የአባወራው ልዕልና ምንጩ ከየት ነው? ማደሪያውስ የት ነው?

ወንድሜ አባወራነትን ከብዙ ሴቶች ጋር በመውጣት የምትለማመደው አይደለም። አልያም ደግሞ ይኼ ሴት አውል ጠባይህ ከብዙዎቹ ጋር ስላወዳጀህ አንዷን ይዞ በአባወራነቱ መኖር የሚቻልህ አይምሰልህ። ሴት አውልነት ራስወዳድነት፣ ራስን ለታላቅ ዐላማ አለማጨት እና ስለነገንም ትውልድ አለማሰብ ነው።

አንተ በፍጹም ልዕልና ያለ አባወራ ለመኾን፣ አንተ በፍጹም ትሕትና የምትታዘዝህን ሚስትህን ለመውደድ፣ አንተ የሚስትህን ስጋዊ ፈቃድ በወደር የለሽ እርካታ ለመመለስ፣ አንተ ሚስትህን ደስ የማሰኘት ተልዕኮ ያለህ(ከእርሷ ጋር ባለህ ጾታዊ ግንኙነት) እርሱንም መፈጸም የሚያስደስትህ፣ ከዚህ ሌላም ደስታን ከእርሷ የማትሸምት ኾነህ ለመገኘት ከትዳር በፊት ከሴት ጋር መተኛት(መዋሰብ) አይጠበቅብህም።

አስቀድሜ እንደነገርኩህ አንተ ስኬታማ አባወራ ለመኾን ቅድመ-ጋብቻ ጋብቻ አልያም የወሲብ ልምምድ አያስፈልግህም። ቀድሞውኑ ከሴቶች ጋር የዚህ አይነቱ ግንኙነት ከሌለህ ታዲያ ትዳርህን እንዴት አድርገህ ማስተዳደር፣ መምራት ሚስትህንስ ማሳረፍ ይቻልሃል? ቁምነገሩ አባወራነት ከተለያዩ ሴቶች ጋር በሚነኖርህ የፍቅር ግንኙነት የምታዳብረው ሳይኾን ከእውነተኛ እውቀት እና እምነት የሚገኝ ስለኾነ ነው።

የአባወራነትህ ምንጭ

ለአባወራነትህ ምንጩ ፈጣሪክ ነው።ግልጽ ባለ ቋንቋ የሚስትህ፣ የቤትህ ራስ፣ እንደኾንክ የተጻፈውን እኔ እንዴት አድርጌ ከዚህ በበለጠ አቅልዬ ልነግርህ እችላለሁ? ምንስ ዓይነት ጥበብ ይኼን ኃይለ-ቃል ለድርድር ያቀርባል? እኔ የምንጩ ነገር ያከራክረናል ብዬ አላስብም።

ይልቁንስ በአባወራነትህ እንድትሰለጥን በእርሱም ጸጋ ተጠቅመህ የሰውን ዘር (ትውልድ) እንድታንጽ ያስችልህ ዘንድ የተሰጡህ አካላዊ ቅርጽ እና አእምሮአዊ ጠባዕይ ይኼንን እንደሚያጠይቁ(እንደሚያስረዱ) አስተውል።

የአባወራው ልዕልና ማደሪያ

ከእውነተኛው የተፈጥሮ እውቀት ላይ ተነስቶ በልቦናው የሚሠራጨው በራስ መተማመን አባወራውን በልዕልና ይሠራዋል ያስቀምጠዋል። በተፈጥሮ ጸጋ ራስነት ቢሰጠውም እውቀቱ እና እምነቱ ከሌለው ግን አይኾንምና።
የአባወራው ልዕልና ማደሪያው እምነቱ ነው። ማመን ደግሞ ከእውቀት የተነሳ በልብ እንደኾነ ልዕልናውም ከልቡ ይገኛል። የልዕልና ከፍታም እንደ እምነትህ ጥንካሬ ይወሰናል።በልብህ ያለው እምነት ሲጠነክር አንተ በልዕልና ታይላለህ።
ልብ አድርግ! አባወራ ያደርገኛል ብለህ ፀጉርህን ብታሳድግ፣ ሰውነትህን ብታሳብጥ፣ ገንዘብም ብትሰበስብ፣ ኃብትንም ብታከማች፣ ልዩ ልዩ ዐለማዊ እውቀትንም ብትቀስም ከንቱ ደክመሃል። አባወራ የሚያደርግህ ልዕልና በተፈጥሮህ የተቸረህ ስጦታህ ሲኾን ይህንንም አምነህ በልብህ ብትቀበለው መኾን ይቻልሃል።

በዚህም ምክንያት ለእምነትህና ለልብህ(ስለምታምነው ነገር) ከፍተኛ ጥንቃቄ ልታደርግ ይገባል። በምንም ዐይነት መልኩ ላንተ ክብር ከሌላቸው፣ በንቀት ዐይን ከሚያዩህ፣ ጥረትህን ከሚያጣጥሉ፣ ውጤቱንም ከሚያንቋሽሹት ሰዎችም ኾነ አመለካከቶች ጋር ሕብረት አይኑርህ። ምንም ዓይነት ዝምድና ትውውቅ፣ ጓደኝነት፣ የፍቅር ግንኙነት ያጣመረህን ሰው እንዲንቅህ አትፍቀድለት አልያም ተለየው። ይህ ሰው የቅርብህ ሰው ነውና በተገናኘኸው ቁጥር የሚናገራቸው የንቀት ቃላት ጠንካራ እምነትህን የመናድ ማደሪያውን ልብህን የማቁሰል አቅም አላቸው።

ይቀርበኛል ይወደኛል ከምትለው ሰው ንቀትን፣ በተደጋጋሚ የምትሰማ ከኾነ በራስህ ማንነት(በልዕልናህ) ላይ ጥርጣሬ ይገባሃል። መጠራጠር ደግሞ ስትጀምር እምነትህ ይሳሳል። ድግግሞሹም በልቦናህ ግድግዳ ይሳላል ይቀበለዋልም ከዛማ “ምስኪኑን-አንተ”፣”ትሑቱን አንተ”፣ይሰጥሃል ትኾንማለህ። ስለዚህም እልሃለው በጭራሽ የፈጣሪህ ስጦታው የኾነ ልዕልናህን፣ የእርሱም ማደሪያ የኾነውን እምነትህን ብሎም ልብህን አታስደፍር።

ለሳምንት ብንኖር *****የልዕልና ድንበርክን አስከብር*****
በዚህ እውቀት እና እምነት መሠራት ስትጀምር ለውጥህን የማይወዱ ሰዎች ይቃረኑሃል። እነርሱ ኹል ጊዜ ድንበር የለሹን ምስኪን እንድትኾን ይሻሉና። አንተ ደግሞ የልዕልና ድንበርክን የማታስከብር ከኾነ እንኳን በሌላ ዐይነት ጸጋ ልታተርፍ ይቅርና(“እንበለ ሰማዕት” ልትኾን) ለዘመናት የያዝከውንም ታጣለህ። የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች ይሉሃል …….ይቆየን።

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *