የወንድነት ስደት

ለወንድነት ስደት አስተዋጽዖ ካደረጉት በርካታ ምክንያቶች መካከል የአንበሳውን ድርሻ የሚይዙት እ.ኤ.አ. በ1950ዎቹ እና 1960ዎቹ መካከል የተነሱት ሁለት ዐበይት አብዮቶች ናቸው፡፡እነሱም የሴቶች መብት ንቅናቄ እና የወሲብ ነጻነት ናቸው፡፡

የሴቶች መብት ንቅናቄ

ከዚህ በፊት እንደጠቀስነው ትዳር በፈጣሪ ታቅዶ ተወጥኖ እና ተመስርቶ ለሰው ልጅ የተሰጠ ነው ብለናል፡፡ በዚህም ውስጥ አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት ሲፈጥራቸው በሰጣቸው ሚና ክልል ውስጥ ሆነው እንዲተጋገዙ እንዲረዳዱ ዘራቸውን እንዲተኩ በዚህም ደስታቸው ምሉዕ እንዲሆን ነው፡፡ በዚህ ሚናው ተለያይቶ በተሰለፍንበት ትዳር ሚናን የሚያስተካክል ሚናን የሚያቻችል የመብት ጥያቄ ቢነሳ ውጤቱ ሊያምር ይችላልን፡፡

ምሳሌ ፡-(ስለ እግርካስ ጨዋታ የማታወውቁ ካላችሁ ከሚያቁት ጋር አንብቡት)

አንድ የእግርካስ ቡድንን እንደ ምሳሌ ብንመለከት ቡድኑ ውጤታማ መሆንን እንደግብ አስቀምጦ በአስራ አንድ ተጫዋቾች ወደ ሜዳ ይገባል፡፡ የቡድኑ አሰልጣኝ (መስራች) እንደልጆቹ ጥያቄ ሳይሆን የተጫዋቾቹን ችሎታ በሚገባ በማወቅ አሰላለፍ (ሚና) ይነድፍላቸዋል፤፡ማ ምን ጋር ቢሰለፍ ምን ሚና ቢጫውት ቡድኑ ውጤታማ እንደሚሆን ያውቃልና፡፡ እነሱም የተሰጣቸውን የቡድናቸውን አሰላለፍ (ሚና) ከዋናው ጨዋታቸው ውጭ ተለማምደውት ሚናውንም ተዋህደውት ሚናውም ተዋህዳቸው እርስበእርሳቸውም ተዋህደው ወደ ሜዳ ይገባሉ ውጤታማም ይሆናሉ፡፡

ይህ ማለት ግን ቡድናቸው ሲጠቃ አጥቂዎች ተቃራኒ ሜዳ ላይ ቁጭ ብለው በቆሎ እሸት ይበላሉ ማለት አይደለም፡፡ አንዳንዴም እኮ ከውጤት ፍለጋ የተነሳ አንድ ቡድን ሲያጠቃ በረኞችም ወደ ፊት ሄደው ትርፍ ሰው በመሆን ጫና ሲፈጥሩ እናስተውላለን፡፡ ይህንንም ለማድረግ ከሜዳ ውጪ ያለውን አሰልጣኛቸውን ማስፈቀድ አይጠበቅባቸውም፡፡

የእነ ፉክክር ቡድን

ነገር ግን ተጫዋቾቹ ቦታ ካልተቀያየርን ቀሪውን ግማሽ ጨዋታ አጥቂዎች ተከላካይ ይሁኑ ተከላካዮች ደግሞ አጥቂ በረኛም የፊት አጥቂ ይሁን ምክንያቱም ጨዋታው ሁሉን ያስተካከለና ሸከሙንም ሚዛናዊ ያደረገ እንዲሆን ቢሉ፤ ደግሞስ ሜዳ ላይ ሁላችንም እኩል ለቡድናችን መድከማችን እንዴት ይታወቃል የሚል የመብት ጥያቄ ቢያመጡ ምን ሊሆን እንደሚችል አስቡት፡፡ እንደዚህ አይነት ጥያቄ የሚጠይቁ ተጫዋቾች ከአሰልጣኙ እንበልጣለን የሚሉ፤ እሱ ሚናን ከያዙት ተፈጥሮአዊ ተክለሰውነት ከቀሰሙት የጨዋታ ዕውቀት አንፃር እያየ እንደ ቡድን ውጤታማ የሚሆኑበትን ሲያድላቸው እነርሱ እርስ በርሳቸው የሚፎካከሩ ናቸው፡፡

እንዲህም ይላሉ
ተከላካይ፡- አንድቀን ጎል ሳላስገባ ጫማዬን ልሰቅል ነው ሁሌ ተከላካይስ ለምን እሆናለሁ፡፡ እዳውም ከእኛ ቡድን ወጥቼ ሌላ ቡድን አጥቂ እሆናለሁ፡፡

በረኛ፡-እስከመቼ ጎል ጋር ተገትሬ እኖራለሁ በሚቀጥለው አመት አማካይ ተጫዋች መሆን አለብኝ፡፡

አጥቂ፡- ለምንድነው አሰልጣኛችን ጎል የማግባትን(የመጨረስን) ሸክም ለኔ ብቻ ሰጥቶ የሚያደክመኝ ለምን ሌሎቹንም ምን ያህል ጎል ማግባት እንደሚያደክም ቦታ እየለዋወጠ አያሳይልኝም በረኛው ሳይሮጥ ቆሞ ውሎ እኔ ባስገባሁት እሱ ይጨፍራል፡፡

እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው ተጫዋቾች ያሉት ቢፈጸምላቸው ለጊዜው ፍላጎታቸው መሳካቱ ደስ ቢያሰኛቸውም ለዘለቃው ግን ቡድናቸው እንደ ቡድን አይሳካለትም፡፡ ተከላካዮቹ አጥቂ ቦታ መጥተው የተቃራኒ ቡድን ተጫዋቾችን ማለፍ ሲሳናቸው አጥቂዎች ካስ ማስጣል ሲቸገሩ እንታዘባለን፡፡ ምክንያቱም አጥቂዎቹ ምንም ያጥቂ ባሕሪ እና ወኔ የሌላቸው ተከላካዮቹም እዲሁ ናቸውና፡፡ የሚገረማችሁ እነዚህን ተጫዋቾች የተቃራኒ በድን ሳይንቃቸው በፊት ቀድመው እርስበርስ ይናናቃሉ፡፡ ያንዱንም ጥረት አንዱ አያደንቅም፡፡ ውጤቱ ሲበላሽም እርስ በእርስ ይካሰሳሉ ጥፋቱ ያንተነው ያንተነው ይባባላሉ፡፡ ሲጀመር አሰልጣኛቸው ያላቸውን ለጋራ ስኬት እርሱ እንደሰጣቸው ሚናቸውን ሳያበላልጡ ጠብቀው ቢጫወቱ ኖሮ ይህ ባልሆነ ሲቀጥል ከፊተኛው የባሰው ደግሞ ስህተቱ የእኔ ነው ብለው ራሳቸውን እንደመውቀስ እርስ በእርሳቸው መካሰሳቸው፤ ችግሩን ከድጡ ወደ ማጡ ወስዶ በድኑን ያፈርሰዋል፡፡

የአሰልጣኛቸው ዓላማ የገባቸው (የስኬት ቡድን)

ከልጅነት ጀምሮ መሆን/መጫወት የሚፈልጉት ሚና ቢኖርም እነርሱን የሚመርጠው አሰልጣኝ ግን አንተ ተክለሰውነትህም ሆነ ካስ አገፋፍህ ለዚህ ቦታ አንተ ደግሞ ለዚህ ቦታ የሰጣችሁ ናችሁ ቢላቸው እሺ ብለው ይሰለፋሉ፡፡ ይህንንም ሚና በዕውቀትም ሆነ በልምምድም በማሳደግ ቡድኑን ውጤታማ በማድረግ ራሳቸውንም ያስጠራሉ፣ የመለመላቸውንም አሰልጣኝ ያኮራሉ፡፡ ምንም እንካ ለአንድ ቦታ/ሚና ቢመለመሉም ቡድናቸው ሲጠቃ/ሲያጠቃ ግን ተጨማሪ ተከላካይ/አጥቂ ሆነው ያግዛሉ፡፡

ታዲያ በትዳራችንም የመብቱ ጥያቄ ያመጣው ተመሳሳይ የሚና መደበላለቅ ነው፡፡ ወንድ በትዳር ውስጥ በወንዳወንድ ባሕሪው ሴትም በሴታሴት ባሕሪዋ ሊረዳዱ ሲገባ ይህ የሚና መደበላለቅ ግን ወንዳወንድነትን ከወንዱ ሴታሴትነትንም ከሴቲቱ አራቀ፡፡ ይህም ለጊዜው ፍቅርና መተጋገዝ ይባላል እንጂ በጊዜ ሂደት ከወንዱ የበለጠ ሴቶችን ደስታቸውን እያሳጣ ባላቸውንም እያስናቀ ወደ ንዝንዝ ሲቀጥልም ወደ ፍቺ እየመራቸው ነው፡፡

በጋብቻ ኢዮቤልዩን ማክበር ብርቅና ታሪክ እየሆነ በትዳር ጉዞ አሥር አመት መቆየት ረዥም ሆኖ ከመቸውም የሰዉ ልጅ ከኖረባቸው ዘመናት ለጥንዶች ፈታኝ እየሆነ ነው፡፡በተጋቢዎች መካከል የተፈጠረው የተፈጥሮ ሚናን አለማወቅ የተረዳዳንና የተግባባን መስሎን ልንረዳዳና ልንተጋገዝበት የሚገባንን አስተወን፡፡ እኛው የፈጠርነው የሚና መደበላለቅ እርሱንም ትክክል ነው ብለን መቀበላችን ችግራችንንም እንካ እንዳንረዳው አደረገን፡፡

ወንዶች ስሜታዊ መሆን፣መልፈስፈስ(ስጋዊም ሆነ ስነልቦናዊ)፣ለውሳኔ መቸገር፣በውሳኔ አለመጽናት፣ሲታይባቸው እንዲሁም ሌሎች ወደፊት የወንድ ብለን የምናስቀምጣቸውን ባሕሪዎች ሲተው በብዛት ሴቶች የሚታወቁባቸውን የተፈጥሮ ባሕሪያት እየተላበሱ ይገኛሉ፡፡ በሌላው ጎን ምንም ሴቶች ወሳኞች እየሆኑ የወንድን ባሕሪያት ቢላበሱም የወንዶቻቸው ስሜተ ስስነትና ወንዳወንድ አለመሆን የእነርሱን የውስጥ ሴትንት አያግዝም/አይገዛምምና በመካከላቸው ያለውን ግንኙነት ያሻክረዋል፡፡

ይቆየን……

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *