የአባወራ ስልጣን ለቅጠኛ ቤተሰብ ማዕዘን ነው

የሰው ልጅ በምድር ላይ መኖር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ፈቅዶም ኾነ ሳይፈቅድ አውቆትም ኾነ ሳያውቅ በአንድ ተቋማዊ መዋቅር ሥር ይኖራል።(ሳይፈቅድ ላልኩት የፈጣሪ እኛን መፍጠር ነው)
ተቋም፦ በዓላማ ፣ ዓላማውንም ለማሳካት እንደ እውቀታቸውና ችሎታቸው የተለያየ ሚና ባላቸው ሰዎች በፈቃደኝነት የተቋቋመ የተመሠረተ ደግሞም በእነርሱም ምርጫ በአንዱ መሪነት፣ አዛዥነት፣ ጠባቂነት የሚተዳደር ሕጋዊ ሰውነት ያለው ቅጠኛ ደርግ ነው።(ደርግ ማለት ምን ማለት ነበር..?) ለምሳሌ ድርጅት፣ መንግስት፣ ትዳርን ውሰድ፤ ነገር ግን ግለሰብ ተቋም አይኾንም።
ትዳርም፦ መሥራቹ እግዚአብሄር አባወራውን እንዲያስተዳድር ኃላፊነት የጣለበት ሌሎቹ የቤተሰብ አባላት ለእርሱ ሥልጣን በፈቃድ የሚታዘዙበት፣ በእርሱም መሪነት የሚያተርፉበት እና የሚደምቁበት ቅጥ (ሥርዓት) ያለው ተቋም ነው። መበልጸግ ቅጠኛ በኾነ አገር ብቻ እንደሚያኮራ ለቅጠኛ ቤተሰብም እንዲህ ይባላል፦”አባት ሳለ አጊጥ ጀምበር ሳለ ሩጥ” እንደማለት ነው።
አስረጅ1 አንዲት ሀገር በሕዝቦቿ መልካም ፈቃድ ስትመሠረት (ወቅታዊውን የሀገራችንን ፖለቲካዊ እሳቤ ግምት ውስጥ ብንከት) ሕዝቦቿ በተወካዮቻቸው(በሕግ አውጪዎች) አማካኝነት የሚተዳደሩበትን ሕግ (ሕገመንግስት) አውጥተው፣ ዳኝነት ሲሹ ሕጉን ተርጉሞ ፍትህን የሚሰጣቸው(ፍርድ ቤት)፣ ሕጉንም የሚያስጠብቅላቸው ሕግ አስፈጻሚ (ፖሊስ) ፣ እነዚህንም ጠንቅቆ አውቆ እና ችሎ የሚያስተዳድራቸውን መሪ(ጠቅላይ ሚንስቴር) መርጠው ይኖራሉ። ይኽን በማድረጋቸው ምን ያገኛሉ ወይም ምን ያጣሉ?
የሚያጡት ነገር በነጻነት እንደፈለጉት መኖርን ያጣሉ። ለምሳሌ ብንዘረዝራቸውም፦
1 ጠጥቶ ማሽከርከር ቢፈልጉ
2 ሽንታቸው እንደመጣ መንገድ ላይ መሽናት ቢፈልጉ
3 ከሀገር ሀገር ያለምንም ፈቃድ መዘዋወር ቢፈልጉ
4 ግብር ሳይከፍሉ መኖር ቢፈልጉ
5 ያገኙትን የቆመ መኪና መንዳት ቢፈልጉ
6 ከተፈቀደው ፍጥነትበላይ ማሽከርከር ቢፈልጉ
7 የፈለጉትን ቀምተው እምቢ ያላቸውን ማጅራቱን ብለው መኖር ቢፈልጉ
8 እርቃናቸውን መንቀሳቀስ ቢፈልጉ
9 ሁሉም ሕዝቦች ለጉብኝት፣ለጥየቃ፣ ለልምድ ልውውጥ ሌላ ሀገር መሄድ ቢፈልጉ
10 ያናደዳቸውን ሰው ሁሉ መግደል ቢፈልጉ……..የመሳሰሉትን ያጣሉ።
በሕግ ጥላ መንግስትም በተባለ በአንድ ሀገራዊ(ሀገር እንደ ተቋም) አስተዳዳር ሥር መሆናቸው ከላይ ያየናቸውን እና ሌሎችም ሕይወታቸውን ዋጋ የሚያስከፍሉ ነጻነቶችን ሲያሳጣቸው ትርፋቸው ግን ሕይወትን የሚያቆዩ ነጻነቶችን ማግኘታቸው ነው። ለምሳሌ ብንዘረዝራቸውም፦
1 ሰዎች ጠጥተው አያሽከረክሩምና ከአደጋ ይጠበቃሉ(አብዛኞቹ ሹፌሮች ሕግ ያብራሉና)
2 ሰዉ በየመንገዱ አይጸዳዳምና ለበሽታ አይዳረጉም
3 የት እንደሚኖር የማይታወቅ ሰው አደጋ አይጥልም(አድራሻው ይታወቃል) አይሰጉም
4 መንገድ፣ መብራት፣ ውኃ፣ ትምህርት፣ ሕክምና የት እናገኛለን ብለው አይጨነቁም
5 መኪናቸውን አቁመው ሲሄዱ ማን ይወስድብናል ቢወሰድስ ማን ያስመልስልናል አይሉም
6 የመኪና አደጋ ተሳቀው ቤት አይቀሩም መኪኖቹ ፍጥነታቸው የተገደበ ነውና
7 አንዱ ቦርሳዬን፣አንዱ ስልኬን ይቀማኛል፣ከኋላዬ ማጅራቴን ይሉኛል ብለው አይሰቀቁም
8 የተስማሙበት ሕግ አለና ባሕላዊም ሆነ ኃይማኖታዊ እሴቶቻቸውን ያቆያሉ
9 መራሔ መንግስት፣ መራሔ ብሔር አላቸውና በሀገራት ሲጋበዙ መብታችን እኩል ነው ብለው…ሁሉም ሻንጣቸውን አይሸክፉም
10 በጊዜያዊ አለመግባባት በሚነሳ ግጭት አንዱ ይገድለኛል ብለው ኃሳባቸውን ከመግለጽ አይቆጠቡም ……..
እነዚህ ሕዝቦች ታዲያ በአንድ ሥልጣን(ሕግ) ስር ለሚያገኙት ጥበቃ ከዚህም የተነሳ ለሚያጣጥሙት ነጻነት ሲሉ የመጀመሪያውን ልቅነት ቢያጡ አበጁ እንጂ መች አጠፉ፣ አተረፉስ እንጂመች ከሠሩ? በዚህም ታዲያ ቅጠኛ ሀገር ስትኖራቸው እነርሱም ለተሻለ ነጻነት በሕግ ቀንበር ስር ለመኖር ተሰማምተው በደስታ ይኖራሉ።
ትዳር ባልነውም ተቋም ውስጥም ይህ ሊሠራ ግድ ነው። መሥራቹ እንዳስቀመጠው፥ ለቤተሰቡ ሁለንተናዊ ደስታ በአባወራው ሥር መኾኑ የማይታበል ቃሉ ነው። እንዴት?….. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *