የወሲብ ነፃነት ወሲባዊ ፊልሞች..

ወሲብ ለሰው ልጅ በምድር ላይ ዘሩ እንዲበዛ ትውልዱም እንዲቀጥል በፍጹም ፍስሃም ሆኖ ጾታዊ ፍቅሩንም ያጠነክርበት ዘንድ ከፈጣሪ የተሰጠው ነው፡፡ በአግባቡና በትክክለኛው መንገድ ከተጠቀመበት እጅግ እጅግ የሚያተርፍበት ባለ ፈርጀ ብዙ ጥቅም ሲሆን አልያ ግን መጥፊያው ይሆናል፡፡

ጤናማ ሕብረተሰብ የተረጋጋ ማህበራዊ እሴቱን ይዞ የሚቀጥለው በወጣቱ ትውልድ ውስጥ እንዳለ የሚያምንበትን ጤናማ የወሲብ ፍላጎትና ኃይል ወደ ትዳር በማምጣት ነው፡፡ ልጆችም የዚህ ትዳር ፍሬ ናቸውና አስፈላጊውን እንክብካቤም ሆነ ጥበቃ ሲያገኙ ሴቶች(ሚስቶች) ደግሞ ይህን ሕብረተሰብ በመገንባቱ ሂደት ከወንዶች አቻዎቻቸው ጋር ያንን እምቅ ኃይል በመቀባበል በሙሉ እርካታና ደስታ ይሳተፋሉ፡፡

የአቶሚክ ልሂቃኑ ሲያገኙት ለሰው ልጅ የበዛ የከፍተኛ ኃይል አቅርቦት ጥያቄዎች ብዙ መልስ እንዳለው ተስፋ አድርገው ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ የሰው ልጅ ኑሮውን ከማቀላጠፍ አነፃር ተአምር ይሠራበታል የተባለው ግኝት ለጥፋት ዋለና ሂሮሺማና ናጋሳኪ ላይ የማይሽር የጥፋት ጠባሳ አሳረፈ፡፡ አሁንም ሀገራት አንተን በዚህ ነው የማጠፋህ አንቺን በዚህ ነው የማጠፋሽ የሚባባሉበት፣አንተና አንቺ ለተባባሉት ብቻ ሳይሆን ለዓለምም ጥፋት የሚደገስበት መሣሪያ ነው፡፡ የአቶሚክ ኃይል ጥፋቱ የትየሌሌ ነውና በከፍተኛ ቁጥጥር ተመርቶ አገልግሎት ላይ ይውላል፡፡ አገልግሎት ላይ ሲውል ደግሞ ሀገራቱን በስልጣኔ ጎዳና ወደፊት ያስወነጭፋል፡፡

ወንድሞቼ ለወሲብም እንደዚሁ ነው የፈጣሪን ፈቃድ፣በባህላችንና በሀይማኖታችን ክልክል የሆኑትን ተከትለን (እነዚህ እንደ አቶሚክ ኃይል ማምረቻው መቆጣጠሪያ ሲሆኑ)በፍጹም ፍስሃ ስንፈጸመው ለሁለቱም ጾታዎች ይህ ነው ተብሎ በቃላት የማይቀመጥ ጥቅም ይኖረዋል፡፡ ያለበለዚያ ግን እገሌንና እገሌን ሳይባል የሰውን ዘር ማጥፋት የሚቻለው ይሆናል፡፡

የወሲብ ትዕይንቶች(ፊልሞች) በተለይ በወንዶች ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖዎች እስቲ ባጭሩ እንያቸው
1 ድብርት:- ይህንን ትዕይንት በተደጋጋሚ የሚያዩ ወንዶች ሚስቶቻቸውን ሁልጊዜ ለቀረፃ ተዘጋጅታ ከሚየዩዋት ሴት አንፃር ያዩዋቸዋልና ለተራክቦው ሁነኛ መስህብ አይሆኑላቸውም ስለዚህም በፍቅራቸው አይደሰቱም ያዩትን ፈልገው ባለማግኘታቸውም ድብርት ውስጥ ይወድቃሉ፡፡በዚህም ጥሩ ባል አይሆኑም፡፡
2 እውነታን ያዛባብናል፡ ትዕይንቱ ለትርፍ ተብሎ የሚሠራ ነውና ከእውነታው የወጣ ግነት የበዛበት ገበያ እንዲያስገኝ ብቻ በአዘጋጆቹ ድርሰት እና ገጸባሕርያት የታጠረ ነው፡፡ የነጻ ትግል ለዚህ ጥሩ ማስረጃ ነው፡፡ ቀድሞ የተፃፈና የተደረሰ በተዋናዮቹ ሲፈፀም ግን እውነት እስኪመስል ድረስ ምን ያህል እንደሚገዛን መገንዘብ ይቻላል፡፡
3 የሴቶችን ክብር ይነካል፡ ክብርና ፍቅር የሚገባቸውን ሴቶቻችንን እንደ የወሲብ ፍላጎት መፈጸሚያ ዕቃእንጂ እነርሱም ስሜት ፍላጎት ያላቸው ክቡር ፍጥረት አድርጎ አይስልብንም፡፡
4 አሁንም አሁንም ለሚል የወሲብ ሱስ አእነና ጉጉት ይዳርገናል፡፡ ወንድ ልጅ የወሲብ ሱሰኛ ሲሆን ደግሞ ሚስቱን በወሲብ ማስደሰት አይችልም፡፡ ግልብና ጊዜያዊ ፍላጎቱን ያረካል እንጂ ሚስቱን መረዳት አይችልም፡፡ የቡና ሱስ ያለበትንና ቡናን ወዶ፣ አጣጥሞ፣ ተደንቆ እና አድንቆ በሚጠጣ መሐል እንዳለው ልዩነት ማለት ነው፡፡ ሱሰኛው ቡና መጠጣቱ አምሮቱ መብረዱን ብቻ ያያል አድናቂው ግን ቡናው ከየት እንደመጣ እንዴት እና በማን እንደተቆላ እንደተፈላ በምን አይነት ፈገግታ እንደቀረበም ያደንቃል ያመሰግናልም ፡፡የወሲብ ሱሰኛ ስንሆን አሁንም አሁንም እንበል እነጂ ሚስታችንን እርፍ አናደርግም የጋራ እርካታንም ግምት ውስጥ አንከትም፡፤

ሱሳችንን እንደ ብቃት በጉራ አጅበን ስንኖር ጉዳችንን የሚያቁት ሴቶች ግን ፍቺ ይጠይቃሉ ፡፡

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *