ደስተኛ ሚስት ደስተኛ ሕይወት ዐላማህን አትሳት በዚህ ተረት ተረት

ይኼንን አባባል ዛሬ ዛሬ በተደጋጋሚ መስማት የተለመደ ነው፤ ሚስትህን ደስተኛ ልታደርጋት እንደሚገባ። እርሷ ደርተኛ ከኾነች አንተም፣ ሕይወትህም ኾነ ቤተሰቡ ደስተኛ እንደሚኾኑ።

አንተም ከዚህ ዘመን የወለደው ተረት ተነስተህ ሚስትህን ማስደሰቱን ዋናው የመውጣት የመግባትህ ዐላማ አድርገኸው ይኾናል። በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን በዘፈን፣ በግጥም፣ በመጽሐፍት፣ በትያትር(በፊልም) እንዲሁም ከአንዳንድ ምስኪን ባሎች ቀጥተኛ ምስክርነት ደጋግመህ ትሰማዋለህና።

“የምኖረው፣ የምሠራው፣ የምደክመው፣…. …..፣ የምኾነውን ኹሉ የምኾነው ለእርሷ(ለሚስቴ) ነው።”
“ካለእርሷስ ምን ሕይወት አለኝ?” ትልም ይኾናል።

ነገር ግን እውነታው ከዚህ በጣም የራቀ ነው። ሚስትህ አንተ ልታስደስታት በምትሞክራቸው ሥራዎች ኹሉ አቃቂር ስታወጣ፣ ደስ ይላታል ብለህ ስትለፋ እርሷግን ስትከፋ፣ የእርሷን ደስታ ያማከለ ጥረትህ ሲጨምር የእርሷም ቅሬታ እንዲሁ ሲጨምር ግራ መጋባትህ አይቀርም።

ግራ አይግባህ ወንድሜ። ችግሩ ካንተ እንጂ ከእርሷ አይደለምና እርሷንም ኾነ በእርሷ የተነሳ የሔዋንን ዘር አታማር።

“እንዴት?” አልኸኝ?

ንሳ ከሕይወት የተገለበጠ ምክር

ዋነኛው ስሕተትህ ሚስትህን የኑሮህ ዓላማ የመውጣት የመግባትህ ምክንያት ማድረግህ ነው።

ወንድሜ እዚህ ምድር ላይ የመጣኸው በአጋጣሚ አይደለም በዓላማ እንጂ። ምናልባት የተረገዝክበትንም ኾነ የተወለድክበትን ኹኔታ ስትሰማ አጋጣሚ ይመስልህ ይኾናል። ነገር ግን ሰውን ወደ ምድር ማምጣትም ኾነ ወደ እርሱ መውሰድ(መፍጠሩንም ኾነ በሞት መውሰዱን) በጊዜውና በምክንያት የሚሠራው የፈጣሪ ብቸኛ ተግባር ነው።

እርሱ ሲሠራ ደግሞ እኔ እና አንተ በዘፈቀደ እንደምንሠራው ሳይኾን ኹሉን በምክንያት ለዓላማ ይሠራዋል።

እናም ያንተ ወደዚህ ምድር መምጣት ዐላማ አለው። ይኽን የተፈጠርክበትን ምክንያት ልታሳካው ያለህንም ዐላማ ፈልገህ አግኝ እንጂ ሚስትህ የኑሮህ ዐላማህ አትኾንም። ምንም ዐይነት ሥራ እርሷን ያስደስታታል ብለህ ሳይኾን ማድረግ ያለብህና ዐላማህንም የሚያሳካ አንድ ክፍል ስለኾነ ይኹን።

በአደባባይ ሥራህ ያለብህን ውጣውረድ ስታጫውታት ደስ የሚላት መስሎህ ቁጭ ብለህ ብታወራላት፣ ላግዛትም ብለህ ኩሽና ብትገባ ችግርን ከእነ ልጆቹ ቤትህ እየጋበዝከው ነው።

እነዚህን ውሸቶች ስትተገብር ከአደባባይ ሥራህ እርካታ ታጣለህ ምክንያቱም ደክመኽ ይዘህ በምትመጣው ደስተኛ አይደለችምና።

በእልፍኝህም ትከፋለህ ዋናውን ሚናህን ዘንግተኸዋልና።

ከኹሉ የሚከፋው ግን በመኝታ ቤትህ የነበረው የፍቅር ግለት ላይመለስ ይኼዳል።

ከዚያማ 3፣ 4፣ 5፣ ዐመቶች ሲያልፉ መቀዛቀዝ ይመጣል፣ አልፎአልፎም በትንሽ በትልቁም መጨቃጨቅ ይመጣል የፍቺ ወሬም ይሰማል።

ወንድሜ! ይኼ ማንም የማይነግርህ እውነት ነው።

እርሷን ለማስደሰት መውጣት መግባቴ ውጤቱ የከፋ ከኾነ ታዲያ፤ የተፈጠርኩበት ዓላማ፣ የባልነትስ ሚናዬ ምን ቢኾን ነው ሚስቴ ደስ የምትሰኘው?”….. ይቆየን

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *