የአባወራው ሚስት

እስከዛሬ ዳር ዳሩን ስንነካካው የነበረውን የአንተን (የእጩ አባወራ) እጮኛ(ሚስት) መረጣ ዛሬ እናየዋለን።

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ መሠረታዊ የተፈጥሮ እውነቶች(ባሕርያዊ) እናነሳለን። በምናነሳቸው እውነቶች የተጎዳንባቸው(በኑሮ)፣ የተሰበርንባቸው(በልብ) እንኖራለን። ነገር ግን የእኛ ቁስል እንዳይነካ ሲባል ሌሎች ሳይማሩባቸው ሊጎዱባቸው አይገባምና እነኾ ደረቅ እውነት አቀብላችዃለሁ።

ለአባወራነት የሚያበቁህን እውቀቶች፣ ብቃቶች ከታጠቅህ አኹን ኹነኛ ሚስት ፍለጋ ትወጣለህ። ያንተ የግል ምርጫዎች እንደተጠበቁ ኾነው ወደ አንተ ሕይወት(ዐለም)የምታመጣትን ሴት በእነዚህ ሁለት መ…ሠ…ረ…ታ…ዊ መሥፈርቶች ትመዝናለህ።

፩ኛ የአባቷ ልጅ የኾነች
የአባቷ ልጅ ፦ አባቷ ያቀበጣት ቀበጥ ማለት አይደለም።
ስለአባቷ ልጅ ለማንሳት አባቷ ይቀድማልና ማንነቱን እንይ እርሱ የግድ ወላጅ አባቷ ላይኾን ይችላል። ታላቅ ወንድም አጎት ወይም እንጀራ አባት ብቻ እርሷ ባደገችበት ቤት ውስጥ በአባወራነት ሚና የጤናማ ወንድ ተምሳሌት የኾነውን ነው። እኛ ጠቅለል አድርገን አባት እንለዋለን። እርሱ ያሳደጋትን የአባቷ ልጅ እንላታለን እንዲህም እንድንላት ያሰኟትጠባዮቿ፦

፩፥ሀ በሥርዓት ማደጓ
አባቷ በቀረጸላት ሥርዓት(መንገድ) ላይ ትዕዛዙን እየፈጸመች በትኅትና ያደገች ለዚህም እናቷ አርአያ የኾነቻት ናት።

አባቷ ይወዳታል፣ ይንከባከባታል፣ ያጀግናታል፣ ያሞካሻታል ይኹንና ስታጠፋ፣ ከስርዓቱ ስትወጣ፣ ከመንገዱም ስትስት ይመክራታል፣ ይቆጣታል፣ ይቀጣታል።
ይኼም ከፍቅሩ የተነሳ ከአጉል መንገድ እርሷን የሚታደግበት ነው። እርሷም ለዚህ እንደኾነ ታውቃለች ከእናቷም ተምራለችና።
የትምሕርት ጉብዝናዋ፣ የቤት ውስጥ ጠባይዋ(ሙያዋ)፣ መልኳ እንዳይቀጣት ሰበብ አይኾኑትም።
የአባቷ ልጅ ያልኾነችው ግን አባቷ የምትሄድበትን መንገድ አላስተማራትም አልያም በአባቷ ላይማመጽን ከእናቷ ተምራለች። አንተ ቤትህን ለምታስተዳድርበት ሥርዓትም ተቃራኒ፣ ለትዕዛዝህም እምቢታን ታሳይሃለች። ልጆችህንም በዚህ መልክ ባንተ ላይ አመጸኛ ታደርጋቸዋለች። ባንተ ላይ የሚያምጹት ልጆች ደግሞ ወደ ማሕበረሰቡ ሲቀላቀሉ ምን ጭምት ቢመስሉ ማሕበረሰቡ(ሀገር) ለሚተዳደርበት ሥርዓት አመጸኞች ይኾናሉ።

፩፥ለ ለራሷ ያላት ዋጋ ከፍተኛና ጤናማ ነው(self-esteem)

የአባቷ ልጅ እንደ ሴታቆርቋዥ(Feminism) ተጠቂዎች ያልኾነ ጤናማ የራስ መተማመን አላት። ፈጣሪ በሰጣትም ጸጋ ልክ በሕይወቷ መልካሙ ነገር በጤናማው መንገድ ከልቧ ትሻለች(ፍቅር፣ ወሲብ፣ቤተሰብ….)።

በሴትነቷ ደስተኛ ስትኾን ጣፋጭ ፍቅር፣ ምርጥ ወሲብ፣ ደስተኛ ቤተሰብ፣ የተደላደለ ኑሮ በጤናማው መንገድ ይገባኛል ብላ የምታምን፤ እርሱንም ለማገኘት የምትጥር በሌሎች ሴቶች ከመቅናት፣ ከወንዶችም ጋር ከመፎካከር የተለየች ነች።

ስለራሷ ጠቅላላ ማንነት ብዥታ ያለባት ያባቷ ልጅ ያልኾነችው ግን ወይ ራሷን ጠልታ ከመልካም አጋጣሚዎች ኹሉ ትርቃለች፤ አልያም አቅሟን፣ ተፈጥሮኣዊ ጸጋዋን ያላገናዘበ በራስ መተማመን ውስጥ ገብታ የቀረባትን ወንድ ኹሉ ስትንቅ ትኖራለች።

በኹለቱም አጋጣሚዎች ይኽች ሴት ወንዶችን ብትቀርብም ብታገባም እነርሱ የሚሰጧትን እፈልገዋለሁ የምትለውን(ፍቅር፣ ወሲብ፣ ቤተሰብ…) ስታገኝ ከማጣጣም ይልቅ ማጨናገፍ ይቀናታል።

፩፥ሐ ታዛዥነት
በሥርዓት ከማደጋ አንጻር የአባቷን ልጅ የሚስተካከላት የለም። መታዘዝና ጥቅሙ ዘርፈ ብዙ ሲኾን 1ኛውና ዋነኛው ጥቅም ግን ለራሷው ነው(በወሲብ ጊዜ)
2ኛው ለልጆቿ ነው፦ ለወላጆቻቸው ለመታዘዝ ሕያው ማሳያ ትኾናለችና

፩፥መ አመሰጋኝነት

የአባቷ ልጅ አባቷ በአቅሙ ሠርቶ ያመጣውን እናቷ አመስግና በደስታም ተቀብላ ስትሰጣቸው ታያለችና የስጦታህን ትልቅነትና ትንሽነት ሳታይ ታመሰግናለች። አባቷ ያፈሰሰው ወዝ የገበረው ደም(ደመወዝ) ነውና ታከብረዋለች።

የአባቷ ልጅ ያልኾነችው ግን ለእርሷም ኾነ ለቤተሰቦቻ ብታደርግ”ግዴታው ነው”፣ ስትገዛላት”ስላለው ነው” ትልሃለች። የሰጠሃትን ትታ ባልሰጠሃት ነገር ታማርራለች። ምን ብትገዛላት ከመርካቶ አይደለም ከዱባይ ስጦታን ብታመጣላት፣ ኧረ ዱባይንም ገዝተህ ብትሰጣት አታመሰግንህም በዚህም ልብህን ስታደማው ትኖራለች።

ብንኖር በሴታቆርቋዡ (Feminism)የተጠመደችው….. …. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *