የአካል ብቃት(physical fitness)

*****በራድነትህ ለተስማማህ ምናልባትም በሕግ ተወስነህ(አግብተህ) ለመኖር ለማታልመውና ጀንደርብነትም ምርጫህ(ጥሪህ) ለኾነው ሳይኾን ሚስት አግብተህ ቤተሰብ መሥርተህ አባወራ መኾን ለምትሻው ተጻፈ።

ወንድሜ ራስህን በአባወራ ሚና ማግኘት ትሻለህን? እንግዲያውስ በጠዋት ከመነሳት በተጨማሪ ንቁ፣ ቆፍጣናና ጠንካራ ተክለሰውነት ሊኖርህ ይገባል።

በፈጣሪ በሚታይና በሚዳሰስ ተፈጥሮ ከደረትህ ሰፋ፣ ከጡንቻህም ፈርጠም፣ ከወደ መቀመጫህም (ቂጥህ) ሳሳ ተደርገህ የተፈጠርከው በምክንያት እንጂ በአጋጣሚ አይደለም።
በተቃራኒው ግን ደረትህ ጡንቻ መኾኑ ቀርቶ ጡት፣ ትከሻህ መስፋቱና መቅናቱ(ቀና) ቀርቶ ጨምዳዳና ጎባጣ ቢኾን፣ ኾድህም ቢንዘረጠጥ፣ ከወደ መቀመጫህም እየሰፋህ ከሄድክ፣ ቆም ብለህ ልታስብ ይገባሃል ጤናማ አይደለምና።

የእኔ እና ያንተ አምላክ በአጋጣሚ የሠራው ነገር ያለ ይመስልሃልን? ኹሉን በምክንያት ለዓላማ ፈጠረው እንጂ። ስለዚህም ያንተ አጥንት በተፈጥሮ ሸክምን እርሱንም የሚያነሳም ጡንቻን መሸከም እንዲችል ተለቅ ከበድ ተደርጎ ተሰጥቶሃል።

ፈጣሪህንና ተፈጥሮህን ካደነቅህና ከወደድህ ይኽንን ስጦታህን እወቀው፣ ጠብቀው፣ አሳድገው ለተሰጠህም ዐላማ አውለው።

በአካል ብቃት እንቅስቃሴ የምናገኘው ንቃት፣ ጤንነት፣ጥንካሬ(ጉልበት)፣ በራስ መተማመንና ወሲባዊ መነቃቃት ፈጣሪ ለለገሰን የአባወራዊ ሚና ኹነኛ ትጥቅ ሲኾን ያለእነርሱም ወንድነት ለዘር ብቻ ይኾናል።

ወንድሜ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለመሥራት ልክ በጠዋት እንደመነሳቱ ያንተ ቆራጥ ውሳኔ ያስፈልጋል። ራስህን ለመቀየር በምታደርገው ትግል ዋነኛው ተገዳዳሪህ አንተው ራስህ ነህና።

ያም ኾነ ይኽ ግን አንተ በዚህ የሰውነት ቅርጽና ጾታ የተፈጠርክበትን ምክንያት አውቀህ የተጠራህበትን ዐላማ ታሳካ ዘንድ የተሰጠህን ጸጋ(አካላዊ ስጦታህ) ተረድተህ እርሱንም በመጠበቅና በማጎልበት ልትኖር ይገባሃል።

ቤትህን(ሚስትህን፣ ልጆችህን) ለመምራትና ብቁ ዜጋ አድርገህ ለማፍራት አንተ ራስህን በሥርዓት የመምራት ብቃት ሊኖርህ ይገባል። ለዚህ ደግሞ ዘወትር በቁርጥ ሰዓት በተወሰነ ቦታ እንደምትሠራው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የተሻለ መሣሪያ የለም። ምክንያቱ ደግሞ ለውጡንና በለውጡ የተገኘውን ስኬት አእምሮህ ይረዳልና፣ ልብህም ያምናልና ነው።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፦

፩ኛ ለንቃት
በጠዋት ከመነሳትህ ጋር የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ስትጀምር ሰውነትህ ንቁ ይኾናል። ሰውነትህን በፈቃድህ፣ በአመንከው መጠን፣ እንደአቅምህም ማዘዝ ይቻልሃል። የሥራ ተነሳሽነትህም ይጨምራህ። ከድብርትና ምንጭ አልባ ጭንቀቶች እንዲኹም በተቀመጥቅክበት ለሚያንቀላፋህም መፍትሄው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ነው።

፪ኛ ለጤንነት
ወንድሜ ቀደም ባሉት ዘመናት ይኖሩ የነበሩት አያቶቻችን የዕለት ተዕለት ተግባራቸው በአብዛኛው በጉልበት የሚሠራ ነበር (አደኑ፣ እርሻው፣ ከብት ጥበቃው…)። ዛሬ ግን እኔ እና አንተ ባለንበት ዘመን አብዛኛው ሥራ ጠዋት ከተቀመጥንበት ወንበር ሳንንቀሳቀስ ከቀኑ ጋር ያልቃል። ይኼም እነዚህ የድሮዎቹ አባቶች የማያቁትን ስኳር፣ ግፊት፣ ኮሌስትሮል፣ ውፍረት የተባሉ የጤና ጠንቆችን አስገኝቷል። የአካል ብቃትእንቅስቃሴን ስትሠራ ግን የእነዚህን ጠንቆች ምንጭ አደረቅህ ማለት ነው።

፫ኛ ለጥንካሬ(ጉልበት)
ወንድሜ ጥንካሬ ወይም ጉልበት ለምን እንደሚያስፈልግ መቼም አይጠፋህም። የምጨምርልህ ነገር ቢኖር አይደለም ጸብን ደስታንም ለማጣጣም ጥንካሬ(ጉልበት) እንደሚያስፈልግህ ብነግርህስ…

፬ኛ ለወሲባዊ መነቃቃት
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስትሠራ በተለይም ጡንቻዎችህን የሚያዳብሩ እና መላ ሰውነትህን የሚያጠነክሩት(ክብደት ማንሳት) በወሲባዊ መነቃቃትህ ላይ አዎንታዊ አንድምታ አላቸው።
ጥልቅ የኾነ አተነፋፈስን፣ በከፍተኛ ፍጥነት ደምህን ማመላለስ የሚችሉ ሰፋፊ ደምሥሮችንም ታተርፋህ።

ይኼን ውጤት ታገኝ ዘንድ ግን እንቅስቃሴህ ልማድ ኾኖ የምትሠራው እንጂ የአንድ ሰሞን ሆይ ሆይታ መኾን የለበትም።

ልብ አድርግ! ወሲባዊ መነቃቃት ስልህ ራስወዳድ ኾነህ ሴታውል፤ አልያም ሱሰኛ ኾነህ ሴሰኛ መኾንን ሳይኾን የምትወዳት ሚስትህን ተፈጥሮኣዊ ጥያቄ ጥግ የምታደርስበት ከፍቅር የመነጨ እንጂ። መቼም ባል ኾነህ ይኼን ግዴታህን እንደ አለመወጣት በሚስትህ የሚያስንቅ አንተንም የሚያስቆጭ ምን ነገር አለ?

እንደ አባወራ አእምሮኣዊና መንፈሳዊ ጥበብን ስታሳድግ ማሕደራቸውን(ማደሪያቸውን ሰውነት)
ጎን ለጎን ማዳበር አትዘንጋ። አልያ ጥበቡ ኖሮህ መተግበሪያው ይቸግርሃልና።

በል ተነስ እጅህን ቅባት እየተቀባህ ማለስለሱ እንዳያልብህም መጠንቀቁ ይቅርና ሰውነትህን በጡንቻ ገንባ ወንድነትህ ከሩቅ ይለይ ዘንድ…. ይቆየን።

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *