የአባወራው ሚስት እማወራ ናትን? ፪(እማወራ)

ሳተናው!
በቀደመው ጦማር የአባወራውን ሚስት አይተናል ዛሬ ደግሞ እማወራዋን እንይ።

እማወራ ስል ሴት የቤተሰብ(የቤት) አሰተዳዳሪ ማለቴ ነው። እርሷ ቤቱን እንድታስተዳድር ግድ ካሉዋት ምክንያቶች ጥቂቶቹ ደግሞ፦

፩ኛ የባሏ አለመኖር
     ፩፥ ሀ ባሏ በአካልም በመንፈስም ካጠገቧ ሳይኖር ሲቀር ለምሳሌ በሞት፣ በፍቺ
     ፩፦ለ ባሏ በአካል ኖሮ በስነልቦናው ግን ካለ የማይቆጠር፤ ከሰጡት በልቶ ካጣ ተደፍቶ የሚያድር፣ ቤቱን፣ ሚስቱን ፣ ልጆቹን ማባበል ማቅበጥ እንጂ በቆራጥነት መምራት የማይችል ሲኾን ነው።

በእነዚኽና በመሳሰሉት ምክንያቶች የተነሳ ባሏ ቤቱን መምራት ሳይችል ቀርቶ እርሷ(ሚስቱ) የምትመራ እና አብዛኛዎቹም ውሳኔዎች በእርሷ በኩል የሚያልፉ ሲኾን እርሷ እማወራ ኾናለች እላለሁ።

አንዲት እማወራነት “ስልጣን” ላይ የወጣች ሴት በትሕትና የምትገዛለት፣ ምርኮም የምትኾንለት ወንድ(ባል) የላትም፤ ይልቁንም ለእርሷ በጉልበትም ይኹን  በ”ፍቅር” የተማረከላት ወንድ በስሯ ይኖራታል እንጂ።

እማወራ ባለችበት ቤት ለልጆቿ የአዛዥነት፣ የበላይነት ምሳሌ ትኾናለች። ከዚኽም የተነሳ ወንዶች ልጆቿ ከእርሷ ጋር ተስማምቶ ለመኖር ሲጥሩ ፈሪ፣ ስሜታዊ፣ ለእርሷ የገቡ,(ከእርሷ በኹሉ የሚስማሙ)፣ የተሸነፉ ነገር ግን ሽንፈታቸውን በ”ፍቅር” ቅብ የቀቡ ናቸው። ሌሎች ሴቶችን ሲቀርቡም እንዲሁ ነው፤ ከሚስት ይልቅ እህት ይወጣላቸዋል።

እነዚህ ወንዶች ከአፋቸው “የፍቅር ወለላ” የሚቆረጥ፣ ወንዳወንድነት በብዙ የሚጎላቸው፣ ውሳኔ ዳገታቸው፣ ቂምና ንዴት በኾዳቸው፣ ኾደ ባሻነት ገንዘባቸው፣ ሚስታቶቻቸው የኑሮ ዓላማቸው፣  ናቸው።

እነርሱ ቢያገቡም ትዳራቸውን መምራት አይችሉም፤ ይልቁንስ በእኩልነት፣ በስልጣኔ ስም ለሴቷ የትዳሩን ልጓም አስጨብጠው እነርሱ መጎተትን(መመራትን) የሚመረጡ ናቸው። የአባትንም ጣዕም አያውቁትምና ብዙውን ጊዜ “እናት ትበቃለች” ሲሉም ይደመጣሉ።

የእማወራዋ ቤት የብዙዎቹ ምስኪን(ንክር ምስኪን) ወንዶች፣ እና ሴታቆርቋዥ ወንዶች (Feminist men) መፍለቂያ ነው።

=========================================

ሴቶች ልጆቿ
===========
የእማወራዋ ሴቶቹ ልጆች ብዙውን ጊዜ ወንዳወንድ የኾነ አለባበስ(ሸሚዝና ሱሪ) የሚያዘወትሩ ጸጉራቸውን(ራሳቸውን) በሴት ወግ የማይንከባከቡ ናቸው። በትዳር ከተጣመሩት ወንድ መደገፍ የሚጠየፉ፣ ትምክህታቸው ባላቸው ሳይኾን ፍርድቤት የኾነባቸው ናቸው።

እነዚህ ሴቶች ከእናታቸው ዘንድ ብዙውን ጊዜ “ለወንድ እንዳትሸነፉ፣ የወንድ እጅ እንዳታዩ፣ በወንድ እንዳትማረኩ” ተብለው ስለሚያድጉ በትዳር ሕይወታቸው ደስተኛ አይደሉም (አይኾኑምም)። ለምን እንደኾነ ግልጽ ባልኾነላቸውም ምክንያት ባላቸውንና የልጆቸቸውን አባት እየጠሉት ይመጣሉ።

============================================================
የዚኽ ምክንያቱ ደግሞ ለሴት ልጅ በወሲብ የሚኾነው የደስታ ጥግ የሚገኘው ልቧ ለባሏ ሲሸነፍ፣ ከዚህም የተነሳ አእምሮዋ ሰውነቷን መምራቱን ሲተው፣ ባሏም መሪውን ተረክቦ ወደ ደስታ ማማ አስከትሏት ሲወጣ እና የሚሠራውንም ሲያውቅ ነው። አንዲት ሴት ከባሏ(ከወንድ) ስትተኛ ልቧ ካልተሸነፈ ከንቱ ደክማለች።
============================================================

እማወራዎች ራሳቸውን ከተፈጥሮኣዊው ጸጋቸውና በእርሱም ካለው ሚናቸው አንጻረ ከመግለጽ ይልቅ ከወንዶች ጋር በንጽጽርና በፉክክር መግለጽ ይቀናቸዋል።
በአንደበታቸውም፦ “ከወንድ አላንስም፣ እርዳታ ከወንድ አልፈልግም፣ ባል አያሰፈልገኝም፣ አባት ምን ይሠራል” ሲሉ ይደመጣሉ።

ሴታቆርቋዡ አመለካከት(Feminism) ሴቶቻችንን በውሸት “ነፃነት” እና “ደስታ” ጋርዶ እንዳያገቡ፣ ያገቡትም እንዲፈቱ፣ ልጆቻቸውን እንዲበትኑ እያደረገ ወደ ብቸኝነት፣ ቁጭት፣ ምሬት፣ ተስፋ መቁረጥና ሞት ያከንፋቸዋል። ከዚኽ ክፉ መንገድ ግን ያ ከባላቸው በላይ የተመኩበት ፍርድ ቤትም ኾነ የፖለቲካ መሪ አይታደጓቸውም፣ አፋቸውን እያጣፈጡ ይጠቀሙባቸዋል እንጂ።

👉 ብዙ ብዙ ማለት ቢቻልም እዚህ ላይ ይብቃን። አንድ ቀን ደግሞ ከአንድ መቶ ገጽ የማትበልጥ  “እማወራዊ ስርዓትና መዘዙ” የተሰኘች “ጥናታዊ” ጽሑፌን አካፍላችኋለሁ።

ለአኹኑ ግን ከዚኽ በታች ያለውን ከሰሜን አሜሪካ የቆጠራ(statistics?) ቢሮ የተወሰደ ሐቅ እንታዘብ።

😱😱😱 ራሳቸውን ከሚያጠፉ ወጣቶች 63 ከመቶዎቹ፣
😱😱😱 በአሥራዎቹ እድሜ ከሚያረግዙ ሴቶች 71 ከመቶዎቹ፣
😱😱😱 በማረሚያ ቤት(በእስር ቤት) ከሚገኙ ወጣቶች 85 ከመቶዎቹ፣
😱😱😱 ሕይወታቸውን በጎዳና ከሚገፉ አልያም ከቤት ወደ ጎዳና ከሚኮበልሉ 90 ከመቶዎቹ
😱😱😱 ትምሕርታቸውን ከሁለተኛ ደረጃ ከሚያቋርጡት 71 ከመቶዎቹ መገኛቸው ይኸው የእማወራዋ (አባወራ የለሽ) ቤት ነው።

…….ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *