የወንዱ የመጋቢነት(nurturing) ሚና እና ያደረሰበት ተጽዕኖ

ቅድሚያ ስለ መጋቢነት
ምንም እንኳ ሰልጥነናል(ሰይጥነናል) የሚሉት ሴታቆርቋዦች(Feminist) ሴቶችን የጨቆነ ሥራ ነው ቢሉትም መጋቢነት በተፈጥሮ ለሴት የተሰጠ ጸጋ ነው።

ፈጣሪያችን ይኼን ጸጋ የሰጠው ከማንም ካልወሰደው ለራሱ ብቻ ካለው የባሕርይው ከኾነው መግቦቱ ከፍሎ(በመክፈሉም ጉድለት ሳይኖርበት) ነው። ዐለምንና በውስጧ ያሉትን ፍጥረታት እንደየወገኑ እና እንደ እየጠባዩ ከእነርሱ ምንም ሳይፈልግ የእርሱ ቸርነት ግን ያስፈልጋቸዋልና መግቦቱ አይጎልባቸውም።

አንዲትም ሴት ቤተሰቧን ብትመግብ፣ ባሏን እና ልጆቿን በሚያስፈልጋቸው ኹሉ ብትንከባከብ ከላይ ከጠቀስነውን መለኮታዊ ግብር የምትጋራ ከባሕርዩም በጸጋ የምትካፈል ነች። ሴታቆርቋዦቹ(Feminists) እንደሚሉት ግን “ግርድና” ወይም ባርነት አይደለም። እንደውም እርሷን ለፈጠረበት ዐላማና በፈጠረበት ክብር መገኘቷን አምና በደስታ ብትቀበለውና ብትፈጽመውም ዛሬ ዛሬ “ሸክም፣ ባርነት፣ ግርድና” ብላ ባላማረረችው ባልተማረረችበትም ነበር።

ለመጋቢነት የሚኾኑ ግብዓቶች(logistics)
ፈጣሪ ሴትን ልጅ ከወንድ ጋር ለመሠረተላት ትዳር(ቤተሰብ) ለመጋቢነት ሲሾማት ተልዕኮዋን ትወጣበት ዘንድ የሚያስችሉ ግብዓቶችን(logistics) አሟልቶ ነው። ግብዓቶቹም በሦስቱም የሰው ልጅ አቋማት ተሟልተው የቀረቡ ናቸው። ለመግቦት ይኾናት ዘንድ፦
፩ኛ አእምሮኣዊ እውቀት ለግሶ
ሴት ልጅ ብልኃተኛ መኾኗን ቤተሰቡን በመላ(በጥበብ) የመያዟን ነገር ልብ ይሏል።
፪ኛ ጥበብ መንፈሳዊ አድሎ
የባሏን ልብ የምትገዛበት ትኅትና፣ ቤተሰቡን የምታሳርፍበት ፍቅር፣ ኹሉን የምትሰማበት ትዕግስት፣….. ….
፫ኛ አካላዊ ብልቶች አሟልቶ
ዘር የምትቀበልበትና ጽንሱን ዘጠኝ ወር የምትመግብበት ማኅፀን ሰጥቶ። ከወለደችም በኋላ የምታጠባበትን ጡት ከተገቢው ቦታ(ከጀረባዋ ያልኾነው፣ ከክንዷም ያልተሰቀለው፣ ከታፋዋም ያላደረገው በምክንያት ኾኖ) አደረገ። ለጡት ምርት፣ ሰውነቷም ምግብ እንዲኾነው የሚጠራቀም ስብ(ዛሬ ሴቶቻችን “ያስጠላል” እያሉ የሚያጠፉት እርግዝናና ወሊድ ላይ የሚቸገሩበት ከወለዱም በኋላ ከጡታቸው ግት ወተት የሚያጡበት ምክንያት)አዘጋጅቶ…. ነው።

ይኽ በእንዲህ እንዳለ ታዲያ ሴታቆርቋዡ (Feminism) ሴቶቹን ከዚኽ ኹሉ ጸጋ አርቆ፣ ከክብርም ጎትቶ፣ የተፈጠሩለትንም ዓላማ አስትቶ ዐዲስ የማያሳርፍ “ትምሕርት፣ሥራ(career) ” የሚባል ዐላማ ሰጥቶ ያባክናቸዋል። በዚኽም ሴቷ ባጎደለችው ፈንታ ወንዱ ገብቶ እንዲሠራ ይገደዳል። ጥያቄው ግን ከላይ ከጠቀስናቸው የትኞቹ ግብዓቶች(logistics) አሉት?

ሰው ሥራን እንዲቀርፅ ሥራም ሰውን ስለመቅረፁ
አስረጅ፦ አንድ በጉልበት ሥራ ላይ የተሠማራ ሰው “ለዕለት ጉርሴ”፣ “ለዓመት ልብሴ” ብሎ በሚሠራው ሥራ ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብሎ ከሚሠራው ሰው ሰውነቱ በእጅጉ ይለያል። ይኽም የጉልበት ሠራተኛው ፈርጠም ጠንከር ያለ እጅ ሲኖረው የቢሮ ሠራተኛው ግን ወይ የሰለለ አልያም ቅርጽ አልባ ሰውነት ይኖረዋል።

የሚሠሩት ሥራ የሚታይ አካላቸው ላይ ተጽፅዕኖ ማሳደሩ በሥራ የሚገለጡ እንጂ በዐይን የማይታዩ በኾኑት አእምሮኣቸውና መንፈሳቸው ላይ ተመሳሳይ አሻራ እንደሚያሳርፍ ማሳያ ነው።
በአንጻሩ ደግሞ ሰው የተሰጠውን አእምሮ ተጠቅሞ የተሰጠውን ሥራ በጥበብና በቅጡ ማከናወኑ፣ ማሻሻሉም በዚህም ፈቃዱን መፈጸሙ ሰው ሥራን መቅረጹን ያስረዳል።

ወደቀደመው ነገራችን ስንመለስ ታዲያ ሲፈጠር ለአቅርቦት(provider)፣ ለደኅንነት(security)፣ ትዳርን እንደተቋም ወጥና ቅጠኛ ቅርጽ ለማስያዝ(discipline) የተፈጠረው ወንድ ወደ መግቦቱ ሥራ ሲገባ የአካሉ ቢቀር ይኼን ማወቅ በመንፈሱም መታጠቅ ይኖርበታል።

መጋቢነት ተመጋቢውን እንደ ዐመሉ ማስታመም፣ ታግሶም ማቅረብ፣ አቅርቦም ማብላት፣ የተመጋቢውን የልብ ትርታ፣ የስሜት ኹነትንና መለዋወጥ መረዳትን ይሻል። ምክንያቱም ይኼን ስንረዳ ብቻ ፍላጎታቸውን እናውቃለንና ባወቅነውም እንመግባቸዋለንና።

ነገር ግን መጋቢ የተመጋቢዎቹን ስሜት ለመረዳት ቆዳው ስስ ሊኾን የተገባ መኾኑ ነው። ስሜትን ለመረዳት ደግሞ ተመሳሳይ የስሜት ንዝረት(vibration) ውስጥ መገኘት ግድ ይላል። ስሜትን በአንደበት ከመግለጽ ይልቅ በንዝረት(vibration) በደመነፍሳዊ መናበብ የበለጠ ይገለጻል፣ ቀጥተኛም፣ ልከኛም ነውና።

አስረጅ ፩ ለዚህ ነው ሴቶች በተደጋጋሚ ሳይነግሩት “የሚረዳኝ(የውስጤን የሚያቅልኝ) ወንድ” ፣ወንዶች ደግሞ “የምላትን የምትሰማ(የምትታዘዘኝ) ባገኝ ሲሉ የሚሰሙት።

አስረጅ ፪ አስተውላችኹ ከኾነ እንኳን በልጅነታችን አድገን አግብተን እንኳ ወደ ቤተሰብ ጋር ስንሄድ እናቶቻችን ከአባቶቻችን በተሻለ ፊታችንን አይተው፣ ግንባራችንን ታዝበው፣ የድምጻችንን ቅላጼ አጣርተው ስለኛ ውሎ፣ ኑሮ እንደተነገረው ሰው ነው የሚረዱት። ከዚህ የተነሳ ነው ከወንዶች ይልቅ ስሜቶችን ተከትለው ነገሮችን የሚረዱበት ስድስተኛ የስሜት ሕዋስ አላቸው የሚባለው።https://www.newtimes.co.rw/section/read/95649
ብንኖር ይኼ ኹሉ ጸጋ የሌለው ወንድ ወደ መጋቢነት ሚና ሲመጣ ምን ይኾናል? … ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *