ጀግንነትህ ውስጥህ ተኝቷልና ቀስቅሰው

የዛሬው ጽሁፌ ጠንካራ ነውና ለመጀመሪያ ቀን በዚህ ገጽ ላይ የተገኛችሁ አታንብቡት!!!!!!

ስማ! እኔ የምነግርህ ጠንካራ እንድትሆን እንጂ ስሜተ ስስ ሆነህ ስትደሰትም እንባ እንባ ስትናደድም እንባ እንባ ስታዝንም እዬዬ ሴት ወደድኩ ወይኔ ወይኔ እያልክ እንባህ እንዲቀድምህ አይደለም። ይህም ደግሞ ተፈጥሮዬ ነው እያልክ ስንፍናህን በፈጣሪህ አታሳብ። ቆፍጠን በል! ሰዉ ሁሉ “ሆዱ ቡቡ ነው” ሲሉህ ቡቡነት ያስወደደህ መስሎህ ለትንሽ ትልቁ አትነፋረቅ። ጨከን ቆፍጠን እንዳትል የሚያደርጉህ ሁሉ ወንድነትህን የሚቀሙህ የማይድን ቁስል፣ የማይሽር ጠባሳ የሚጥሉብህ ናቸው።

“ይሄ ጽሁፍ ይከብደኛል፣ መነፋረቁ የፍቅሬ መገለጫ ነው” የምትል ከሆነ፤ “የምትነግረኝ ወንድነት ጊዜው ያለፈበት ያፈጀ ያረጀ ነው”ም ካልክ ደግሞ ወደፊት ከዚህ የባሰ ወንድነት እጽፋለሁና አሁኑኑ ማንበብ አቁም። አዎ ይህ ጽሁፍ መስማት የፈለጉትን ለሚሰሙ ሳይሆን ምንም ብትመር እውነትን ለሚሹ ጀግንነትን ለሚናፍቁ ድልን ለሚያሸቱ ገንዘብም ለሚያደርጉት በቻ የተጻፈ ነውና።

ወዳጄ! ወንድ ሆነህ ተፈጥረሃል እና ወንድ ሁን!!!!!
በኑሮህ ስኬትም በለው በፍቅር ህይወትህ ወንድ ሆነህ ተገኝ።

ምንድነው ወንድነት? (እንደጋግመዋለን)
ወንድ መሪ፣ ወሳኝ፣ አዛዥ፣ ናዛዥ፣ አስተዳዳሪ፣ ፍቅር ሰጪ(ለሚስቱ)፣ አስቦ ተናጋሪ፣ የተናገረውን ፈጻሚ(ቃሉን ጠባቂ)፣ ስሜታዊ ሳይሆን ምክንያታዊ፣…..ነው። ይህን ስብዕና ትቶ በተቃራኒው መንገድ የሄደው ምን ሸበላ ቢሆን፣ ምን ሰውነቱ የሰጠ ቢሆን፣ ምን ዝና፣ ገንዘብ ፣ሥልጣን፣የሰው መውደድ በአንድም ሆነ በሌላ አጋጣሚ ቢያገኝ በወንድነቱ ግን የከሰረ ነው። አንተ ግን በአመንክበት ዓላማ ጽና።ለታመንክለት ሰው ቃልህን ጠብቅ። ዓማህን አቋምህን አስር ጊዜ የምትቀያይር ወላዋይ አትሁን። ወሬ ወዳድ ወረኛ፤ ለወሬ ሟች የወሬ ሱሰኛ አትሁን፤ ሰዎች ስለ እኔ ምን አሉ? ሳትል የሰዎችን ምስክርነት ሳትሻ ስብዕናህን አሻሽል። ለመወሰን ምርጫዎችን አታብዛ በትዳርህ ውስጥ የአዛዥነትን ሚና ለመጫወት ይሉኝታ አይያዝህ በፍቅርም አታመኻኝ። ሚስቴ እኔ እንደምወዳት አትወደኝም እንደምስማት አትስመኝም እንደማቅፋት አታቅፈኝም እንደም…… አት………. አትበል ይሄ ያንተ እና ያንተ ሥራ፣ግዴታ ነውና። በነገሮች ሁሉ ስሜታዊ አትሁን መቸም የዛሬ ጊዜ ወንዶች ለሴቶች ከማይመቹባቸው ጠባዮች አንዱ ይህ ስሜታዊ መሆን ነው።ልጆቻቸውን ማስከተብ የሚፈሩ ፣ልጆቹም ሆኑ እናቶቻቸው ሲያለቅሱ አብረው የሚያነቡ፣ ልጆች ሲቦርቁ አብረው የሚቦርቁ፣ ሲደሙ ሙሾ የሚያስነኩ ናቸው።

የማንነትህ ልክ፣የድርጊቶችህ ሚዛን ፣ የኩራትህ ምንጭ፣ በራስ የመተማመንህ ምክንያት የፈጣሪህ ቃል እንጂ የሰው አፍ አይሁን። እንዲህ ስትሆን በየትኛውም አይነት የህይወት ማዕበል ውስጥ ማለፍ የምትችል የምንጊዜም አባወራ ትሆናለህ።

ልብ አድርግ አንተ ወንድ ነህ ያውም አባወራ ግን መሆን እስከፈለክ ብቻ ነው። ልብህ ውስጥ ጀግና ተኝቷል፤ የአፈቀርኩ ለቅሶ አይሉት ዘፈን እየዘፈንክ፣ በእኩልነት ሽፋን የምስኪን ኑሮ እየኖርክ፣ በትምህርት እና ሥራ ሰበብ ለሚስትህ በድንህን እያሳቀፍካት አትኑር። እኔ እንዲህ እና እንዲያነኝ ማለቱን ተውና ጀግናህን ቀስቅሰው ሥራህንም ሥራ፣ እርሱም ይመሰክርልሃል።
ይቆየን…

Author: Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

Henok Hailegabriel

A Husband & a Father who believes in men dominance, anti feminist and helps other men to boost their masculinity, dominate life & save their marriages.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *