የጋብቻ እድሜ ክፍል ፪ (በስንት ዓመታችን እናግባ የእድሜያችንስ ልዩነት ስንት ይኹን)

ሳተናው!

በቀደመው ጽሑፍ በአንተ እና ለትዳር በምትመርጣት ሴት መካከል በሚኖረው የእድሜ ልዩነት(ባንተ መብለጥ) የተነሳ የምታተርፋቸውን ሁለት ጥቅሞች አይተናል።

አንተ በእድሜ በመገፋትህ(ከእርሷ አንፃር) የምታገኛቸውን ልምዶች፣ የምትደርስባቸውን ስኬቶች እና የምትላበሳቸውም ጥበቦች በትዳርህ ስኬታማ ትኾን ዘንድ የሚያግዙህ፣ በተለይም በዋነኛው ሚናህ(መሪነት) ላይ ጉልህ አስተዋጽዖ ያላቸው ናቸው።

ምንም እንኳ የቀደሙት ሁለቱ (ጥበብ እና ስኬት) በወጣትነት እድሜ ሊገኙ ይችላሉ  ብንል ዛሬ የማወጋህ ግን ተፈጥሮህ የኾነ ተቀብለኸው እና ተስማምተህበት(ባትስማማበትም የማትቀይረው) ግን የምትኖርበት ሐቅ ነው።

===========================================================

ሳተናው!

አካላዊ ተፈጥሮኣችንን (አፈጣጠሩን፣ አስተዳደጉን፣ አበሳሰሉን፣ አጠወላለጉንና አሟሟቱን) ብቻ ብትታዘብ ወንድ ልጅ ሴትን በእድሜ በልጦ ማግባቱ ተገቢ ነው ትላለህ።

ምክንያት ፩ 
የሴትን ቶሎ መጎርመስ ስታይ(ከወንዱ የእድሜ አቻዋ አንጻር)፦ ሴቶች ከ8-12 ዓመት ውስጥ ጉርምስና ሲጀምሩ ወንዶች ከ9-14 ውስጥ ይጎረምሳሉ። ከዚህም የተነሳ የወንዶች አካላዊ ለውጥ የዘገየ መኾኑን ትረዳለህ።

ምክንያት ፪ 
የሴት ሰውነት በእድሜዋ ከሃያዎቹ መጀመሪያ እስከ አጋማሹ ድረስ ከፍተኛው የውበት ማማ ላይ ሲወጣ ለምለምነቷም(fertility) እንዲሁ የሰጠ ነው። ከዚያ በኋላ ግን እየቀነሰ ኼዶ በተለይ ከ35ኛ ዓመቷ በኋላ በከፍተኛ ኹኔታ ያሽቆለቁላል።ይኽም ማለት ለማርገዝ ስትቸገር ብታረግዝ እንኳ በወሊድ ወቅት የመሞት እድሉ ሰፊ ነው።

ምክንያት ፫ 
ሳተናው! ይኼ ሌላው ልታስተውለው የሚገባህ ተፈጥሮኣዊ ሐቅ፦ ሴት ልጅ ከወንድ ልጅ ቀድማ መብሰሏ ነው። አንዲት በቤት ውጥ በስነስርዓት ያደገች ሴት ከእድሜ አቻ ወንድሟ ይልቅ የተሻለ ቤተሰቡን የመንከባከብ፣ የማስተዳደር ብልሃትና ክህሎት አላት(የዛሬዎቹ?)።

ምክንያት ፬
ወንድ ልጅ ራሱን ገዝቶ ከስሜታዊነት ወጥቶ ወደኃላፊነት የሚመጣው በጥበብም መሞላት የሚጀምረው ከሠላሳ ዓመቱ በተለይ ከሠላሳ አምስት በኋላ ነው

ምክንያት ፭
ወንድ ልጅ እድሜው ሠላሳዎቹ ውስጥ ሲገባ በተለይም ከሠላሳ አምስት በኋላ በጥበብ ከመሞላቱ ባሻገር ግርማ ሞገስንም ይላበሳል ይኽም መከበርን ያተርፍለታል(ልብ አድርግ! ለወንድ ልጅ በሚስቱ ዘንድ መከበር ትልቁን ቦታ ይይዛል)።

ምክንያት ፮
ሴት ልጅ የማርገዣ እድሜዋ በጊዜ የተገደበ ነው። ትዳር የምትመሠርተው አንድም ዘርን ለመቀጠል ነውና ይኼንን ግምት ውስጥ ማስገባት አለበህ። 

ምክንያት ፯
ወንድ ልጅ በሕወት ባለበት ጊዜ ሁሉ መውለድ መቻሉ 

ከላይ የዘረዘርናቸውን ተፈጥሮኣዊ ሐቆች ይዘን ስንነሳ አንተ ከእጮኛ በእድሜ በልጠህ መገኘትህ ሁለታችሁንም ተጠቃሚ ሲያደርግ በተለይም አንተ ትዳርህን ልጆችህን በጥበብ እንድትመራ ያስችልሃል። በተጨማሪም የሚስትህ እድሜ በሃያዎቹ መጀመሪያ መኾን በገዜ ተገድቦ የተሰጣትን የተፈጥሮ ጸጋዋን በደንብ ለመጠቀም እድሉን ይሰጣታል።

ምሳሌ፦አንተ ከ32-35 ኾነህ ሚስትህ ደግሞ 22-25ብትኾን እና በ25 ዓመቷ ብትወልድ ልጁ 15 ዓመት ሲሞላው እርሷ 40 ይኾናታል። ነገር ግን እርሷ በ35 ዓመቷ ብትወልድ ልጁ 15 ዓመት ሲሞላው እርሷ 50 ይሞላታል።

ከላይ በተጠቀሰው ምሳሌ በሁለተኛው ላይ ማየት እንደምትችለው እረሷ አያት በምትኾንበት እድሜ የመጀመሪያ ልጇ ገና እየጎረመሰ ነው። ሁለተኛ እና ሦስተኛው ላይ ደግሞ ስንት እንደምትደርስ ገምት። 
ጥያቄው ታዲያ “ይኽ ምን ጉዳት አለው?” ነው።

መልሱ ደግሞ እነኾ፦ከአያታችሁ ጋር ለአጭር ጊዜ ኖራችሁ ታውቃላችሁ? አባትና እናት በቅርብ ሳይኖሩ አያት ያሳደጋችሁተን አያካትትም።

አያቶቻችን ትምሕርት ሲዘጋ ልጆቻቸውን “ልጆቹን እስቲ ላኳቸው” ብለው በጉጉት ይጠብቃሉ። ነገር ግን ኼደን ወር እንደተቀመጥን ደግሞ የእኛ እሳትነት ያሰለቻቸዋል። 

ከዚህ የምንማረው ነገር ቢኖር ሴት ልጅ እድሜዋ እየገፋ በሄደበት ወቅት ልጅ መውለዷ(በተለይም ከ35 በኋላ) ቢያስደስታትም እንደእናት ተንከባክቦ ማሳደጉን ግን በቅጡ ሳትጀምረው እንደሚሰለቻት ነው።

ይኼ አለመቻል ግን ብዙውን ጊዜ በልጆቹ “አስቸጋሪነት”፣ በዘመኑ “ክፉነት” እና በባልየው ስንፍና ይሳበባል። እርሷም ብስጩ፣ ደረሳ ኾደ ባሻ፣ ቁጡም ትኾናለች። በዚህ ላይ ደግሞ ካረጠች በኋላ ከሚከሰተው አካላዊና አእምሮኣሯዊ ለውጥ ጋር ሲደመር በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይኾናል።

ማጠቃለያ
ሳተናው!
ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ያስቀመጥናቸውን ጨምረህ በተፈጥሮኣዊ እወቀት ላይ ተመሥረት። ትዳርን ስትጀምረው በምክንያትና በዓላማ ይኹን። ውሸታሟ ዓለም በዘፈን፣ በዝሙት በስሜት አግለብልባህ “አንተ ከወደድካት ሌላው እዳው ገብስ ነው” ስትልህ አትመናት።

አንተ ሠላሳዎቹ ውስጥ ከከገባህ ሃያዎቹ መካከል ላይ ያለችውን ብታጭ ለትዳራችሁ ስምረት፣ ለቤታችሁ ድምቀት፣ ለልጆቻችሁ እድገት ተመራጭ ነው።

ልብ አድርግ! ተመራጭ ነው አልኩህ እንጂ ግዴታህ ነው አላልኩህም።

ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *