የጋብቻ እድሜ (በስንት ዓመታችን እናግባ የእድሜያችንስ ልዩነት ስንት ይኹን)


==============================
ሳተናው!

እንደተለመደው ሁሉ ይኽ ጽሑፍ መራር ተፈጥሮኣዊ ሐቅን ይዟል። እውነት ምቾት ብትነሳህም ፈርተህ ግን አትሽሻት። ይልቁንስ ተቀብለህ አጣጥማት ለሕሊናህ እረፍት፣ ለሕይወትህም አርነት(ነፃነት) ስትሰጥህ ቀሪውን ዘመንህንም እንዴት በጥበብ መኖር እንዳለብህም ታሳውቅሃለች።

ዛሬ የማነሳልህ ጉዳይ ጋብቻ የምንመሠርትበትን እድሜ በተመለከተ ነው። “እኔ አግብቻለሁ ምን ይጠቅመኛል” ካልከኝ ያገባህበትን እድሜ  እና አሁን የደረስክበትን ከሚስትህ ጋር በማነጻጸር በትዳራችሁ ውስጥ የሚከሰቱ አካላዊም ኾነ ስነልቦናዊ ለውጦችን ትታዘብበታለህ።

ከተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ አሁን ባለንበት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ጋብቻዎች በእኩያሞች መካከል አልያም በሁለት ወይም በሦስት ዓመት በሚበላለጡ ወንድና ሴት መካከል ይፈጸማል። 

ይኼንን ጥምረት በተለይ በከተማ ወይንም ተማሩ በሚባሉት የሕብረተሰብ ክፍሎች ላይም ይስተዋላል። አኹን ላይ ሕብረተሰባችንም ያለምንም በቂ መረጃ፣ ከተፈጥሮኣዊው እውነት በራቀ፣ ከተራ የእኩልነት ጩኸትም የተነሳም ይኼንኑ ያበረታታል።

መንፈሳዊ ነኝ ብትለኝም ያንተ መንፈሳዊነት ተፈጥሮህን፣ ፍጥረትን እና ፈጣሪህን እንድትረዳበት እንጂ በተለያዩ ዘመናት በስልጣኔ ስም ተሳበው በሚመጡት እሳቤዎች ተፈጥሮን እንድትክድበት አይደለም። 

ይኼን ብታደረግ ግን እንኳ ከሌላ ሰው(ፍጥረት) ጋር ልትኖር ቀርቶ የራስህን ተፈጥሮ መቀበል ከእርሱም ጋር ተስማምቶ መኖር ይኽንኑም ማሳደግ ይሳንሃል።

ታዲያ ከተፈጥሮኣችን ውጪ እንድንኖር ማን ግድ አለን? በከባቢያችን ያለው ልክ ያጣው የ”እኩልነት” ጩኸት በሴቶችና በሕጻናት ስም የሚነገደው ንግድ ነው። እርሱ ከተፈጥሮኣችን ውጪ አውጥቶን በትዳራችን ስኬታማ እንዳንኾን የተባረከ ትውልድም እንዳይወጣን ትልቁን አስተዋጽዖ ያደርጋል።

============================================================
በትዳር አብራህ እንድትኖር የምትመርጣት ሴት በእድሜ ቢያንስ አምስት አልያ ግን አሥር ዓመት የምትበልጣት ትኹን።
============================================================

ይኽን ደፍሬ እንድናገር ካደረገኙ ከብዙ ምክንያቶች መካከል ሦስቱን እነግርሃለሁ። ለሦስቱም ምክንያቶች ማስፈንጠሪያው ደግሞ እነኾ “ሴት ልጅ ከእርሷ በብዙ ነገር የተሻለ፣ ከፍም ያለ ወንድ ትመርጣለች”። 

እርሱ እንደ ሞገድ ለሚነሳና ለሚወድቀው ስሜቷ ወደብ፣ ከሌሎችም ኾነ ከራሷ ከሚመነጩ  ክፉ ኃሳቦች እና ድርጊቶች ደህንነት፣ ለቀጣዩም ትውልድ ዘር፣ ለቤተሰቡም ሕልውና አቅርቦት እንዲመጥን ትሻለች።

ምክንያት ፩ በጥበብ፣ በልምድ፣ በሞገስ ማሳደጉ
=====================================
ሳተናው!
እድሜህ በጨመረ ቁጥር ሰከን ትላለህ፣ ብዙ ጥበባትን በልብህ ልምዶችንም በመዳፍህ ትጨብጣለህ። እነዚህ ልምዶች፣ የስሜት እርጋታዎች፣ የጥበብ ኃብቶች በትምሕርት ማዕረግ ብዛት ሳይኾን ከእድሜ ብዛት የምታገኛቸው ናቸው።

እነዚህ የዘረዘርናቸው ደግሞ አንተ ልትመራው በተገባህ ትዳር ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዙ ትጥቆችህ ናቸው። 

ልብ አድርግ! ዘመኑ “ዘመነ ግርንቢጥ” ኾኖ “ተነጋግራችሁ ተግባቡ” ይሉናል እንጂ ሴት ልጅ የምትፈልገውን ሳይኾን የሚያስፈልጋትን፣ የተናገረችውን ሰምቶ ሳይኾን ያደረገችውን አይቶ የሚረዳትንና የሚረዳትን (ጠብቆና ላልቶ ይነበብ) ወንድ ትመርጣለች። 

ይኼንን ደግሞ ዕድሜህ ሲገፋ እና ከእርሷ ስትበልጥ ገንዘብ የምታደርገው ነው። በጉርምስናህ ወራትማ አብዛኛዎቹ ውሳኔዎችህና ድርጊቶችህ ከስሜት የመነጩ አይደሉምን?

ምክንያት ፪ ቁሳዊ ስኬት ማስከተሉ
================================

ወንድሜ ዘመንኛዋ ዓለም ከምትዋሸን ነገሮች ውስጥ በትዳር ተወስኖ በፍቅርም ተጣምሮ ለመኖር ቁሳዊ ስኬት ኢምንት እንደኾነ በፊልሙ፣ በዘፈኑ እና በተለያዩ መድረኮች ትነግረናለች። 

ውሸት ነው! ሳተናው! ዲፕሎማም ኾነ ዲግሪ አልያም ከቤተሰብ የወረስከው ኃብት ስላለክም ለማግባት አትቸኩል። 

ለምን መሰለህ፦ ትዳር ተቋም ነው፣ በዚህ ተቋም ውስጥ ደግሞ የሚፈጠሩት የቤት ቁሳቁሶች አልያም እንሰሳት ሳይኾኑ ነገ ሀገርን ካንተ የሚረከቡ ትውልዶች ናቸው።

ከስሜት(ከፈቃደ ስጋህ) ብቻ ተነስተህ ሳይኾን እግዚኣብሄርም በሰው ልጅ ላይ ያለውን ዓላማ ለማሳካት ስትል ተፈጥሮህን ጠንቅቀህ እወቅ። ያንተ ተፈጥሮ በርዕይ ተመርተህ ዓለምን ማበጀት፣ ለኑሮም ምቹ ማድረግ እንጂ ሴትን ማሳደድ አይደለም።

ሴት ልጅ በብዙ ውጣውረዶች ውስጥ አልፎ ስኬት ላይ የደረሰ ወንድ ይማርካታል። ይኽ በቁሙ ምንም ሕጸጽ የሌለበት ተፈጥሮኣዊ ሲኾን ጤናማ ጾታዊ ስበትንም ያስከትላል። ስለዚህም ስኬታማ ለጊዜው ባትኾን እንኳ እንዲያ የሚያደርግህ ርዕይ ጥረቱም ይኑርህ።

ሳተናው! ሚስት ሳይኾን የተጠራህበትን ርዕይህን ፈልግ፤ ሴትን ሳይኾን ስኬትን አሳድ በዚህም ሴቶቹ ራሳቸው ይሳባሉ። በጭራሽ! በጭራሽ! ግን ሴትን በስኬትህ መንገድ ላይ ስታገኛት ገንዘቤን ፈልጋ መጣች አትበል። ይኼ የተፈጥሮኣችንን ቅኝት ያለማወቅህና ያለመብሰልህ ውጤት ነው።

አስረጅ፦ በቀደመው ዘመን ከእጮኛ ቤት ሽማግሌ ይላካል። የልጅቷ ቤተሰቦች ምን ብለው እንደሚጠይቁ ታውቃለህ? “ሥራው ምንድን ነው? ምንስ አለው? በምንስ ያኖራታል?” ይሉ ነበር። ይኽ በአጭሩ በሕይወቱ “ምን አሳክቷል?” ማለት ነው።

እኔ እና አንተ ግን አወቅን፣ “ሰለጠንም” ብለን ይኼ እኮ “ኋላቀር አካሄድ ነው ” እንላለን። ይኽ ያላዋቂ የማይምም አነጋገር ነው።

ምሳሌ፦ አንተ የሠላሳ አምስት ዓመት ሳተና ከኾንክ የሀያ አምስት ዓመቷን ኮረዳ በዘረዘርናቸው ነጥቦች ምን ያክል ታጥቀህና ተገንብተህ እንደምትጠብቃት አስተውል። ይኼም አንተንም ኾነ እርሷን ፣ ትዳሩንም ኾነ ፍሬዎቹን በብዙ ፈርጁ ተጠቃሚ ያደርጋል።

ምክንያት ፫ አካላዊ ተፈጥሮኣችንን ስናስተውል
==================================

ሳተናው! 
የአካላዊ ተፈጥሮኣችንን (አፈጣጠሩን፣ አስተዳደጉን፣ አበሳሰሉን፣ አጠወላለጉንና አሟሟቱን) ብቻ ብናስተውል ወንድ ልጅ ሴትን በእድሜ በልጦ የማግባቱ ጥቅም ይገባናል።

የቀደሙት ሁለቱ ለድርደር ቢዳርጉ እንኳ ይኽ አካላዊ ተፈጥሮህ ነውና አስተውለው።

በዚኽ ሥር ሰባት ነጥቦችን አስቀምጬሌሃለሁ
፩ኛ…… ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *