላት “ቆንጆ” የአባቷ ምክር የመራት፣ ቁጣው የመለሳት፣ተግሳጹ ልቧን የገዛት፣ ቁንጥጫው የጠበቃት፣ፈርታው እርሱ ግን ጀግና የኾነላት “ፉንጋ” ትሻልኻለች። ያቺ ጥረትህ ፣ድካምህ ላይ ውኃ የምትቸልስ ውስጧ ለእርሷም እንቆቅልሽ በኾነ ምክንያት የማይማረክልህ፣ የማይጨበጥልህ፣የማያርፍልህ ለዚህም አንተን የምትከስህ፣ ስታሳዝንህ ኖረህ ሲያሳዝነኝ ኖረ የምትልህ፤ ይኽቺ ግን አይደለም ጥረትህን ኃሳብህን፣ አይደለም ድርጊትህን ዕቅድህን የምታደነቅልህ፣ለእርሷ ጀግና ሰው፣ ምርኮ የተገባህ፣ ስለዚህም የምትሰጥህ ፣በትንሿ ጥረትህም እርፍ የምትልልህ ናት። ብቻ ይቅናህ …..ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *