የአባቷ ልጅ

የመጽሐፉ ርዕስ፦ የአባቷ ልጅ

ቅጽ ፩

(ወንዶች ኹሉ ሊያነቡት የሚገባ)
ከሰማንያ አምስት ሳምንታት በላይ ተፈጥሮኣዊ የኾነውንና ዛሬ ዛሬ በወንዶቻችን ውስጥ እየተመናመነ የመጣውን ወንዳወነድነት እንዲያንሠራራ በአባወራ የፌስቡክ ገጼ ላይ አኹን ደግሞ www.abawera.com ድረ ገጼ ላይ ከከተተየበው ተቀንጭቦ በኹለት ቅጽም ተዘጋጅቶ የታተመ ነው።
የመጽሐፉ ርዕስ “የአባቷ ልጅ” መባሉ?አባቷ በምክር፣ በተግሳጽ በቅጣትም ጭምር በስነስርዓትና ስነምግባር አስጊጦ ያሳደጋት ናትና..?አንድም ለአባቷ ከፍተኛ ክብርና ፍቅር ያላት ከዚህም የተነሳ ለወንዶች(በተለይም ለባሏ) ጤናማ አመለካከት ያላት ናትና?የወደፊቱን፦ ስሜቱን የገዛ መምራትና ማስተዳደር የሚችል የሰከነ መንፈስ የአመክኖያዊም አእምሮ ባለቤት የኾነ ትውልድ የምታፈራ ናትና?መጽሐፉ ውስጥም የመወያያ ርዕስ ናትና ?እነዚህንና የመሳሰሉትን መልካም ጠባዮች ባለቤት ዋጋዋም ውድ ነውና በእርሷ ተሰየመ።
የመጽሐፉ ይዘትመጽሐፉ በሦስት ዐበይት ጉዳዮች(የአባቷ ልጅ፣ ምስኪንነትና ጉዳቱ አባወራነትና ጥቅሙ) ላይ እያጠነጠነ ወንዶችን ወደ ተፈጠሩበት ልዕልና ይመለሱ ዘንድ በአጫጭር ወጎች ይዞን ይጓዛል። ይኽም መጽሐፉን ወንዶች ራሳቸውን እንዲፈትሹበት፣ እንዲያበቁበትም የተጻፈ ሲያደርገው ሴቶች ለወንዶቻቸው የሚሰጡት ምርጥ ስጦታም ይኾናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
“አንተ ወንድሜ ትዳርክን ትመራለህ? ሚስትህንና ልጆችህንስ? ወይስ የዓለም የእኩልነት አባዜ ጠልፎህ ልትመራው በሚገባህ ትዳርህ ቤትህ ባይተዋር ኾነሃል?
ያገባሃት ወይም ልታገባት ያሰብካትስ አባቷ የወንድ ልክ የኾነላት ትኅትናንም የተላበሰች ወይስ …..?
አንተስ የምትፈልገውን፣ የምታውቀውን የምትናገርና የምታደርግ ለእርሱም ኃላፊነት የምትወስድ ነህ? ወይሰ ሰዎች እንዳይከፋቸው ስትል ከእውነት ርቀህ የይሉኝታ ኑሮ የምትገፋ ነህ?”
እነዚህንና የመሳሰሉት በመጽሐፉ ውስጥ ይዳሰሳሉአስተያየታችሁን admi@abawera.com ላይ እጠብቃለሁ።

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *