የወንዶች በራድነት፣ ሚናቸውን መሸሽና መዘዙ

በራድነት

የወንዶች ወንዳወንድነት መጥፋት፣ በተፈጥሮ ካገኙት አካላዊ መንፈሳዊ እና አእምሮኣዊ አቅም(ንቃት) መቀዛቀዝን ወይም ፍዝነትን ይገልጻል። ይህ ማለት ግን በራድ ወንዶች ኃይለኝነት የለባቸውም አይደለም እጩ ምስኪን ናቸውና እንደውም የታመቀና ድብቅ ኃይለኝነት አለባቸው(passive aggression)።

ይኽ በራድነት ደግሞ በተራው
፩ኛ በአደባባይ(በሥራ፣ በትምሕርት፣ በተለያዩ ማሕበራዊ ሕብረተሰባዊ እና ሀገራዊ አመራርነት ላይ)፣
፪ኛ በእልፍኝ(በቤት አመራር፣ በሚስትና በልጆች አስተዳደር ወይም ሥርዓት) እና
፫ኛ በመኝታ ቤት(ከሚስቶቻቸው ጋር ባላቸው ወሲባዊ ግለትና ተራክቦ) ጎልቶ ይታያል።

ከሃምሳ እና ስድሳ ዐመት በፊት በምዕራቡ ዐለም ተቀስቅሶ ከዚያም ወዲህ ተጠናክሮ የመጣው “የሴቶች እኩልነት”ን ዐላማ አንግቦ የተነሳው የሴታቆርቋዡ እሳቤ(Feminism) ለወንዶች በራድነት ከፍተኛውን ሚና ተጫውቷል።

በትንሹ በጎጇችን በቤተሰብ እንዲሁም በሰፊው በማሕበረሰብ፣ በሕብረተሰብ እና በሀገር አስተዳደር ደረጃ የወንዶች መሪነት ተቀባይነትን እያጣ ተቃውሞም እየገጠመው ነው።

በሴቶቹ ብቻ ያልተወሰነ በራሳቸው በወንዶቹም እየተራገበ የመጣው የወንዶች መሪነት ተቃውሞ ጥያቄን ሲያስከትል፤ የሚቀጥለው አጭር ሐተታ ደግሞ ለምን እና ማን የወንዶቹን ሚና ይገፋል ሲል….

፩ኛ ሴቶቹ ቢቃወሙት እሺ ወንዶቹ ግን ለምን ብትሉ ወንዶቹስ(በከፊል) ከበራድነታቸው የተነሳ ነው እላችኋለሁ።

በንቃትና በቀጥተኛ ተሳትፎ (active participant)ሚናቸውን ከመወጣት ይልቅ በበራድነታቸው ያመጡትን/የመጣባቸውን ስንፍና እና የብቃት ማነስ ለመደበቅ ሲሹ የቀደመውን የወንዶች የመሪነት ሥርዓት ይቃወማሉ፤ ወደኃላፊነት ወደ ተጠያቂነት ያመጣቸዋላ።

በራዶቹ ወንዶች
👉በአደባባይ ሥራቸው ከተጠያቂነት ለመሸሽ ሲሹ (በአስተዳዳር፣ በፍትህ፣ በአመራር) ጉንጭ አልፋ ምክክርና ስብሰባ በማድረግ ለውሳኔ መዘግየት ይታይባቸዋል። ቢወስኑም እኔ ብለው ኃላፊነቱን ከመውሰድ ይልቅ እኛ ብለው መደበቅን ይሻሉ ዋጋ ከፍሎ መወሰን ለእነርሱ ሩቅ ነው።

👉በእልፍኝ፦በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በ”sitcom” ድራማዎች ላይ እንደ “ቤቶች” ባሉ የምናስተውለው አባት የቤቱ ተጫዋች ፣አጫዋች፣ ሞኛሞኝ፣ ምስኪን ተራችና መተረቻ ተደርጎ እናት ደግሞ ብልህ አስተዋይ የሞኛሞኙን ባሏንም ሚና የደረበች ተደረጋየሚቀርበውን በገሃዱ ዐለም እያየነው ነው።

በቁጥር ትንሽ የማይባሉ ወዳጆቼ ከኃላፊነት ራሳቸውን አሽሽተው ሚስታቸው ቤታቸውን እንደምታስተዳድር ልጆቹንም የምትቀጣና የምትፈራዋም እርሷ እንደኾነች ሲያወሩ ሚናቸውን አሳልፈው መስጠታቸውን ለአፍታ እንኳ አይጠረጥሩም።

👉በመኝታቸው፦ በራድነታቸው ይበልጥ በተራክቧቸው ይገለጣል። ተፈላጊውን ግለት አጥተው የሰውነታቸውም ውጥረት ረግቦ የሚስታቸውን ተፈጥሮኣዊ ጥያቄ መመለስ አለመቻላቸው ነው።

በራድ ወንዶች የአደባባይ በራድነታቸውን/ስንፍናቸውን(incompetence)፣ የእልፍኝ ሚና መሳታቸውንና የመኝታቤት (ወሲባዊ ግለት-አልቦነታቸውን) አንድም ለመደበቅ አንድም ከሴቶቹ ክስ ለመሸሽ ሲሉ የሴቶችን መሪነት(በአደባባዩም ኾነ በእልፍኙ)፣ ወሲባዊ ተራክቦም በሴቶች ይኹንታ መኾኑ አግባብ ነው ሲሉ ይሞግታሉ።

፪ኛ ሴታቆርቋዡን እሳቤ የሚያራምዱትና የሚደግፉት(Feminist) ደግሞ ተተኪ ምልምል የሚያፈሩት ይኽንን ነባር ሥርዓት አምባገነናዊ፣ ሴቷን ስልጣን የማያካፍል፣ ፊውዳላዊ፣ ያረጀ ያፈጀ ነው ብለው ሲኮንኑ ነውና ይኽም ይኾናል።

ሴታቆርቋዡ(Feminism) እንዲህ ይላል “እናንተን ስልጣን ከከለከላችሁ ወንድ እኩል እንደውም ከዚያ በላይ መኾን ትችላላችሁ። ወንዶቹ ይኽንንም ስለሚያውቁ ነው እነርሱ “በጻፉት” የኃይማኖት መጻሕፍትም ኾነ የቃል መመሪያ እናንተን መሪ እንዳትኾኑ የደነገጉት። ብትኾኑ ግን ‘የቤተሰብ፣ የሕብረተሰብ፣ የሃገር እንዲሁም የኃይማኖት ተቋማት ይፈርሳሉ ይሏቹኋል’። እናንተ ግን በወንዶች ከመመራት ይልቅ ራሳችሁን ወደ መሪነት አምጡና ስልጣንን አጣጥሟት ወንዶቹ እንዳስጠነቀቁት ሳትጠፉ/ሳታጠፉ ደስተኛ ኑሮን ትኖራላችሁ”።

ከዚህም የተነሳ ብዙ ሴቶች እናታቸውን አይተው መጀመሪያ ከአባታቸው ኋላም ከባላቸው ትዕዛዝ ማፈንገጥ መሪነቱንም አለመቀበል ጀብድ ያደርጉታል፤ ንቅናቄውም ተተኪ አግኝቷልና ይቀጥላል ድምር ውጤቱ ግን…..

፫ኛ ሴታውሎቹ ወንዶች ደግሞ ያልተቋረጠና ልቅ የኾነ ወሲብን ከሴቶች ይፈልጋሉ። ይኼንንም ለማሳካት ሴቶች ጋብቻን በትምሕርትና ስኬት(career)ምክንያት(ዲፕሎማ፣ ዲግሪ፣ማስተርስ፣ ዶክትሬት….እያሉ) እንዲያዘገዩት እስከዚያው ድረስ ግን ከወደዱት ወንድ ጋር በተለያየ ጊዜ በመውጣት “በሰውነታቸው የፈቀዳቸውን ማድረግ ሰብዓዊ መብታቸው ነው” ሲሉ ይሞግታሉ።

በትዳር የተወሰኑትንም ቢኾን ያተረፉት “የወንዶች አምባገነናዊ አገዛዝ” ነጻነታቸውን እንደነፈጋቸው በማስመሰል ክቡር የኾነውን የአንድነት ምሥጢር ረግጠው እንዲወጡ ያበረታታሉ። ይኼን በማድረጋቸውም ለእነርሱ ሴሰኝነት ሴቶቹን “በመብት” ስም መጠቀሚያ ያደርጋሉ። በዓይነትና በብዛትም የተመኙትን ያገኛሉ።ስለዚህም የወንዶቹን (የአባትን አስተዳዳሪነት፣ የባልን ራስነት፣ የወንድን መሪነት) ይቃወማሉ።…..

መዘዙ በትውልዳችን ላይ ምን ይዞ መጣ ይመጣስ ይኾን? …… ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *